Wednesday, March 22, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በስም መመሳሰል የባንክ ሒሳባቸው የታገደባቸው በርካታ ግለሰቦች ችግር ላይ መውደቃቸውን ተናገሩ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከውጭ ገንዘብ ምንዛሪ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕግድ ከጣለባቸው ግለሰቦች ጋር በስም መመሳሰል፣ የወር ደመወዛቸው የታገደባቸው ግለሰቦች፣ በችግር ውስጥ መሆናቸውን ተናገሩ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከጥር 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ 65 ግለሰቦችና ተቋማት፣ ከሁሉም ንግድ ባንኮች ጋር ያላቸው የቢዝነስ ግንኙነት እንዲቋረጥ፣ የባንክ ሒሳባቸውም ታግዶ ማጣራት እንዲደረግባቸው ሰርኩላር ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡

ባንኩ በቁጥር V/G/FIS/005/2021 ለሁሉም የንግድ ባንኮች ባስተላለፈው ሰርኩላር፣ የ65 ግለሰቦችና ተቋማት የባንክ ሒሳብ እንዳይንቀሳቀስ ታግዷል፡፡ ብሔራዊ ባንክ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 780/2005 እና ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም የወጣውን መመርያ ቁጥር 01/2006 አንቀጽ (37) ድንጋጌን በመጥቀስ፣ የፋይናንስ ሥራ ለመሥራት ፈቃድ ከሌላቸው (Shell Banks) ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳያደርጉ ባንኮቹን አስጠንቅቆ፣ የፌዴራል ፖሊሲ ምርመራ እንዲያደርግ የ65 ግለሰቦችና የድርጅቶች ዝርዝር የላከ ቢሆንም፣ ከግለሰቦች ጋር ተመሳሳይ ስም ያላቸው በርካታ ግለሰቦች መቸገራቸውን እየገለጹ ነው፡፡  

ደመወዛቸውን ከባንክ ለመቀበል (ለማውጣት) የሄዱ በርካታ ግለሰቦች፣ በባንኩ ሠራተኞች በልዩ ትኩረት እየታዩ፣ ‹‹መንግሥት ሒሳባችሁ እንዲታገድ ትዕዛዝ ደርሶናል›› በማለት እየመለሷቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ለምን እንደታገደ ሲጠይቁ እንኳን ተገቢ ምላሽ እንደማያገኙ፣ ወደ ኃላፊዎችም ቢሄዱ ምላሽ ስለተነፈጋቸው ግራ መጋባታቸውን ተናግረዋል፡፡

‹‹ጥፋተኛን በሠራው ነገር መጠየቅ ወይም አጣርቶ ምላሽ መስጠት ሲገባ፣ እኛ ለምን ያለሥራችን ከእነ ቤተሰቦቻችን እንድንቸገር ያደርጋል?›› በማለት የሚጠይቁት ግለሰቦቹ፣ የሚመለከተው አካል ወይም መንግሥት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

በርካታ ግለሰቦች ከባንክ ሒሳብ መታገድ ጋር በተያያዘ እየደረሰባቸው ያለውን ችግር በሚመለከት ማብራሪያ እንዲሰጡ ሪፖርተር ያነጋገራቸውና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ ኃላፊ በሰጡት ምላሽ፣ ችግሩ መኖሩን አረጋግጠው፣ ነገር ግን ስማቸው ተመሳሳይ የሆኑ ግለሰቦችን ማንነታቸውን በፊርማ ናሙና የመለየት ሥራ መከናወኑንና በሁለት ሳምንታት ውስጥ መፍትሔ እንደሚያገኙ ተናግረዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች