Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዓለምማርች 8 ሲታሰብ

ማርች 8 ሲታሰብ

ቀን:

የዓለም ሴቶች ቀን ሴቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን አበርክቶ በማጉላትና የተደቀኑባቸው ውስብስብ ችግሮች እንዲፈቱ ምልከታ በመስጠት መከበር ከጀመረ ከ100 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል፡፡

ሴቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም በደሃና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገሮች  የሴቶች ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ አነስተኛ ነው፡፡ ሴቶች ለፆታዊ ጥቃት የተጋለጡትና ድህነት አብዝቶ የሚፈትናቸውም በየአገራቸው ያላቸው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ አነስተኛ በመሆኑ ነው፡፡

በተለያዩ ውስብስብ ችግሮች ውስጥ አልፈው ለፖለቲካ ውሳኔ ሰጪነት የሚበቁትም ጥቂት ናቸው፡፡ ዩኤን ውሜን በቅርቡ ይፋ ያደረገው ሪፖርት እንደሚያሳየውም፣ ሴቶች በመምራትና በፖለቲካ ሕይወት መሳተፋቸው በየአገራቸው ለሚኖረው ዕድገት አስተዋጽኦው ጉልህ ቢሆንም፣ ያላቸው ሥፍራ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ ሴቶች ውሳኔ መስጠት ላይ ያላቸው ውክልናም አነስተኛ ነው፡፡

- Advertisement -

አሁን ላይ በዓለም 22 አገሮች ብቻ ናቸው ሴት የአገር መሪ ወይም ጠቅላይ ሚኒስትር ያላቸው፡፡ 119 አገሮች ደግሞ ፈጽሞ ሴት መሪ ኖሯቸው አያውቅም፡፡

ማርች 8 ሲታሰብ

ሴት ሚኒስትሮች 21 በመቶ ሲሆኑ፣ የካቢኔ አባሎቻቸውን 50 በመቶ ሴቶችን ያደረጉ አገሮች ደግሞ 14 ብቻ ናቸው፡፡ ሴት ሚኒስትር የሚሆኑባቸው ዘርፎችም የሴቶች ጉዳይ፣ የሕፃናትና ወጣቶች፣ ጤና፣ ማኅበራዊ፣ ሥልጠናና ሥራ አጥነት ዘርፎች ናቸው፡፡

ሴቶች በፖለቲካው፣ በማኅበራዊውና በኢኮኖሚው ጎልተው እንዳይወጡ በየአገራቸው ለሚኖረው ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳያበረክቱ የማኅበረሰቡ ወግ፣ ልማድና ባህል የደቀነባቸውን መሰናክሎች እንዲያልፉ፣ መንግሥታዊ፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ፣ ዓለም አቀፍ ተቋማትና መንግሥታት ጥረት ማድረጋቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ ለውጦች እንዲመጡ አስችሏል፡፡ ሆኖም ሴቶች ዛሬም መድረስ ከሚገባቸው ማማ ላይ አይገኙም፡፡

ከታኅሣሥ 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ደግሞ ሴቶች ላይ ተጨማሪ ጫናን አሳድሯል፡፡ ዓለም አቀፉ ሥራ ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው በኮቪድ ምክንያት ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ኢኮኖሚያዊ ጫና ውስጥ ገብተዋል፡፡

ከወንዶች ይልቅ በወረርሽኙ ምክንያት ከሥራ የተፈናቀሉት ሴቶች ናቸው፡፡ ቤት በመቀመጣቸው ከሚጠብቃቸው ኃላፊነት በተጨማሪ ሥራ ማጣታቸው ለከባድ ችግር አጋልጧቸዋል፡፡

በ2020 ወደ አምስት በመቶ ያህል ሴቶች ሥራቸውን አጥተዋል፣ አልያም የሚሠሩበት ሰዓት ተቀንሷል፡፡ ይህ ከወንዶች ሲሰላ የ1.2 በመቶ ብልጫ አለው፡፡  ሥራ አጥተዋል፡፡

