Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ የአንድ ዓመት ጉዞ

ኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ የአንድ ዓመት ጉዞ

ቀን:

በዓለም አቀፍ ደረጃ ወረርሽኘ ሆኖ የበርካቶችን ሕይወት የቀጠፈው ኮቪድ-19 ከተከሰተ ከአንድ ዓመት በላይ አስቆጥሯል፡፡ የኢትዮጵያን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የአንድ ዓመት ጉዞ አስመልክቶ አገራዊው የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጊዜ ቅደም ተከተል ያወጣው መረጃ እንደሚከተለው ተቀናብሯል፡፡

ዓምና (2012)

ታኅሣሥ 21

ቻይና ለዓለም ጤና ድርጅት ከዚህ በፊት ያልታየ የሳምባ ምች ምልክቶችን የሚያሳዩ በርካታ ታማሚዎች እንዳጋጠሟት አስታወቀች፡፡

ጥር 12

የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱ ቫይረስ ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ አረጋገጠ፡፡

ጥር 15

የኮቪድ-19 በሽታን ሪፖርት ካደረጉ አገሮች የሚበልጡ ተጓዦች ወደ ኢትዮጵያ ከመግባታቸው በፊት በቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት የሙቀት ልኬት ተጀመረ፡፡

ጥር 18

በብሔራዊ የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል የኮቪድ-19 ቅድመ ዝግጅትና ምላሽ ማስተባበር እንዲጀመር በመወሰን ዋና አስተባባሪ ተመደበ፡፡

ጥር 21

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ወረርሽኙን የዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ ጤና ሥጋት ብለው አወጁ፡፡

ጥር 29

ኢትዮጵያ በብሔራዊ ኢንፉሌንዛ ላቦራቶሪ የኮቪድ-19 ምርመራ ጀመረች፡፡

የካቲት 3

የዓለም ጤና ድርጅት ለአዲሱ ወረርሽኝ፣ የኮሮና ቫይረስ ኮቪድ-19 የሚል ስያሜ ሰጠው፡፡

የካቲት 6

ግብፅ የአፍሪካን የመጀመርያ የኮቪድ-19 ቫይረስ የተገኘበት ግለሰብ ሪፖርት አደረገች፡፡

መጋቢት 2

የዓለም ጤና ድርጅት ኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ እንደሆነ አወጀ፡፡

መጋቢት 4

ኢትዮጵያ የመጀመርያውን የኮቪድ-19 ቫይረስ የተገኘበትን ግለሰብ ሪፖርት አደረገች፡፡

መጋቢት 6

8335 የኮቪድ-19 መረጃ ነፃ የስልክ መስመር ወደ ዲጂታል ተሻሻለ፡፡

መጋቢት 7

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉና ስብሰባዎችን ማድረግ መከልከላቸውን አሳወቁ፡፡

መጋቢት 11

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 30 የሚጠጉ አገሮች በረራ አቋረጠ፡፡

መጋቢት 14

ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ሁሉም መንገደኞች የ14 ቀናት የግዴታ የኳራንቲን (ውሸባ) አገልግሎት ጀመረ፡፡

መጋቢት 15

በብሔራዊ የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል የኮቪድ-19 ምላሽ ማስተባበር አወቃቀር እንዲከለስ ተደረገ፡፡

መጋቢት 16

ብሔራዊ የኮቪድ-19 የሀብት ማሰባሰብ ኮሚቴ ተቋቋመ፡፡

መጋቢት 18

ምንም ዓይነት የጉዞ ታሪክና የታወቀ ንክኪ የሌለው ሰው የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኘበት፡፡

መጋቢት 19

በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ ከኮቪድ-19 አገግሞ የወጣ ሰው ሪፖርት ተደረገ፡፡

መጋቢት 23

የኮቪድ-19 የላቦራቶሪ ምርመራ በአህሪና ናህዲክ ተጀመረ፡፡

መጋቢት 27

ኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ምክንያት የመጀመርያውን ሞት ሪፖርት አደረገች፡፡

መጋቢት 30

ኮቪድ-19 በሽታን ለመዋጋት ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች፡፡

ሚያዝያ 7

በአፍሪካ ውስጥ በኮቪድ-19 ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺሕ በላይ አለፈ፡፡

ሚያዝያ 26

ለመጀመርያ ጊዜ በአንድ አካባቢ ብዙ የኮቪድ-19 ታማሚዎች ሪፖርት ተደረገ፡፡

ሐምሌ 4

የኮቪድ-19 ሥርጭት በአዲስ አበባ መጠነ ሰፊ የማኅበረሰብ ሥርጭት ደረጃ ላይ እንደደረሰ ታወቀ፡፡

ነሐሴ 1

ማኅበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና ዘመቻ ተጀመረ፡፡

ዘንድሮ (2013)

መስከረም 25

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር መመርያ ቁጥር 30/2013 ፀደቀ፡፡

ኅዳር 9

ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከል ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶችን መክፈት ተጀመረ፡፡

ጥር 5

‹‹እንድናገለግልዎ ማስክዎን ያድርጉ›› በሚል መሪ ቃል የማኅበረሰብ ንቅናቄ ተጀመረ፡፡

ጥር 25

ኮቪድ-19ን ለመከላከል በትምህርት ቤቶች የቅስቀሳ ዘመቻ ተጀመረ፡፡

የካቲት 28

  • የመጀመርያ ዙር 2.2 ሚሊዮን ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ከኮቫክስ ፋሲሊቲ ወደ ኢትዮጵያ ገባ፡፡
  • የኮቪድ-19 ክትባት በኢትዮጵያ መሰጠት ተጀመረ፡፡

መጋቢት 4

ከአንድ ዓመት በኋላ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 53,527፣ ሕይወታቸውን ያጡት 781 ደረሰ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...