Tuesday, March 5, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየአዲስ አበባን ጥንታዊ ሕንፃ የተረከበው የጣይቱ ባህልና ትምህርት ማዕከል

የአዲስ አበባን ጥንታዊ ሕንፃ የተረከበው የጣይቱ ባህልና ትምህርት ማዕከል

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአራዳ ምድብ ችሎት ይጠቀምበት የነበረውን የቢትወደድ ኃይለ ጊዮርጊስ ወልደ ሚካኤል መኖሪያ ቤትን መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ለጣይቱ ባህልና ትምህርት ማዕከል አስረክቧል።

ጣይቱ የባህልና ትምህርት ማዕከል፣ በአንጋፋዋ ከያኒት ዓለም ፀሐይ ወዳጆ ከሁለት አሠርታት በፊት በአሜሪካ ተቋቁሞ በኪነ ጥበብ ላይ ሲሠራ የነበረ ነው፡፡

በቅርስነት የተመዘገበው ነባር ሕንፃ ለጣይቱ ባህልና ትምህርት ማዕከል ያስረከቡት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ በሥነ ሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት፣ የትናንቱ ትውልድ ያስቀመጣቸውን መልካም አሻራዎች እንዳይደበዝዙ፣ ከነጥንታዊነታቸው፣ ከነታሪካቸውና ከነፋይዳቸው ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ በአግባቡ መጠበቅና መንከባከብ ይገባል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በአዲስ አበባ የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶች በቅርስነታቸው ብቻም ሳይሆን፣ በዘመን ተሻጋሪነታቸው ታሳቢ ተደርገው መጠቀምና መንከባበከብ እንደሚገባ ያሳሰቡት ምክትል ከንቲባዋ፣ ከተማዋን እንደስሟ አበባ ለማድረግ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ፣ዕውንነቱም የባህል ማዕከላትን ማስፋፋት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መካነ ቅርሱን ለማደሻ የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያሠራጨው መረጃ ያመለክታል፡፡

‹‹ጣይቱ የባህልና የትምህርት ማዕከል የረጅም ጊዜ ጥረቱ እውን ሆነ። በአዲስ አበባ ከተማ በታሪካዊነቱ ከፍተኛ ሥፍራ የሚሰጠውን የቀድሞ ማዘጋጃ ቤት ተሰጥቶት የኢትዮጵያን ባህል ጥበብና ታሪክ ለትውልድ የማስተላለፍ ኃላፊነቱን ተረክቧል። የዚህ ታሪካዊ ተግባር አካል በመሆን ትብብሮን እንዲያሳዩን እንጠይቃለን፤›› ብላ፣ ዕውቋ ከያኒት ዓለም ፀሐይ ወዳጆ አስቀድማ ባስተላለፈችው ጥሪ መሠረት በርክክቡ ዕለት በተከናወነው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት 11.7 ሚሊዮን ብር መገኘቱና ቃል መገባቱ ታውቋል፡፡

በሕንፃው ርክክብ ሥነ ሥርዓት ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኰንን፣ ሚኒስትሮችና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

የቢትወደድ ኃይለ ጊዮርጊስ ወልደ ሚካኤል መኖሪያ ቤት ከ117 ዓመታት በፊት መገንባቱ ይታወቃል፡፡

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ 1900 .. ሚኒስትሮችን ሲሾሙ ያኔነጋድራስየነበሩት ቢትወደድ ኃይለ ጊዮርጊስን የንግድና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲያደርጓቸው፣ በልጅ ኢያሱ ዘመን የመጀመርያው ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ። ለአዲስ አበባ ሁለተኛው ከንቲባዋ ሆነው አገልግለዋል።

በማዘጋጃ ቤትነት፣ በቴአትርና ሙዚቃ ክፍል ማዕከልነት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው  ሕንፃ እስከ ቅርቡ የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያራዳ ምድብ ችሎት ነበረ። መጎሳቆሉንና የመፍረስ ሥጋት ላይ መውደቁን የተመለከተውና ፍርድ ቤቱ ወደ ሌላ ሥፍራ ተዘዋውሮ እንደሌሎቹ ጥንታዊ ሕንፃዎች ላስተዳድረው ሲል ለሁለት አሠርታት የጮኸው የኢትዮጵያ ቅርስ ባለ አደራ ማኅበር ነበር።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...