Wednesday, March 22, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ባለሀብቶች አትክልትና ፍራፍሬ ለማምረት መሰማራት ቢፈልጉም የመሬት አቅርቦት ችግር መኖሩ ተገለጸ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

በአትክልትና በፍራፍሬ ዘርፍ ተሰማርተው ለማምረት የሚፈልጉ የአገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች ቁጥር እየጨመረ ቢመጣም፣ መንግሥት መሬት ማቅረብ ባለመቻሉና በየተቋማቱ ባሉ የአሠራር ማነቆዎች ምክንያት ወደ ሥራ መግባት እንዳልቻሉ ተገለጸ፡፡

መንግሥት ወደ አገር የሚያስገባውን የስንዴ ምርት ሙሉ ለሙሉ ለማቆም እንደሚያደርገው ጥረት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ለሚታዩ ችግሮች ትኩረት ቢሰጥ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የአትክልትና ፍራፍሬ ፍላጎትን ሙሉ ለሙሉ ከማርካት ባለፈ ወደ ውጭ አገር ተልኮ ትልቅ ገቢ የማስገኘት አቅም ያለው ዘርፍ ነው ሲሉ፣ የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ አምራችና ላኪዎች ማኅበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ ለሪፖርተር ተናገሩ፡፡

አሁን በሥራ ላይ ያሉት የአትክልትና ፍራፍሬ አምራቾች የማስፋፊያ ቦታ ከሚጠይቁት በተጨማሪ፣ በርካታ የአገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች ጥያቄ እያቀረቡ እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

የቅርብ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በኢትዮጵያ ከ15 ሚሊዮን ሔክታር በላይ የሚታረስ መሬት አለ፡፡ ከዚህ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ በአትክልትና በፍራፍሬ አልሚዎች እየለማ ያለው መሬት 1,400 ሔክታር ብቻ ነው፡፡

የአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ በየዓመቱ ወደ ግማሽ ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኝ ሲሆን፣ ከ200,000 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ደግሞ የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡ ወደ ውጭ ተልከው የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ ሸቀጦች ውስጥ እስከ አምስተኛ ደረጃ ይይዛል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ወደ ዘርፉ ለመግባት ከሚጠይቁ ባለሀብቶች ውስጥ አቦካዶ፣ ማንጎ፣ ስትሮበሪ፣ አበባ፣ ብርቱካንና የመሳሰሉ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ለማምረት እንደሆነ አቶ ቴዎድሮስ አክለው ገልጸዋል፡፡

ከመሬት አቅርቦት በተጨማሪ በባለሀብቶች የመሠረተ ልማት ግንባታዎች በተለይም የመንገድ፣ የኤሌክትሪክ፣ የውጭ ምንዛሪ፣ የአድካሚ የሆኑ የመንግሥት ተቋማት አሠራሮችን መንግሥት ሊቀርፍ እንደሚገባ እንደሚፈልጉ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

በከፍተኛ ደረጃና በመካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የአትክልትና ፍራፍሬ አምራች ድርጅቶች እየጠየቁት ያለው ዋናው ችግራቸው ከተፈታ፣ በአጭር ዓመታት አሁን ያለውን ምርት በአሥር እጥፍ ማሳደግ ይቻላል ብለዋል፡፡

የውጭ ባለሀብቶች ብዙውን ጊዜ የኢትዮጵያን የአየር ሁኔታ፣ አገሪቱ ለዓለም አቀፍ ገበያ ያላትን ቅርበት፣ ዘርፉ ያልተነካ በመሆኑና በተለያዩ መሰል ምክንያቶች ሁልጊዜም ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ማድረግ ይፈልጋሉ ሲል አቶ ቴዎድሮስ አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ አትክልትና ፍራፍሬ አምራችና ላኪዎች ማኅበር ከክልልም ሆነ ከፌዴራል መንግሥት አካላት ጋር መሬት ስለሚገኝበት ሁኔታ ንግግር እያደረገ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች