Saturday, April 1, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

መቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ሥራ ቢገባም በርካታ ሠራተኞች እንዳልተመለሱ ተገለጸ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

መንግሥት በጥቅምት ወር በትግራይ ክልል የጀመረውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ ተከትሎ፣ በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ሥራ አቁመው የነበሩ አምራች ድርጅቶች ወደ ሥራ ቢገቡም፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች ወደ ሥራ ገበታቸው መመለስ እንዳልቻሉ ተገለጸ፡፡

በመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚሠሩ አምስት ድርጅቶች ምንም እንኳ ወደ ሥራ የተመለሱ ቢሆንም፣ ድርጅቶቹ ቀጥረው ከሚያስተዳድሯቸው 2‚000 ሠራተኞች 700 ያህል ብቻ ወደ ሥራ እንደተመለሱ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የኮሮና ወረርሽኝ መንግሥት በትግራይ ክልል ሲያደርግ የነበረው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ጋር ተዳምሮ፣ በርካታ የውጭ አገር ድርጅቶች ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባና ወደ ውጭ አገር በመሄድ ሥራቸውን አቋርጠው እንደነበር ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በፓርኩ ከሚንቀሳቀሱ አምራች ድርጅቶች ውስጥ አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የውጭ  ዜጋ የድርጅት ኃላፊ ለሪፖርተር እንደተናሩት፣ በክልሉ ያለው የፀጥታው ሁኔታ ተገማች ባለመሆኑና ክልሉ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ በመሆኑ ሠራተኞችን በፊት በነበረበት ልክ መልሶ ማሰማራት አልተቻለም፡፡

አክለውም፣ ‹‹ድርጅታችን የሕግ ማስከበር ዘመቻው ከመጀመሩ ከነበሩት ሠራተኞች  አሁን መመለስ የተቻለው ከ30 በመቶ አይበልጥም፡፡ ሠራተኞቻችን  እንዲመለሱ መንግሥት አዋጁ የሚያነሳበትን ጊዜ በጉጉት እየጠበቅን ነው፤›› ብለዋል፡፡

ምንም እንኳ የሰላም አለመኖር ትልቁ ሥጋታቸው ቢሆንም አልፎ አልፎ የኢንተርኔትና የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግራቸውን የበለጠ እንዳባባሰው ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ በቅርቡ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የመከላከያና ሌሎች አካላት ባደረጉት ጥረት የሰላም ሁኔታው እንደተስተካከለና ድርጅቶቹ ሥራቸውን ለማስኬድ በሚያስችላቸው ልክ መንግሥት በልዩ ሁኔታ ድጋፍ እያደረገላቸው እንደሆነ አክለው ገልጸዋል፡፡

አቶ ሳንዶካን ወደ ሥራ ያልተመለሱ ሠራተኞች በጥቂት ጊዜ ውስጥ እንደሚመለሱ ገልጸው፣ የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ያስቀመጠው አቅጣጫ በተለይም ለፓርኩ ግንባታ መሬታቸውን የሰጡ ሰዎች ተደራጅተው የጥበቃ ሥራ እንዲያከናውኑ መደረጉ በግጭቱ ወቅት የፓርኩ አንድም ብሎን እንዳይጠፋና ደኅንነቱ እንደተጠበቀ እንዲቆይ አድርጎታል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች