Friday, December 8, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ለሞባይል ስልኮች የመድን ሽፋን መስጠት ጀመረ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ለሞባይል ስልኮች የመድን ሽፋን የሚሰጥ አዲስ አገልግሎት መጀመሩን ይፋ አደረገ፡፡

ኢንሹራንስ ኩባንያው፣ ማንኛውም የሞባይል ተጠቃሚ ሞባይሉ ቢጎዳ ወይም ቢጠፋ ካሳ የሚያገኝበትን አዲስ አገልግሎት ለሕዝብ ያስተዋወቀው ሐሙስ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም. ነው፡፡

‹‹ለሞባይሌ›› የሚል ስያሜ ባለው አገልግሎት ማንኛውም ሰው በቀን አንድ ብር በመክፈል ለሞባይሉ ኢንሹራንስ መግባት ይችላል፡፡

የሞባይል ደንበኞች ከአየር ሰዓታቸው እየቀነሱ በመክፈል አገልግሎቱን እንዲያገኙ የተመቻቸ ሲሆን፣ አገልግሎቱም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በተደረገ ስምምነት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

ደንበኛው 813 ላይ በመደወል የመድን ሽፋኑን ማግኘትም ይችላል፡፡ በቀን አንድ ብር በማሰብ የዓመቱን አንድ ጊዜ ለመክፈል የሚቻልበት አሠራርም አለው፡፡

በኢንሹራንስ ሽፋኑ አገልግሎት አንድ ሰው ሞባይሉ ከጠፋበት ያንን ሞባይል የሚተካ ካሳ ያገኛል፡፡ ነገር ግን የጠፋው ስልክ በምንም ሁኔታ አገልግሎት ላይ የማይውል ይሆናል፡፡ ይህም የሚደረገው ጠፋ የተባለው ስልክ ፈፅሞ አገልግሎት እንዳይሰጥ በማድረግ ነው፡፡

የተሰበረ ስልክም ኒያላ ኢንሹራንስ ስምምነት ከተፈራረመባቸው የሞባይል ማዕከሎች መጠገን ይችላል፡፡ ይህንን አገልግሎት ለየት የሚያደርገው አንድ የጠፋ ስልክ ቢሰረቅ ሌላ ሰው እንዳይጠቀምበት የሚያደርግ በመሆኑ ነው፡፡

ኒያላ ኢንሹራንስ በዚህ አገልግሎት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደንበኞችን ማፍራት እችላለሁ የሚል እምነት ያለው ሲሆን፣ አገልግሎቱን ለመጀመር የሚያስችለውንም ፈቃድ ከብሔራዊ ባንክ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች