Saturday, December 3, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ይድረስ ለሪፖርተርጃንሜዳ ከ362 ቀናት መጠቀሚያነት ወደ ሦስት ቀናት ለመቀየር መጣጣር ተገቢ ነውን?

  ጃንሜዳ ከ362 ቀናት መጠቀሚያነት ወደ ሦስት ቀናት ለመቀየር መጣጣር ተገቢ ነውን?

  ቀን:

  ጃንሜዳ ተብሎ የሚታወቀው ሜዳ ከረዥም ዓመታት ጀምሮ የተለያዩ የኅብረተሰቡ ክፍሎች ሲጠቀሙበት የኖረ ቦታ ነው፡፡ በዚህ ሥፍራ 362 ቀናት የስፖርት ኮሚሽን፣ ሦስት ቀናትን ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ይጠቀምበታል፡፡

   ይኼንን ደብዳቤ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ዋነኛው ምክንያት በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ አንዳንድ ግለሰቦች ቦታው ለቤተ ክርስቲያቱ ካርታ ተሠርቶላት ሊሰጣት ይገባል የሚል ሐሳብ እየሰነዘሩ ያሉ በመሆኑ ጉዳዩ ትኩረት እንዲያገኝ ሐሳባችንን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

  በመሠረቱ ከላይ እንደገለጽነው በዓመቱ ውስጥ 362 ቀናት የተለያዩ የእግር ኳስ ክበባት፣ የአትሌቲክስ ተወዳዳሪዎች፣ የመረብ ኳስ ክበባት፣ አዳዲስና አንጋፋ አትሌቶች፣ ታዳጊ ሕፃናትና ወላጆች፣ ወዘተ ከመርካቶ እስከ ፈረንሣይ ለጋሲዮን፣ ከሽሮ ሜዳ እስከ አራት ኪሎ፣ ከቤላ እስከ ቀበና ያሉ ከጠዋቱ አሥራ ሁለት ሰዓት

  ጀምሮ በአውቶብስና በሌሎች ተሽከርካሪዎች፣ እንዲሁም በእግራቸው እየመጡ ሲለማመዱና ዓመታዊ ውድድር ጭምር ሲያደርጉ የሚውሉበት ነው፡፡

  በአገራችን በወጣቱ ላይ በሰፊው ከሚሰነዘረው ትችት ዋነኛው ‹‹አልባሌ ቦታ ይውላሉ›› ነው፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ መንግሥት መሥራት ያለበት እንደ ጃንሜዳ ያሉትን የማዘውተሪያ ሥፍራዎች ማስፋፊያ እያደረገላቸው እንዲጠቀሙበት ማድረግ እንጂ፣ በዓመት ሦስት ቀን ብቻ ለሚገለገልበት ቤተ ክርስቲያን ቢሰጥ በሒደት ወጣቱ ወደዚያ ግቢ እንዳይገባና እንዳይገለገል ሊያደርግ ይችላል የሚል እምነት አለን፡፡ 

  በመሆኑም የስፖርት ኮሚሽንና አዲስ አበባ ስፖርት ቢሮ ልዩ ትኩረት ከመስጠት ተጨማሪ የመፀዳጃ ቤቶችንና መታጠቢያ ቤቶችን በመሥራት፣ እንዲሁም ለረዥም ጊዜ በሜዳው ላይ ተዝረክርከው የሚገኙ ‹‹ቁራሌዎችን›› በማስወጣት ለወጣቱና ለታዳጊ ትውልድ ተገቢ አገልግሎት እንዲያገኙ እንዲያደርግ በታላቅ ትህትና እንጠይቃን፡፡ ዛሬ ለወጣቱ ጥሩ መሠረት ከተጣለ የነገ ኃላፊነት የሚሰማው ጥሩ ዜጋ ይሆናል፡፡
  (ዓለማየሁ ….. ከአዲስ አበባ)

  * * *
  የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበር ኮንፌዴሬሽን ለላብ 
  አደሩ ምን እየሠራ ነው?

  1.    ኢሠማኮ ከደሃው ሠራተኛ ላይ ገንዘብ ከመልቀም በዘለለ ለዚህ ሠራተኛ ያመጣለት ለውጥ የለም፡፡ 

  2.    ለመንግሥት ሠራተኞች በሕዝብ ገንዘብ የሚገነባ የጋራ መኖሪያ ቤት ቅድሚያ ለመንግሥት ሠራተኛ ሲሰጥ ለግሉ አይሰጥም፡፡ ይኼ አግባብ ነው? የግሉ ሠራተኛ ለጎረቤት አገር ነው የሚሠራው? በዚህ ላይ ኢሠማኮ ምን አደረገ? 

  3.    ሚኒመም ዌጅ ይኼው እስካሁን ሊከበር አልቻለም፡፡ በአዋጅ የተከበረው መብታችን ኢሠማኮም ተኝቷል፡፡ 
  4.    የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች በአንድ ሠራተኛ ከሚቀበሉት 80 በመቶ ለሠራተኛው እንዲከፍሉ የኤጀንሲዎች መመርያ ወጥቶ ሳይከበር ይኼው ዓመት አለፈው፣ ኢሠማኮ ምን አደረገ?

  5.    በአሠማኮ ሥር 9 የፌዴሬሽኖች አሉ፡፡ የአመራር ምርጫ ግልጽነት የጎደለው ነው፡፡ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ተወካዮች ምርጫውን እንዳይታዘቡ ይደረጋል፡፡ ለምን? 

  6.    ከደሃው ሠራተኛ አባላት የሚሰበሰበው የገንዘብ መዋጮም ብክነት አለ፡፡ የኢሰማኮ ንብረቶች፣ ሆቴሎችና ዋርካ ሆቴል፣ ወዘተ ሁልጊዜ እየሠሩ እንዴት የሠራተኛ ደመወዝ መክፈል አቃታቸው? ሁልጊዜ ድጎማ ነው፡፡ ሰው የራሱ ሕንፃ ላይ ሠርቶ እንዴት ይከስራል? ከግለሰብ ተከራይተው አትርፈው የሚበለፅጉና የሚያድጉ ባለበት አገር፡፡ 

  7.    ዘመናዊነትን ጠልነት በስንት ውትውታ ፌስቡክ ገጽ ከፈቱ፡፡ ሁልጊዜ የሐዘን መግለጫ ነው፡፡ ለሠራተኛው መደራጀትና የአዋጆች መመርያዎች ማስገንዘቢያ የተለያዩ ጥቆማዎች ግን የሉም ከግልና ከመንግሥት የኤሌክትሮኒክ መገናኛ ብዙኃን ጋር በትብብር መሥራት ሲገባ ምንም የለም፡፡ ለምን?

  8.    ኢሠማኮ የኢትዮጵያ በሚሊዮን የሚቆጠረውን የግል ሠራተኞች እንደሚወከሉ በመንግሥት ተገቢ ክብርና ተሰሚነት ሊያገኝ ሲገባ፣ መንግሥት የዝንብ ያህል አያከብረውም፡፡ ለዚህ ማሳያ ጥቅምት 18 ለኤጀንሲ ሠራተኞች በአዋጅ መሠረት ማስፈጸሚያ ሆኖ በወጣው መመርያ 80 በመቶ ክፍያን መንግሥት በ15 ቀን ውስጥ ካላስከበረ አገር አንቀጥቅጦ ሠልፍ እጠራለሁ ሲል፣ የመንግሥት አካላት እስኪ እናናግርህ እንኳን አላለውም፡፡ ከንቀት ይመነጫል፡፡ ኢሰማኮም ቃሉን አክብሮ ቢከለከል እንኳን ለአፉ ሠልፉን ልጥራ አላላም፡፡ የኤጀንሲ ሠራተኞች በደልም እንደቀጠለ ነው፡፡ 

  አመሠግናለሁ የሠራተኛ ማኅበር አባልና በኢሰማኮ ጠንካራ ተቋም ሆኖ አለመውጣት ከሚያዝኑና ከሚቆጩ ላብ አደሮች አንዱ ነኝ፡፡ እባካችሁ ይህ ጥያቄ የሚሊዮኖች ላብ አደሮች ጥያቄ ነው፡፡ እባካችሁ ጠይቁልን፡፡ 
  (ከፍፁም ዘበርጋ፣ አዲስ አበባ)

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...