በዓለም አቀፍ ደረጃ የጤና ሥጋትና ወረርሽኝ ከሆነው ኮቪድ-19 ኅብረተሰቡን ለመታደግ የሚያስችል ክትባት፣ በአዲስ አበባ ከተማ ቅዳሜ መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም. መከተብ ተጀመረ፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 እፎይታ ጤና ጣቢያ በመገኘት፣ የኮቪድ-19 የመጀመርያ ዙር ክትባትን በይፋ ያስጀመሩት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ሲሆኑ፣ ቀዳሚው ተከታቢ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዮሐንስ ጫላ (ዶ/ር) ሆነዋል። በሥራቸው ምክንያት ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሊጋለጡ የሚችሉት የሕክምና ባለሙያዎችም በዕለቱ ተከትበዋል፡፡
በኮቫክስ አማካይነት ወደ ኢትዮጵያ የገባው የኮቪድ-19 ክትባት፣ በአዲስ አበባ በሚገኙ የጤና ተቋማት ለሚሠሩ የሕክምና ባለሙያዎች፣ በዕድሜና በተጓዳኝ በሽታ ተጋላጭ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሰጥ የጤና ቢሮ ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ 2.2 ሚሊዮን የመጀመሪያው ዙር ክትባት፣ ከኮቫክስ ዓለም አቀፍ ጥምረት ባለፈው ሳምንት መረከቧ ይታወሳል፡፡ ክትባቱ በቅድሚያ የሚሰጣቸው ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ የጤና ባለሙያዎችና ሠራተኞች፣ ዕድሜያቸው ከፍ ያሉና ተጓዳኝ ሕመም ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሆን የጤና ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቱ በክልሎች፣ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተሞች መጀመሩ ታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ የኮቪድ-19 የመጀመርያ ዙር ክትባት ተጀመረ
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -