Wednesday, September 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናባልደራስ ልዩ የምርጫ ችሎቶችን ገለልተኝነት ለመፈተሽ ወደ ፍርድ ቤት እንደሚያመራ አስታወቀ

ባልደራስ ልዩ የምርጫ ችሎቶችን ገለልተኝነት ለመፈተሽ ወደ ፍርድ ቤት እንደሚያመራ አስታወቀ

ቀን:

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አባሎቹን በዕጩነት ለማቅረብ ያቀረበው አቤቱታ በምርጫ ቦርድ ውድቅ መሆኑን ተከትሎ፣ ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት በማምራት የልዩ የምርጫ ችሎቶችን ገለልተኝነት እንደሚፈትሽ አስታወቀ፡፡

ይህ የተገለጸው ፓርቲው ከአገራዊ ምርጫው ጋር በተያያዘ ሐሙስ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤቱ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ወቅት ነው፡፡ የባልደራስ የሕግና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሔኖክ አክሊሉ እንዳስታወቁት፣ ባልደራስ በሁለት ጉዳዮች ላይ ወደ ፍርድ ቤት ለማምራት ወስኗል፡፡ አንደኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፓርቲውን ፕሬዚዳንት አቶ እስክንድር ነጋ ጨምሮ ሌሎች አባላትን ‹‹በዕጩነት አይቀርቡም›› በማለት የወሰነውን የመጨረሻ ውሳኔ በተመለከተ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ የሚደረገው ምርጫ ጠቅላላ ምርጫው  ግንቦት 28 2013 ዓ.ም. ሰኔ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. ከተካሄደ በኋላ በሳምንቱ እንዲካሄድ የተወሰነውን በመቃወም እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

‹‹እነ አቶ እስክንድር ነጋ ያላግባብ ለእስር የተዳረጉት የፈጸሙት አንዳች የሚያስጠይቅ ነገር ኖሮ ሳይሆን፣ ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ እንዳይሳተፉ ፖለቲካዊ ውሳኔ ተሰጥቶ እንደሆነ እናምናለን፤›› ያለው የፓርቲው መግለጫ፣ ‹‹ምርጫ ቦርድ እነ አቶ እስክንድር ነጋ ለስድስተኛ አገራዊ ምርጫ በባልደራስ ፓርቲ ስም ዕጩ ሆነው እንዳይቀርቡ ያስተላለፈው ውሳኔ፣ የፓርቲውን አመራሮች ከገዥዎች ጋር ተደርቦ እንደ ማጥቃት እንቆጥረዋለን፤›› ብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሚደረገው ምርጫ በሁለት የተለያዩ ቀናት መሆኑ፣ የኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ አገር አቀፍ ምርጫ በአንድ ቀን ይካሄዳል ብሎ ያስቀመጠውን ሕግ የሚያፋልስ በመሆኑ፣ የሕጉን መጣረስ ባልደራስ የማይቀበል እንደሆነ አቶ ሔኖክ አስረድተዋል፡፡ ‹‹የተቋቋሙ ልዩ የምርጫ ችሎቶች ከተፅዕኖ በነፃ ሁኔታ ፍትሕ ይሰጣሉ? ወይስ አይሰጡም?›› የሚለውን ጉዳይ በስፋት ለመፈተሽ ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት እንሚወስዱት አስታውቀዋል፡፡

የባልደራስ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊና የምርጫ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ አቶ ጌታነህ ባልቻ (ኢንጂነር)፣ ‹‹ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ነፃና ገለልተኛ ነው ወይ?›› የሚሉት ጥያቄዎች እንዲመለሱለት ባልደራስ ለቦርዱ ጥያቄ አቅርቦ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ይህም ከምርጫ አስፈጻሚዎች ገለልተኝነት ጋር በተያያዘ፣ በአዲስ አበባ በሁለት የተለያዩ ቀናት እንደሚከናወን የተወሰነውን ውሳኔ፣ እንዲሁም በእስር ላይ የሚገኙ የፓርቲ አመራሮች ዕጩ ሆነው እንዳይቀርቡ የተከለከለውን በተመለከተ እንደነበር አስታውቀዋል፡፡

‹‹ቦርዱ በ2007 ዓ.ም. ከመርጋ በቃና (ፕሮፌሰር) አመራር ኮምፒዩተራዝድ ከመሆን ባለፈ፣ ያለው ፖለቲካዊ ጫና ተቋቁሞ ወገንተኝነቱን ለእውነት ብቻ እንደሆነ ለማሳየት ተስኖታል›› የሚለው የባልደራስ መግለጫ፣ ‹‹በእነ አቶ እስክንድር ነጋ ዴሞክራሲያዊ መብት መገፈፍ ላይ ከገዥው ፓርቲ እኩል ምርጫ ቦርድ የወሰደው አቋም፣ ቦርዱን እንደ ተቋም የማውረድ ብቻ ሳይሆን፣ በአገሪቱ ለሚከሰተው ችግር ቦርዱ ራሱ አንድ ምንጭ እንደሆነ ባልደራስ ያምናል፤›› ሲል ይከሳል፡፡

የፓርቲውን ከከፍተኛ አመራሮች በምርጫ ዕጩነት ስለማስመዝገብ ጥያቄ ጋር በተገናኘ ያስመዘገቧቸውን ዕጩዎች በተመለከተ መግለጫ ሳይሰጡ እንደቆዩ ያስታወቁት ጌታነህ (ኢንጂነር)፣ ሆኖም ፓርቲው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 23 ዕጩዎች፣ እንዲሁም 138 ዕጩዎችን ለክልል ምክር ቤት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...