Wednesday, February 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊማቆሚያው ያልታወቀለት የዋጋ ንረት

ማቆሚያው ያልታወቀለት የዋጋ ንረት

ቀን:

የኑሮ ውድነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ዘይት፣ እህል ጥራጥሬ፣ የታሸጉ እንደ ፓስታ ያሉና ሌሎችም መሠረታዊ ምግቦች ዋጋ መናር ከጀመረም ወራት ተቆጥረዋል፡፡ የዳቦ ዋጋን ጨምሮ እየናረ የሄደው የምግብ ዋጋ ሸማቹንም ሆድ ያስባሰ ሆኗል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ የተለያዩ ጥረቶች ተደርገዋል ቢባልም፣ አሁንም ችግሩ ይታያል፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርም ሆኑ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በንግዱ ላይ አሻጥር የሠሩ፣ ምርት የደበቁና ዋጋ ያናሩ እየቀጣሁ ነው ቢልም፣ ውጤቱ ገና አልታየም፡፡ በየጊዜው ሁሉም የኃላፊነቱን ይወጣ የሚል መልዕክት ከመንግሥት ባለሥልጣናት ቢሰማም ከሸማቹ የወረደ ነገር የለም፡፡ ችግሩ ሰፊና ውስብስብ ነውና ዘርፉ ብዙ ምላሽ እንደሚፈልግ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች በተደጋጋሚ ሲገልጹ ተሰምቷል፡፡    

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢግልድ) የኅብረት ሥራ ማኅበርና ሌሎች ተቋማት በተገኙበት ‹‹ማቆሚያው ያልታወቀለት የዋጋ ንረት የሸማቹ ሥጋትና የባለድርሻ አካላት ሚና›› በሚል መሪ ቃል መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. የውይይት መድረክ ላይ ተካሂዷል፡፡

የምጣኔ ሀብት ባለሙያና የጥናት አስተባባሪ አቶ ሁሴን ዓሊ እንደገለጹት፣ በአርሶ አደሩ ዘንድ የተመረቱ ምርቶችን በአግባቡ ለኅብረተሰቡ ባለመድረሱ፣ በተገቢው መንገድ ወደ ገበያ ባለመውጣቱ እንዲሁም የዶላር ምንዛሪ ዕጥረት በመከሰቱ ምክንያት የኑሮ ውድነት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ይገኛል፡፡

መንግሥት የግብርና ኢንዱስትሪውን በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ፣ ለአርሶ አደሩ የተመቻቸ የገበያ ሰንሰለት በመፍጠር፣ በአሁኑ ወቅት ማኅበረሰቡ ዘንድ ጥያቄ እያስነሳ የመጣውን የኑሮ ውድነት ማረጋጋት እንዳለበት አቶ ሁሴን ተናግረዋል፡፡

የግብርና ዘርፍ አሁን ላይ ያለውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት ከፍተኛ ሚና ስላለው፣ በአገሪቱ የሚገኙ ባለሀብቶች በዘርፍ ላይ ኢንቨስት በማድረግና ያላቸውን አቅም በመጠቀም መሥራት እንዳለባቸው የጥናት አስተባባሪው አስረድተዋል፡፡  

የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት ግብርና ሚኒስቴር በዘንድሮ ዓመት 13.9 ሚሊዮን ሔክታር መሬት በማረስ በቂ የሆነ ምርት ማግኘቱን፣ ይሁን እንጂ በግል ባለሀብቶች በኩል በሚደረገው አሻጥር ምክንያት የኑሮ ውድነት መባባሱን የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ተወካይ አቶ ገርማሜ ጋሩማ ተናግረዋል፡፡

መንግሥት የመስኖ ልማቱ ላይ ትኩረት በመስጠት በዘርፉ ላይ ሰፊ ሥራ እየሠራ መሆኑን የገለጹት አቶ ገርማሜ፣ ይህም አሁን እየተከሰተ ያለውን የኑሮ ውድነት በተወሰነ መልኩ ሊቀርፍ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

ያሉትን ግብዓቶች ወደ ገበያ በማውጣትና ለማኅበረሰቡ ተደራሽ በማድረግ በኩል የተፈጠረውን ክፍተት በመሙላት የኑሮ ውድነቱን መቅረፍ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የኑሮ ውድነትን ወደ ነበረበት ለመመለስ ሕገወጥ የሆኑ አሠራሮችን ተከታትሎ ለሕግ አቅርቦ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥና የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን መሥራት እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል፡፡

የኅብረት ሥራ ማኅበራትም የኑሮ ውድነትን በጊዜያዊነት ለማረጋጋት ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ የምግብ እህሎችንና ሌሎች የግብርና ምርቶችን በማቅረብ የቀጥታ ሽያጭ ማከናወኑ ይታወሳል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...

ይኼ አመላችን የት ያደርሰን ይሆን?

እነሆ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። ‹‹አዳም ሆይ በግንባር ወዝ ትበላለህ››...