Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበጤናማ ከተሞች ሽርክና የተደገፈው የአዲስ አበባ የመንገድ ደኅንነት ሥራ

በጤናማ ከተሞች ሽርክና የተደገፈው የአዲስ አበባ የመንገድ ደኅንነት ሥራ

ቀን:

በአዲስ አበባ ከተማ በየዓመቱ በአማካይ 450 ሰዎች በላይ በትራፊክ ግጭት ምክንያት ሕይወታቸውን ያጣሉ፡፡ ለመንገድ ትራፊክ አደጋ ከሚያጋልጡ ምክንያቶች ውስጥ ደግሞ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር የአደጋ መንስዔ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ  መግለጫ ያስረዳል፡፡

በፍጥነት ማሽከርከር ለአደጋ የማጋለጥ ዕድሉ ከፍተኛ ሲሆን የሚያደርሰው ጉዳትም እንዲሁ የከፋ ያደርገዋል፡፡ ይኸውም በአጠቃላይ ከሚደርሰው የትራፊክ ግጭት ውስጥ ሢሶው  ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር እንደሚሸፍን ጥናቶች ያመለክተሉ፡፡

የከተማዪቱ አስተዳደር የማኅበረሰቡ ከፍተኛ የጤና ችግር የሆነውን፣ በተለይም አምራቹን  ዜጋ እየቀጠፈ ያለውን የትራፊክ ግጭት ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ የመፍትሔ ዕርምጃዎችን በመውሰድ ላይ እንደሆነ ዘርፉን የሚመራው ተቋም ይገልጻል፡፡ እነሱም የትራፊክ አደጋ መረጃዎች አያያዝና አስተዳደር ሥርዓትን ማዘመን፣ የመንገድ መሠረተ ልማት ግንባታና ዲዛይን ማሻሻያ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ እንዲሁም የትራፊክ ደንብን ማስከበርና የፍጥነት ገደብ ቁጥጥር ሥራዎች ዋናዎቹ ናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ፣ ከጤናማ ከተሞች ሽርክና ጋር በመተባበር በከተማዋ የተመረጡ የተለያዩ ኮሪደሮች የመንገድ ደኅንነትን ለማረጋገጥ ሁለተኛውን ዙር የመንገድ አካፋይ ደኅንነት ማሻሻያና የፍጥነት አስተዳደር ፕሮጀክት በስፋት ማከናወኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሂራጳ ጂሬኛ ሂራጳ (ኢንጂነር) በሰጡት የፕሬስ መግለጫ ገልጸዋል፡፡

ኤጀንሲው በመጀመርያ 4.5 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑትን ከጎሮጃክሮስመብራት ኃይል ሃያ አራት ኮሪደሮች ለይቷል፡፡ የኮሪደሮቹ ሁለቱም አቅጣጫዎች 30 ሜትር ስፋት ያላቸው ሁለት ሌኖች የያዙ ናቸው፡፡ በተጨማሪም የእግረኛ መንገድና የመንገድ አካፋይ ዲዛይን የተደረገውና የተገነባው ዋና እና መጋቢ መንገዶችን ጥቅም ላይ ለማዋል በወጣው መመዘኛ መስፈርት መሠረት የተከናወነ ነው፡፡

የተመረጡ ኮሪደሮች ከመሀል ከተማ ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ ከመኖሪያ አካባቢ ወደ ሥራ ቦታ ደርሶ መልስ የሚያጓጉዝ መስመር በመሆኑ ስትራቴጂካል እንደሆነ ታምኖበታል፡፡ ከምንም በላይ ኮሪደሮቹ የተመረጡት የመንገድ ደኅንነትና የትራፊክ እንቅስቃሴ ችግር ያለባቸው በመሆኑ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ በማሳያነት 2008 እስከ 2010 .. ያለው የሦስት ዓመታት የትራፊክ አደጋ መረጃ እንደሚያሳየው፣ በእነዚህ የመንገድ አካፋዮች ከሠላሳ ሰዎች በላይ በግጭት ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡

