Sunday, March 26, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ልማት ባንክ ከስምንት ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ሊሰጥ ነው

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ድጋፍ የሚሆን ከ8.6 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ለመስጠት ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ፡፡ ባንኩ ይህንን ያስታወቀው የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በተለዩ የሥልጠና ማዕከላት ከ2,500 በላይ ሠልጣኞች የተሳተፉበት ሥልጠና መጀመሩን ይፋ ባደረገበት ፕሮግራም ላይ ነው፡፡

ከባንኩ መረጃ መገንዘብ እንደተቻለው ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ባንኩ ያዘጋጀው ከ8.6 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር አቅርቦት ለ2013 የተያዘ ነው፡፡

ይህ በባንኩ የተመደበው ብድር ወጣቶች ሥራ ፈጠራ ለሚያስፈልጉ ለተለያዩ የማሽነሪ ግዥዎች እንዲሁም ከዚሁ ዓላማ ጋር ለተያያዙ ሥራዎች የሚውል መሆኑ ታውቋል፡፡

ኢንተፕራይዞች በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ቢዝነሶችን በመፍጠር ተወዳዳሪ የሚሆኑበትን አሠራር ለመፍጠር ይችሉ ዘንድ ባንኩ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን የባንኩ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) አመልክተዋል፡፡

ሰኞ መጋቢት 13 ቀን 2013 ዓ.ም. የተጀመረው ሥልጠና ለመጀመርያ ዙር ሲሆን፣ በቀጣይም በተለያዩ ከተሞች ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቅ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአሁኑ ወቅት የተበላሸ የብድር መጠኑን ዝቅ እያደረገና ከኪሳራ በመውጣት ወደ አትራፊነት እየተሸጋገረ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የ2013 የሒሳብ ዓመት አፈጻሙን የተመለከተው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በግማሽ የበጀት ዓመቱ ከታክስ በፊት 530.5 ሚሊዮን ብር ማትረፍ ችሏል፡፡ በስድስት ወራት ከታክስ በፊት አገኛለሁ ብሎ በዕቅድ ከያዘው አንፃር ሲታይ የ388 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ ያገኘ መሆኑን ያመለክታል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች