Sunday, September 25, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  [የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ዘወትር እንደሚያደርገው ወቅታዊ ሁኔታዎችን የተመለከተ ሪፖርት እያቀረበ ቢሆንም ሚኒስትሩ ምርጫን በተመለከተ የቀረበላቸው መረጃ ላይ ትኩረታቸውን አድርገው ማብራሪያ እየጠየቁ ነው] 

  • ምዕራባውያኑ የጀመሩትን ጫና በዚህ ሳምንትም አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡
  • ቆይ. . . እሱን አቆየው፡፡
  • በምርጫው ለመወዳደር የቀረቡት ስንት የግል ዕጩዎች ናቸው ያልከኝ?
  • ይፋ በተደረገው ጊዜያዊ መረጃ መሠረት 125 ዕጩዎች ተመዝግበዋል፡፡ 
  • 125 ነው ያልከው? 
  • አዎ። ተቋሙ ያወጣው ጊዜያዊ መረጃ እንደዚያ ነው የሚለው፡፡
  • በግል 125 ዕጩዎች? 
  • እንደዚያ ነው። ፖለቲካዊ ትርጉሙም ቀላል አይደለም።
  • ምንድነው?
  • ማኅበረሰቡ በብሔር ተደራጅቶ ፖለቲካ ማራመድ እንደሰለቸው ያሳያል። 
  • እኛም የፓርቲያችንን ስያሜ ብልፅግና ያልነው ይህ እንደሚመጣ ቀድመን ስለተመለከትን ነው።
  • የግል ዕጩዎቹ መብዛት ሥጋትም ሊሆን ይችላል።
  • እንዴት?
  • በፓርቲ ቢደራጁ ፈተና ነው ለማለት ነው።
  • አልገባኝም?
  • የግል ዕጩዎቹ ቢያሸንፉ ከሁለቱ ክልሎች ቀጥሎ በፓርላማ ብዙ መቀመጫ የሚኖራቸው እነሱ ይሆናሉ።
  • እንደዚያ ነው። በል ከጀርባቸው ማን እንዳለ ይጣራ፡፡
  • ጥሩ። በእኛ በኩል ያሉትም ጉዳይ ይጣራ?
  • በኛ በኩል ምን አለ?
  • እኛ ያቀረብናቸው አንዳንድ ዕጮዎች አቋም አልታወቀም።
  • እንዴት?
  • በእኛ ፓርቲ በኩል ተመዝግበው ሲያበቁ የሚወዳደሩት በግል እንደሆነ እየገለጹ ነው። 
  • ምን ማለት ነው ይኼ?
  • ነገሩ ድብልቅል ያለ ነው።
  • መረጃው ጊዜያዊ ነው ያልከኝ አይደል?
  • አዎ። 
  • ጊዜያዊነቱ ሳያበቃ ጀርባቸው ይጣራ!

  [ክቡር ሚኒስትሩ በሌላ ስም የከፈቱትን የፌስቡክ ገጽ እንደከፈቱ ቀድሞ በመጣላቸው መረጃ ተናደው ሳለ የሥራ ባልደረባ ወዳጃቸው ደወለ]

  • ክቡር ሚኒስትር እንዴት አሉ? 
  • ደህና ነኝ እኔ። ምን እሆናለሁ ብለህ ነው።
  • ከአባባልዎት ግን ደህና አይመስሉም ወይም ያናደደዎት ነገር ያለ ይመስላል?
  • ያናድዳል እንጂ እንዴት አልናደድም።
  • ምን ገጠምወት? 
  • በስንት ጩኸት ከእስር ይፈቱና አሁንም አርፈው አይቀመጡም፡፡ አሁን እስኪ በኛ ላይ ይፈረዳል?
  •  ምንድን ነው?
  • አላየኸውም እያለ ያለውን?
  • ማን ነው? 
  • ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመናድ ክስ የቀረበበት ሰውዬ ነዋ፡፡
  •  ምን አለ?
  • በስንት ጩኸት በዋስ ቢለቀቁ ረቂቅ ሕገ መንግሥት በመጽሐፍ መልክ እያሳተሙ ነው።
  • እሱን ነው እንዴ? አልሰሙም ማለት ነው?
  • ምን?
  • ፍርድ ቤቱ ከክሱ ነፃ አደረጋቸው እኮ፡፡
  •  እንደዚያ ከሆነ ያሳትሙ፡፡
  • የፍትሕ ሥርዓቱ ከፈቀደላቸው ምን ይደረጋል። 
  • ልክ ነው። የፍትሕ ሥርዓቱ ከፈቀደላቸው ያሳትሙ!

