Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአሜሪካው ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያና በሌሎች ቀጣናዊ ቀውሶች ላይ ተመድ ዕርምጃ መውሰድ አለበት አሉ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያና በሌሎች ቀጣናዊ ቀውሶች ላይ ተመድ ዕርምጃ መውሰድ አለበት አሉ

ቀን:

  • በትግራይ ክልል ቀውስ ላይ ያላቸውን ሥጋት ለመግለጽ መልዕክተኛ ሊልኩ ነው

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባይደን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የፀጥታ ምክር ቤት፣ቋሚ አባል አገሮች ጋር ባለፈው ዓርብ ባደረጉት ውይይት፣ የፀጥታ ምክር ቤቱ በኢትዮጵያና በሌሎች ቀጣናዊ ቀውሶች ላይ ዕርምጃ መውሰድ አለበት አሉ።

ፕሬዚዳንት ባይደን ይህንን የመንግሥታቸውን አቋም ያስታወቁት፣ የፀጥታው ምክር ቤት ከአንድ ሳምንት በፊት በዚሁ ተመሳሳይ ጉዳይ ላይ ውሳኔ እንዲያሳልፍ፣ በአሜሪካ መንግሥት በቀረበው አጀንዳ ላይ ስምምነት መድረስ አለመቻሉን ተከትሎ ነው።

ግጭት ወለድ ርሃብ በተከሰተባቸው አገሮች ላይ የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዕርምጃ እንዲወሰድ በአሜሪካ መንግሥት ተረቆ በቀረበው አጀንዳ ላይ፣ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም. የመከሩት የፀጥታ ምክር ቤት አባል አገሮች መካከል በተፈጠረ ልዩነት፣ በአሜሪካ የተፈለገውን ውሳኔ ሳያሳልፉ መቅረታቸውን ተመድ ያወጣው መግለጫ ያመለክታል። 

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በዚህ የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ መግባባት ካልተደረሰባቸው የልዩነት ነጥቦች መካከል በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ሁኔታ ላይ አሜሪካ እንዲተላለፍ የፈለገችው ውሳኔ አንዱ ሲሆንትግራይን አስመልክቶ በአሜሪካ በኩል የተንፀባረቀው ፍላጎት ከበርካታ አገሮች ተቃውሞ ገጥሞት ያለስምምነት መጠናቀቁን ተመድ ያወጣው መግለጫ ያመለክታል።

መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም. በተካሄደው የፀጥታ ምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ በአሜሪካ መንግሥት የተቀረፀውን አጀንዳ የተቃወሙት ሩሲያ፣ ህንድና ቻይና መሆናቸውን ያመለከተው የተመድ መግለጫተቃውሟቸውን የገለጹት ከአጀንዳው አቀራረፅ ጋር በተገናኘ እንዲሁም ጉዳዩ ከፀጥታ ምክር ቤቱ የሥልጣን ወሰን ውጪ እንደሆነ በመከራከር መሆኑን ያስረዳል።

ከዚህ በተጨማሪ የጋራ የአቋም መግለጫ ለማውጣት በቀረበው ረቂቅ ሰነድ ላይ የትግራይ ክልል ስም መጠቀስ የለበትም በማለት በፀጥታ ምክር ቤት የአፍሪካ አኅጉርን የወከሉት ሦስቱ ቋሚ አባል አገሮች ማለትም ኬንያ፣ ቱኒዚያና ኒጀርበተጨማሪም በጉዳዩ ላይ ያላትን አቋሟ በጋራ ከጀርመን ጋር የገለጸችው ሴንት ቪንሰንትና ግሬናዲንስ በመከራከራቸው፣ የፀጥታ ምክር ቤቱ ሰምነነት የተደረሰበት አቋም መያዝ ሳይችል ቀርቷል።

ይህንን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ባይደን ከፀጥታው ምክር አባል አገሮች ጋር ባለፈው ሳምንት ዓርብ በበይነመረብ የመከሩ ሲሆንበዚህም ወቅት ኢትዮጵያን ጨምሮ መሰል ግጭት ወለድ ቀውስ ባለባቸው እንደ ሊቢያ፣ ሶሪያ፣ የመንና ሌሎች መሰል ቀውስ በሚታይባቸው አገሮች ላይ ዕርምጃ ሊወሰድ ይገባል የሚል አቋማቸውን መግለጻቸውን፣ ዋይት ሀውስ ዓርብ ዕለት ያወጣው መግለጫ ያመለክታል።

ባለፈው ዓርብ ከፀጥታ ምክር ቤቱ አባል አገሮች ጋር የተወያዩት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባይደንየአሜሪካ እሴቶችን መሠረት ያደረገ ዓለም አቀፋዊ አመራር እንዲሰፍን ያላቸውን ፅኑ ፍላጎት የገለጹ ሲሆንለዚህም ከተመድ የፀጥታ ምክር ቤት ቋሚ አባል አገሮችና ሌሎች መሰል ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር እንደሚሠሩ ተናግረዋል። 

ከአሜሪካ ወዳጅ አገሮች ጋርና ከሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር የዓለም ሰላምና ደኅንነት እንዲሻሻል፣ የኮሮና ወረርሽኝና ሌሎች የጤና እክሎች እንዲወገዱ እንዲሁም በዚህ ምክንያት የተፈጠሩ የኢኮኖሚ ቀውሶች በዘላቂነት እንዲቀረፉ እንደሚሠሩ ለፀጥታ ምክር ቤት አባል አገሮች ተናግረዋል።

በተያያዘ ዜና ፕሬዚዳንት ባይደን በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ነባራዊ ሁኔታ ላይ ያለቸውን ከፍተኛ ሥጋት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ለማሳወቅ፣ የሰየሟቸውን ክሪስ ኩንስ የተባሉ የአሜሪካ ሴናተር በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚልኩ የአሜሪካ የውጭ ገዳይ መሥሪያ ቤት መግለጫ ያመለክታል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...