Sunday, March 26, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የሮተርዳም አልኮል አምራች ኩባንያ በ350 ሚሊዮን ብር በኢትዮጵያ የቮድካ ፋብሪካ ሊከፍት ነው

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ኖዛ ማኑፋክቸሪንግ የተባለ የኔዘርላንድ ኩባንያ በ350 ሚሊዮን ብር ኢትዮጵያ ውስጥ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የቮድካ ፋብሪካ ሊከፍት መሆኑ ተሰማ፡፡

ፋብሪካው ከ200 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድሎች እንደሚፈጥርና ምርቶቹን ወደ ተለያዩ አገሮች በመላክ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የማስገኘት ትልም እንዳለው፣ ኩባንያው ለሪፖርተር የላከው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኩባንያው ወደ ሥራ ሲገባ በሚያመርተው ለቮድካ ምርት የሚጠቀምባቸው በአገር ውስጥ የሚገኙ ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያላቸው ጥሬ ዕቃዎች ከመሆናቸው በተጨማሪ፣ ከሮተርዳም የሚመጡ ጥሬ ዕቃዎችንም እንደሚጠቀም ተገልጿል፡፡

ይመረታል የተባለው የቮድካ ምርት መጠሪያ ስም እስካሁን እንዳልወጣለት የተገለጸ ሲሆን፣ የምርቱ አልኮልነት መጠነኛ እንደሚሆን ድርጅቱ በላከው መረጃ ገልጿል፡፡

የኖዛ ምርቶች ለመዋቢያነት፣ ለመድኃኒት፣ ቀለምና ሽቶዎችን ለሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎች በዋና ጥሬ ዕቃነት ያገለግላሉ ተብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች