የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን አስመልክቶ ባወጣው ሳምንታዊ ንፅፅር ላይ ያስታወቀው፡፡ ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 5 ቀን 2013 ዓ.ም. በነበሩት ሰባት ቀናት 121 ሰዎች በበሽታው ሕይወታቸውን ማጣታቸውን የገለጸው ኢንስቲትዩቱ፣ ምርመራ ከተደረገላቸው 49,326 ሰዎች መካከል 9,329 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፣ ካለፉት ሳምንታት ጋር ሲነፃፀር በ32 በመቶ መጨመሩንም አውስቷል፡፡