Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናእነ አቶ ስብሃት ነጋ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በመናድና በሽብርተኝነት ሊከሰሱ ነው

እነ አቶ ስብሃት ነጋ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በመናድና በሽብርተኝነት ሊከሰሱ ነው

ቀን:

  • አዲስ ዓለም ባሌማ ሲካተቱ ሦስት ተጠርጣሪዎች በዋስ ተለቀቁ

ጥቅምት 24 ቀን 2013 .. በሰሜን ዕዝ ላይ በተከፈተው ጦርነትና ከደረሰው ጥቃት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራቸው በተጠናቀቀው በእነ አቶ ስብሃት ነጋ (16 ተጠርጣሪዎች) ላይ፣ ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል መናድና በሽብርተኝነት እንደሚከሰሱ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡

ዓቃቤ ሕግ ስለክሱ ዓይነት የተናገረው፣ መጋቢት 2 ቀን 2013 .. ለፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት፣ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን በተጠርጣሪዎቹ ላይ ሲያካሂድ የከረመውን ምርመራ አጠናቆ፣ የምርመራ መዝገቡን እንዳስረከበው ለማረጋገጥ በቀረበበት ወቅት ነው፡፡

ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ቀጥሮ የነበረው መርማሪ ቡድኑ ተጠርጣሪዎቹን የወንጀል ተሳትፎ ለይቶ እንዲያቀርብና ቀሩኝ ያላቸውን ምርመራዎች ሠርቶ እንዲያቀርብ የነበረ ቢሆንም፣ ቡድኑ ግን ምርመራውን እንዳጠናቀቀና የምርመራ መዝገቡን ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ማስረከቡን ተናግሯል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ዓቃቤ ሕግም የምርመራ መዝገቡን መቀበሉን አረጋግጦ፣ መዝገቡን ሲመረምረው፣ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ያሰባሰባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በፍርድ ቤት ማረጋገጥ እንዳለበት ውሳኔ ላይ በመድረሱ፣ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ቁጥር 38 80 እና ተከታዮቹ ድንጋጌ መሠረት ቅድመ ምርመራ ፍርድ ቤት ለማቅረብ መዝገብ ቁጥር 220866 መዝገብ መክፈቱን ለፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ያስረከበውን የምርመራ መዝገብ ሲመረምረው፣ የቀድሞ ትግራይ ክልል ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት / ህሪቲ ምሕረተ አብ፣ የደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (/) አማካሪ የነበሩት አቶ ወልደ ጊዮርጊስ ደስታና አቶ ዓምደ ማርያም ተሰማ በተባሉበት ተጠርጣሪዎች ላይ ለክሱ የሚያበቃ የወንጀል ድርጊት እንዳላገኘባች ገልጾ፣ በበቂ ዋስ ቢለቀቁ እንደማይቃወም ተናግሯል፡፡

ሌሎቹ ተጠርጣሪዎች አቶ ስብሃት ነጋ፣ አባዲ ዘሙ (አምባሳደር) ሰለሞን ኪዳኔ (/) / ቅዱሳን ነጋ፣ አቶ ቴዎድሮስ ሐጎስ፣ አቶ ተክለ ወይኒ አሰፋ፣ አቶ ገብረ መድኅን ተወልደ፣ አቶ ዓባይ ወልዱ (አምባሳደር) አብርሃም ተከስተ (/) ረዳዒ በርሄ (/) ሙለታ ይርጋ (/) / ኪሮስ ሐጎስ፣ አቶ ዕቁባይ ታፈረ፣ አቶ ጌታቸው ተፈሪ፣ አቶ ንጋቱ አለፎም፣ በሌላ የምርመራ መዝገብ ከሁሉም ተጠርጣሪዎች ቀደም ብለው በአዲስ አበባ በቁጥጥር ሥር የዋሉትና በቀድሞ ምርመራ መዝገብ የተካተቱት አዲስ ዓለም ባሌማ (/) ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል በመናድና በሽብርተኝነት ስለሚከሰሱ፣ ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ትዕዛዝ እንዲሰጥለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