በመንገድ ደኅንነትና ፍሰት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ከተወሰዱ የመፍትሔ ዕርምጃዎች መካከል፣ በመጋጠሚያና ማቋረጫ ቦታዎች ላይ የተደረገ ማሻሻያ፣ የፍጥነት ወሰንን መወሰን፣ የተሽከርካሪ ፍጥነት ማብረጃና መቀነሻ ሥራዎችና የመንገድ አካፋይ አጥሮች ዋናዎቹ መሆናቸው የኤጀንሲው መግለጫ ያስረዳል እነዚህ በምሕንድስናው የተወሰዱ ዕርምጃዎች ከትራፊክ ደንብ ማስከበር  ጋር ተደማምረው በኮሪደሮች አካባቢ ያለውን የተሽከርካሪዎች ፍጥነት ለመቆጣጠር ያስችላሉ፡፡

አዲስ አበባ የዓለም አቀፍ ከተሞች መረብ አባል እንደ መሆኗ  የከተማዋ ኮሪደር ደኅንነት ማሻሻያና ሁለተኛ ዙር የፍጥነት አስተዳደር ፕሮጀክት መጠናቀቁን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሂራጳ አስታውቀዋል፡፡

የጤናማ ከተሞች ሽርክና ዕውቅና ያለው ዓለም አቀፍ የከተሞች መረብ ሲሆን፣ እንደ ካንሰርና ስኳር፣ የመንገድ ትራፊክ አደጋና የመሳሰሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከል በዓለም  300 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ሕይወት ለመታደግ ትኩረት ሰጥቶ ይሠራል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ከዚህ ዓለም አቀፍ ኢንሺዬቲቭ ጋር የመንገድ ደኅንነት ማሻሻያ ሥራዎች ላይ በጋራ ትሠራለች፡፡

የጤናማ ከተሞች ሽርክና ዓለም አቀፍ መረብ የመጀመርያ ዙርአዲስ አበባ የተጀመረው 2010 .. ሲሆን፣ ሽርክናው ከፍጥነት ወሰን በላይ በማሽከርከር የሚከሰት የትራፊክ አደጋን ለመከላከል 50 ሺሕ የአሜሪካ ዶላር ለከተማው አስተዳደር የፍጥነት መቆጣጠሪያ ራዳር ግዥ የሚውል ድጋፍ አድርጓል። ዓምና በዚሁ ተቋም የመጀመርያ ዙር የፍጥነት አስተዳደር ፕሮጀክት 90,819.12 የአሜሪካ ዶላር ዕርዳታ የተገዙና በፒያሳ ዙሪያ የተተከሉ ዲጂታል ቋሚ የፍጥነት መጠን ጠቋሚዎችን በመትከል በአካባቢው ያለውን ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ለመቀነስና ሕግ ማስከበሩን  በቴክኖሎጂ ለመደገፍ ተችሏል፡፡

 እንደ ኤጀንሲው ማብራሪያ፣ የተገዛው ራዳር ብዙ ጠንካራ ጎኖች ያሉት ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ቀንም ሆነ ሌሊት የመሥራት አቅም ያለው፣ ስህተት እንዳይሠራና አውቶማቲክ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው። በቪዲዮ የተደገፈም ዳታቤዝ ያለው፣ በመስክ ላይ ማተም የሚችል፣ ለመቆሚያ የሚያገለግል ትራይፖድ ያለው ነው፡፡

በአዲስ አበባ የሚደርሰውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ እንዲረዳ ጥብቅ የትራፊክ ሕጎችን በማስከበር ላይ እንደሚገኝ የሚገልጸው ኤጀንሲው፣ ጠጥቶ ማሽከርከርን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የአልኮል መጠጥ መፈተሻ ዘመናዊ መሣሪያዎችን ግዥ በመፈጸም ለአሥሩም ክፍለ ከተሞች መስጠቱን አስታውሷል፡፡

የጤናማ ከተሞች ሽርክና የብሉምበርግ ፊላንትሮፒስ ከዓለም ጤና ድርጅትና ቫይታል ስትራቴጂስ ጋር በመተባበር ድጋፍ የሚሰጡት ሲሆን፣ ሽርክናውም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችንና ጉዳቶችን ለመከላከል ውጤታማነታቸው የተረጋገጠ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በመተግበር ከተሞች የሚጫወቱትን የላቀ ሚና ዕውቅና የሚሰጥ ፕሮጀክት ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...