Thursday, March 23, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናምርጫ ቦርድ አማራና ኦሮሚያን ጨምሮ ለአራት ክልሎች ማሳሰቢያ ሰጠ

ምርጫ ቦርድ አማራና ኦሮሚያን ጨምሮ ለአራት ክልሎች ማሳሰቢያ ሰጠ

ቀን:

የዕጩዎች ምዝገባ እስከ የካቲት 30 ቀን ድረስ ተራዝሟል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ደኅንነት ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ባደረጋቸው ውይይቶችና ንግግሮች መሠረት አብዛኛዎቹ የምርጫ ክልሎች ጥበቃ ሊሟላላቸው መቻሉን ጠቁሞ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በሱማሌና በደቡብ ክልሎች 98 የምርጫ ክልሎች ጥበቃ ስላልተመደበላቸው በአስቸኳይ እንዲያሟሉላቸው አሳሰበ፡፡

ቦርዱ የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ጥበቃ ያልተመደበላቸው የምርጫ ክልል ቢሮዎች በኦሮሚያ ክልል 21 የምርጫ ክልሎችበሶማሌ ክልል 31 የምርጫ ክልሎች፣አማራ ክልል 40 የምርጫ ክልሎችና በደቡብ ክልል ስድስት የምርጫ ክልሎች ጥበቃ አልተመደበላቸውም፡፡ በመሆኑም በአስቸኳይ ጥበቃ እንዲመደብላቸው አሳስቧል፡፡

ምርጫ ቦርድ ስድስተኛው አጠቃላይ አገራዊ ምርጫ 673 የምርጫ ክልሎችን በመክፈት የዕጩዎች ምዝገባን እያከናወነ መሆኑን አስታውሶ፣ የምርጫ ክልሎችን ደኅንነታቸውን የማስጠበቅላፊነት የክልልና የከተማ መስተዳድሮች መሆኑን አስታውቋል።

ቦርዱ በተለያዩ ጊዜያት የምርጫውን ደኅንነት ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይቶችና ንግግሮችን እያደረገ የቆየ መሆኑን፣ በዚህም መሠረት አብዛኞቹ የምርጫ ክልሎች ጥበቃ እንደተሟላላቸው ገልጿል።

ነገር ግን ከላይ በተገለጹት አራት ክልሎች 98 የምርጫ ክልሎች፣ አስፈላጊውን የደኅንነት ከለላ ከክልል መንግሥታቱ እያገኙ አለመሆናቸውን አስረድቷል፡፡

ቦርዱ ክልሎች በአስቸኳይ ለቀሪ የምርጫ ክልል ቢሮዎች የጥበቃ ምደባ እንዲያከናውኑ አሳስቦ፣ ሳይመድብ ቀርቶ በጥበቃ አለመኖር ምክንያት ሊፈጠሩ የሚችሉ የምርጫ አፈጻጸም ችግሮች ቢያጋጥሙክልሎቹ መስተዳድሮችና የፀጥታ አካላት ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ አስገንዝቧል።

ምርጫ ቦርድ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. የዕጩዎችን ምዝገባ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው፣ የዕጩዎች ምዝገባደትን አስመልክቶ በተለያየ ወቅት የተለያዩ መረጃዎችን ሲያደርስ እንደነበር አስታውሷል። በተጨማሪም የዕጩዎች ምዝገባን አስመልክቶ ሦስት የተለያዩ ምክክሮችን ከፓርቲዎች ጋር ማከናወኑን ገልጿል፡፡

በመሆኑም በመጀመርያ ዙር ዕጩዎች ምዝገባ የተጀመረባቸው ክልልሎች ወይም በከተማ መስተዳድሮች ማለትም በአዲስ አበባበድሬዳዋ፣ በኦሮሚያበሐረሪበጋምቤላ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች የዕጩዎች ምዝገባን የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም. መጠናቀቁን አስተውቋል፡፡ ነገር ግን የዕጩዎች ምዝገባ ዘግይተው በጀመሩ ክልሎችና ቦታዎች ማለትም በአማራ፣ በሶማሌ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ በምዕራብና በምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ በቄለም ወለጋናሆሮ ጉድሩ፣ በደቡብና በሲዳማ ክልሎች በመርሐ ግብሩ መሠረት የካቲት 26 ቀን 2013 .ም. መጠናቀቅ የሚገባው ቢሆንም በቢሮዎች መከፈት፣ መዘግየትና፣ እንዲሁም የትራንስፖርትና ሌሎች እክሎችንና የፓርቲዎች አቤቱታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ሁለተኛ ዙር የዕጩዎች ምዝገባ እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 .ም. ድረስ እንዲራዘም ማድረጉን፣ ፓርቲዎችም በተሰጡት ተጨማሪ ቀናት ውስጥ ምዝገባቸውን እንዲያጠናቅቁ አሳስቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...