Thursday, December 1, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊበኢትዮጵያ የዞረ እግር ያላቸው አምስት ሺሕ ሕፃናት በየዓመቱ ይወለዳሉ

  በኢትዮጵያ የዞረ እግር ያላቸው አምስት ሺሕ ሕፃናት በየዓመቱ ይወለዳሉ

  ቀን:

  የዞረ እግር (ክለብፉት) በወሊድ ወቅት የሚከሰት የአፈጣጠር ችግር ነው፡፡ የሕፃኑ እግር በቀላሉ የማይንቀሳቀስ ሲሆን ወደ ታችና ወደ ውስጥ ይጠማዘዛል (ይዞራል)፡፡ በወቅቱ ካልታከመ ለአካል ጉዳተኝነት ይዳርጋል፡፡ በእርግጠኝነት የታወቀ መንስዔ ባይኖረውም በፈጣሪ ቁጣ (እርግማን)፣ በኃጢአት ምክንያት እንደማይከሰት ግን ይወሳል፡፡

  አቶ ሔኖክ ነጋሽ ‹‹ሆፕ ዎክስ›› በተባለና የዞረ እግር ችግር ባለባቸው ሕፃናት ላይ በሚሠራው መንግሥታዊ ያልሆነ በጎ አድራጊ ድርጅት የምክር አገልግሎት የሚሰጡ (ካውንስሊንግ) እና አስተባባሪ ናቸው፡፡

  እንደ እሳቸው አነጋገር የዞረ ችግር ፖንሴንቴ በሚባል የሕክምና ዘዴ ይድናል፡፡ ልጁ በተወለደ አጭር ጊዜ ውስጥ የተጠቀሰውን ሕክምና መጀመር ይኖርበታል፡፡ የፖንሴቴቲ የሕክምና ዘዴ በጣም ተመራጭ የሆነ ሕክምና ዘዴ መሆኑንና ሁለት ደረጃዎችም እንዳሉት ይገልጻሉ፡፡ የመጀመርያ ደረጃ የማስተካከያ (የጄሶ ሕክምናና የጅማት መብጣት ቴናቶሚ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደረጃ ደግሞ የማስጠበቂያ (የጫማ ድጋፍ) ናቸው፡፡

  የመጀመርያ ደረጃ የሆነው የጄሶ ሕክምና የዞረው እግር በቀስታ ወደ ቦታው እንዲመለስ ማድረግ ሲሆን፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የተስተካከለው እግር ከእግር ጣቶቹ አንስቶ እስከ የላይኛው እግሩ ታፋ ድረስ በጄሶ ይጠቀለላል፡፡ የሕፃናትን የዞረ እግርን ለማስተካከል ከስድስት እስከ ስምንት ጊዜ በጄሶ መታሰር ሊያስፈልጋቸው እንደሚችል፣ የታሰረውን ጄሶ በአዲስ ለመተካት ሕፃኑን በየሳምንቱ ወደ ሕክምና ተቋም መውሰድ ያስፈልጋል፡፡   

  የዞረ እግር የሚከሰተው በወሊድ ጊዜ ወይም ሲወለድ ሲሆን፣ በታዳጊ አገሮች የሚታወቀው ሲወለድ ነው፡፡ በጣም በሠለጠኑት አገሮች ግን ሕፃኑ ማሕፀን ውስጥ እያለ በመሣሪያ ሊለዩት ይችላሉ፡፡ ይህም ቢሆን ተገቢውን ሕክምና የሚያገኘውና የሚስተካከለው ከተወለደ በኋላ ነው፡፡

  በኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ የተካሄደው ጥናት እንደሚያሳየው፣ የዞረ እግር ያላቸው 5,000 ሕፃናት በየዓመቱ ይወለዳሉ፡፡ ከነዚህም መካከል እስከ 1,800 ሕፃናት ተገቢውን ሕክምና ያገኙት ሕክምናው በሚሰጥባቸው በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ 35 የመንግሥት ሆስፒታሎች ውስጥ ነው፡፡

  ለዚህም ዕውን መሆን ሆፕ ዎክስ ከጤና ሚኒስቴር ጋር ባደረገው ስምምነት መሠረት፣ ሕክምናው የሚሰጠው በሳምንት አንድ ቀን ይሰጣል፡፡ የሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡ ሐኪሞችም በሕክምናው ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡

  በሕክምና ላይ ያሉት ሕፃናት የሕክምና ዘዴዎችን ሳያቋርጡ መጠቀማቸውን ለማረጋገጥ ክትትልና ቁጥጥሩ በስልክና ቤት ለቤት እየተዘዋወሩ የሚያካሂዱት በጎ ፈቃደኛ የሆኑ የቤተሰብ አማካሪዎች ናቸው፡፡

   ድርጅቱ የሕክምና ዕርዳታ የሚያደርግላቸውን ሕፃናት ቁጥር ዘንድሮ ወደ ሁለት ሺሕ ከፍ ለማድረግ ቢያቅድም፣ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሳቢያ ዕቅዱን ማዘግየት ግድ እንደሆነበት አስተባባሪው ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

  ሆፖ ዎክስ በአሥራ አንድ ዓመታት ጉዞው የዞረ እግር ችግር ላለባቸው 11,000 ሕፃናት ተገቢውን ሕክምና እንዲያገኙ በማድረጉ ሕፃናቱ መራመድ፣ መሮጥና መጫወት መጀመራቸውን ከአስተባባሪው ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...