  [አምሽተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው የገቡት ሚኒስትሩ ቀኑን ያልሰሙት የታክሲ አሽከርካሪዎች አድማን የተመለከተ ዜና በቴሌቪዥን መስኮታቸው እየተላለፈ ነው። ባለቤታቸውም አብረው እየተከታተሉ ነው]

  • መቼ ነው ደግሞ እንዲህ ያደረጉት?
  • ነዋሪው ትራንስፖርት አጥቶ ሲቸገር መች ታያላችሁ እናንተ?
  • 97ቱም ምርጫ እነሱ ነበር የቀሰቀሱብን. . .
  •  እናንተ ስለ ሥልጣን ከመቀጠል በላይ ስለነዋሪው የምትጨነቁት መቼ ነው?
  • ያኔ እነሱ በቀደዱት ነው ጅብ የገባው. . . አሁንስ ቀልድ የለም፡፡ 
  • ምን ልታደርጉ? 
  • እናስገባቸዋለን፡፡ 
  • ስንቱን አስገብቶ ይቻላል?
  • ሳይቻል ሲቀር መላ አለን፡፡ 
  • ምን?
  • ምሕረት እያደረግን ማስወጣት፡፡
  • ታዲያ እንደዚያ አትለኝም እንዴ?
  • ምን ልበል?
  • ውኃ ቅዳ ውኃ መልስ፡፡ 

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  የአውሮፓ ኅብረት ተወካይ በተመድ ጉባዔ ‹‹የትግራይ መንግሥት›› በማለት ላደረጉት ንግግር ማስተካከያ እንዲደረግ ኢትዮጵያ ጠየቀች

  በስዊዘርላንድ ጄኔቭ እየተካሄደ በሚገኘው 51ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ)...

  መንግሥት የሥራ ግብር ምጣኔን እንዲቀንስ ተጠየቀ

  የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) መንግሥት የሠራተኛውን የኑሮ ጫና...

  የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የድጎማ በጀት ለፖለቲካ ሥራ ማስፈጸሚያ እንደሚውል የሚያሳይ ሪፖርት ቀረበ

  ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚደረግ የበጀት ድጎማ ከመደበኛው ሥራ ይልቅ ከዋናው...

  ብሔራዊ ባንክ ለፋይናንስ ተቋማት ለሚሰጠው ፈቃድና አገልግሎት እስከ አንድ ሚሊዮን ብር ሊያስከፍል ነው

  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአገሪቱ የፋይናንስ ተቋማት ለሚሰጠው የፈቃድ፣ የብቃት...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  በኢትዮጵያ ላይ የቀጠለው የምዕራባውያን ጣልቃ ገብነት

  ምዕራባውያን አገሮች በኢትዮጵያ ላይ ጠንካራ ጫና ማሳደራቸውን ቀጥለዋል፡፡ በዲፕሎማሲም...

  የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የድጎማ በጀት ለፖለቲካ ሥራ ማስፈጸሚያ እንደሚውል የሚያሳይ ሪፖርት ቀረበ

  ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚደረግ የበጀት ድጎማ ከመደበኛው ሥራ ይልቅ ከዋናው...

  መንግሥት የሥራ ግብር ምጣኔን እንዲቀንስ ተጠየቀ

  የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) መንግሥት የሠራተኛውን የኑሮ ጫና...

  የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የአመራሮች ምርጫና ቀጣይ ዕቅዶቹ

  የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ሲጠበቅ የነበረውን...

  በ15 ቢሊዮን ብር የተመዘገበ ካፒታል የማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎቱን ያሻገረው ስንቄ ባንክ ሥራ ጀመረ

  ከማክሮ ፋይናንስ ተቋምነት ወደ ባንክ አገልግሎት ከተሸጋገሩ አምስት የማክሮ...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [አብሮ የሚኖረው ወንድማቸው በተደጋጋሚ እየደወለ መሆኑን የተመለከቱት ክቡር ሚኒስትሩ በስተመጨረሻ የእጅ ስልካቸውን አንስተው ሃሎ አሉ]

  ሃሎ... ስብሰባ ላይ ሆኜ ነው ያላነሳሁት ...በሰላም ነው? ሰላም ነው። ልንገርህ ብዬ ነው... ምንድነው ምትነግረኝ?  ዛሬ አልመጣም፣ እንዳትጠብቀኝ ልነግርህ ነው። ምን ማለት ነው? ወደ አገር ቤት ልትመለስ ነው?  እንደዚያ...

  [ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጋር ደውለው ልማታዊ ወጣቶች ያቀረቡት አቤቱታ በአፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጠው እያሳሰቡ ነው]

  እየደገፉን ያሉ አንዳንድ ልማታዊ ወጣቶች በከተማ አስተዳደሩ ላይ ቅሬታ አቅርበዋል። እኛ ላይ?  አዎ!  ቅሬታቸው ምንድነው? ለምን ለእኛ አላሳወቁንም? የሚሰማቸው ስላላገኙ ነው ቅሬታቸውን ወደ እኛ ይዘው የመጡት።  እስኪ ነገሩን አጣራለሁ...

  [ክቡር ሚኒስትሩ አዲሱ ዓመት ሰላም ይዞ ይመጣል የሚል ተስፋቸውን ለባለቤታቸው እየገለጹ ነው]

  መንግሥት አሁንም እጁን ለሰላም እንደዘረጋ ነው። ነገር ግን በዚያኛው ወገን ከጦርነት በቀር ሌላ ፍላጎት የለም። ከዚህ አዙሪት በቀላሉ መውጣት ይቻላል ብለህ ታምናለህ? አዲሱ ዓመት ሰላም ይዞ...