በዓለም ማንኛውም ነገር ሲፈጠር ቀድመው የሚጠቁት ሴቶች ናቸው፡፡ ካለባቸው ውስብስብ ችግር ላይ በየጊዜው የሚፈጠሩ ችግሮች ሁለት ጫና እንዲሸከሙ አድርገዋቸዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬስ እንደገለጹት፣ የፆታ እኩልነት አለመስፈን በተለይ ዓምና ላይ ጨምሯል፡፡ የትምህርት መዘጋትና ከቤት መሥራት ሴቶች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖንም ፈጥሯል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሴቶች ጠንካራ ፈተና የገጠማቸውም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በዓለም ኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ሕይወትን ሲያስተጓጉል ነው፡፡ ይሁን እንጂ የኮቪድ ሕሙማን በማከምና በመንከባከብ ከፊት በመገኘት ጉልህ አስተዋጽኦ ካደረጉትና እያደረጉ ከሚገኙት የሕክምናው ዘርፍ ባለሙያዎች ሴቶች አብዛኛውን ቁጥር ይይዛሉ፡፡ ሴቶች ከፊት ሆነው የችግሩ ገፈት ቀማሽ ቢሆኑም፣ ኮቪድን የተመለከቱ ፖሊሲዎች ላይ ያላቸው ተሳትፎ አናሳ መሆኑን ተመድ ይገልጻል፡፡

በዩኤን ውሜን ጥናት መሠረት፣ 60 በመቶ ሴቶች በኢመደበኛ ሥራ የተሰማሩ ናቸው፡፡ ቁጥጥር በማይደረግባቸውና በሕግ በማይገደዱ በተለይም ታክስ ሳይከፍሉና ከየመሥሪያ ቤታቸውም ጥቅማ ጥቅም ሳያገኙ የሚሠሩም ናቸው፡፡ በብዛት ተሰማርተው የሚገኙትም በኮሮና ወረርሽኝ በስፋት ለችግር በተጋለጡት በሆቴል ኢንዱስትሪ ዘርፍና በሕፃናት ጥበቃ ማዕከላት ነው፡፡

የተመድ ድረ ገጽ እንደሚያሳየው 60 በመቶ ሴቶች በኢመደበኛ ኢኮኖሚ ውስጥ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ ይህም ዝቅተኛ ተከፋይ እንዲሆኑ፣ እንዳይቆጥቡና ለከፍተኛ ድህነት እንዲጋለጡ አድርጓል፡፡

ሴቶች ወንዶች ከሚከፈላቸው 23 በመቶ ያነሰ ይከፈላቸዋል፡፡ በፓርላማ ያላቸው መቀመጫ 24 በመቶ ነው፡፡ ከሦስት አንዱ አካላዊ ወይም ፆታዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡ 200 ሚሊዮን ሴቶች ደግሞ ተገርዘዋል፡፡

ሴቶች ላይ የሚደርሰውን ግርዛትና ያለ ዕድሜ ጋብቻ በ2030 ለማስቆም ግብ ያስቀመጠው ተመድ፣ የዓለም የሴቶች ቀን ለውጥ ላይ በማተኮር የ2030 ግብ እንዲሳካና ሴቶች በየአገራቸው በሚኖረው ልማት እንዲሳተፉ አገሮች የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል ብሏል፡፡

በውስብስብ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ከችግሩ ለማውጣት ለከፍተኛ ደረጃ የበቁትን ደግሞ በማጉላት የሚከበረው የዓለም የሴቶች ቀን የዘንድሮ ጭብጥ ‹‹ቹዝ ቱ ቻሌንጅ›› የሚል ነበር፡፡ ከፈተና ለውጥ ይመጣል የሚል ሐሳብም ይዟል፡፡

ሰኞ የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም. (ማርች 8) በኢትዮጵያም በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡ በየትውልዱ የነበሩ ሴቶች በአገራቸው የነበራቸውን ተሳትፎ በማጉላት፣ አካላዊ ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግና ውይይቶች በማዘጋጀት በተለያዩ ዘርፍ መሥሪያ ቤቶች ተከብሯል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...