የእያንዳንዱን ተጠርጣሪ የወንጀል ተሳትፎ በሚመለከት ዓቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ ማስረዳት ሲገባው፣ የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሳይፈጸም መቅረቱንና አግባብ የሚሆነውም እንደ ቀዳሚነቱ ትዕዛዙን ፈጽሞ የእንዳንዱን ተጠርጣሪ የወንጀል ተሳትፎ በመለየት ማቅረብ እንደነበረበት በመግለጽ፣ የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ተቃውሟቸውን ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል፡፡ ችሎቱ በተጠርጣሪዎቹ ላይ በቂ ማስረጃ ስለመቅረቡ ማረጋገጥ እንዳለበት፣ በደንበኞቻቸው ላይ የቀረበው የምርመራ ውጤት በተሳትፎ ደረጂ እንደ ድርጊት ስለመፈጸሙ እንዳልሆነ፣  በጡረታ የተገለሉና ወታደራዊ ዕውቀትም የሌላቸው መሆናቸውንም አክለዋል፡፡

ዓቃቤ ሕግ ለጠበቆቹ በሰጠው ምላሽ፣ አቶ ስብሃት በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት ‹‹ጥገኛ መንግሥት ነው›› በማለት በትግራይ ያለው ኮማንዶ እንዲጠናከር አስፈላጊውን ምክር ያደርጉና ትዕዛዝ ይሰጡ እንደነበር፣ አባዲ ዘሙ (አምባሳደር) አቶ ቴዎድሮስ ሐጎስና አቶ ገብረ መድኅን ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ፣ ‹‹ልዩ ኃይሉ ምን ይበላል?›› በማለት ለሦስት ወራት የሚሆን ቀለብ (ምግብ) ሲያዘጋጁ እንደነበር፣ አቶ ተክለ ወይኒ ከኤፈርት 50 ሚሊዮን ብር ይዘው ለልዩ ኃይሉ ድጋፍ ለማድረግ ሲዘዋወሩ እንደነበር፣ ሰለሞን (/) አብረው እንደነበሩና / ቅዱሳንም ወጣቱ እንዲዘምት ሲቀሰቅሱ እንደነበር በመግለጽ ተሳትፏቸውን መለየቱን አስረድቷል፡፡

ሌላው ጠበቆቹ ያነሱት ጥያቄ ለአቶ ስብሃት የታዘዘው ሕክምና አለመፈጸሙን ሲሆን፣ ዓቃቤ ሕግ ለዚህም ምላሽ ሰጥቷል፡፡ እሳቸውን (አቶ ስብሃትን) የሚያክሙት ሐኪም መሣሪያ ነቅለውና ማረሚያ ቤት በመውሰድ ማከም እንደማይችሉ በመግለጻቸው ትዕዛዙ እንዳልተፈጸመ ሲያስረዳ፣ ፍርድ ቤቱ ሐኪሙ ፍርድ ቤት ቀርቦ ቃለ መሃላ በመፈጸም ሕክምና እንዲሰጥ ትዕዛዝ መስጠቱን አስታውሷል፡፡ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ፣ ተጠርጣሪዎቹ በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

በሌላ የምርመራ መዝገብ የነበሩት የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀድሞ አፈ ጉባዔ / ኬሪያ ኢብራሂም ፍርድ ቤት ባይቀርቡም፣ / ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር ግን ቀርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ / ኬሪያ ለምን እንዳልቀረቡ ሲጠይቅ፣ / ኬሪያን ፖሊስ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 28 ድንጋጌ መሠረት [‹‹ማለትም በራስ ዋስትና በማስፈረም››] መለቀቃቸውን አስረድቷል፡፡ / ሙሉ ግን በወንጀል ስለሚከሰሱ አዲስ በከፈተው የቀዳሚ ምርመራ ቁጥር 220866 መዝገብ መካተታቸውን አክሏል፡፡ በመሆኑም ሌሎቹ ተጠርጣሪ የነበሩት / ህሪቲ፣ አቶ ወልደጊዮርጊስና አቶ ዓምደማርያም እንዳንዳቸው 30 ሺሕ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ መዝገብን ዘግቷል፡፡      

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...