Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበተሳሳተ የመንግሥት አመራርና የውጭ ፖሊሲ ሉዓላዊነታችን እየተደፈረ ነው ሲል ኅብር ኢትዮጵያ ገለጸ

በተሳሳተ የመንግሥት አመራርና የውጭ ፖሊሲ ሉዓላዊነታችን እየተደፈረ ነው ሲል ኅብር ኢትዮጵያ ገለጸ

ቀን:

መንግሥት በያዘው የተሳሳተ የፖለቲካ አመራርና የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ችግር፣ እንዲሁም በቸልተኝነት ምክንያት የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እየተደፈረ ነው ሲል ኅብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ገለጸ፡፡

ፓርቲው በፖለቲካ ኃይሎች መካከል ትልቅ የሆነ አለመተማመን እንዳለና ይህ አለመተማመን ደግሞ በመንግሥት የአያያዝ ችግር የተፈጠረ በመሆኑ፣ ይህ ሁኔታ አገሪቱን ወደ የእርስ በርስ ጦርነት እያስገባት ነው ሲሉ የፓርቲው አመራሮች ገልጸዋል፡፡

አመራሮች የፓርቲውን የምርጫ ማኒፌስቶ ዓርብ መጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ.ም.  ይፋ አድርገዋል፡፡

በመግለጫው ወቅት የተገኙት የፓርቲው የጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር) በኢትዮጵያ እየታየ ያለው የእርስ በርስ ጦርነት ቀጣናዊ ቅርፅ እየያዘና በአገሪቱ ሉዓላዊነት ላይ እያነጣጠረ ከመምጣቱ ባለፈ፣ በሱዳን ወረራ እየተደፈረ ነው ብለዋል፡፡

‹‹ይህን ተከትሎ የውኃ ሀብታችን እንዳንጠቀምና ሌላ አስገዳጅ የሆነ ዓለም አቀፋዊ ጫና በመፍጠር አገሪቱ በቀጣናውና በዓለም አቀፍ መድረክ ዋና መነጋገሪያ አጀንዳ ሆናለች፤›› ሲሉ አክለው ተናግረዋል፡፡

እነዚህን በመንግሥት በቸልተኝነት፣ በአያያዝ ችግርና በአስጠቂነት አካሄድ የተፈጠሩትን በርካታ ችግሮችን ለመፍታት፣ ፓርቲው በመጪው ምርጫ ከተመረጠ ለማስተካከል ቃል የሚገባበት ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

ኅብር ኢትዮጵያ መንግሥት አሁን እየተከተለው ያለውን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በማስተካከል፣ በእኩልነትና በሰጥቶ መቀበል መርህ አካሄድ መንፈስ አንደሚያስቀጥል ይልቃል (ኢንጂነር) ተናግረዋል፡፡

ኅብር ኢትዮጵያ አሁን በአገሪቱ ላይ ወረራ የፈጸሙ አካላት ጉዳይ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ፣ በትዕግሥትና በዓለም አቀፍ መድረኮች እንዲያልቅ መደረግ እንዳለበት፣ ነገር ግን ይህ የማይሆን ከሆነ ዜጎች ሉዓላዊነታቸውን ለማስጠበቅ ታሪካዊ ኃላፊነት ስላለባቸው ጠንካራ የመከላከያ፣ የደኅንነትና የፖሊስ ኃይል በማስተባበርና  ፍትሐዊነቱን በማሳመን፣ አገሪቱን የመከላከል ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው አስታውቀዋል፡፡

በተጨማሪም ሥልጣን ላይ ባለው ገዥው ፓርቲ በስስትና በልምድ ማነስ እጅግ ግዴለሽነት የተሞላባቸውና መሬት ያልረገጡ፣ ሳይንሳዊ ያልሆኑና በግልጽ መመርያ ያልታገዙ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዎች አገሪቱን ችግር ውስጥ ጥለዋታል ሲሉ ወቅሰዋል፡፡

በመሆኑም ኅብር ኢትዮጵያ የአገሪቱ የውጭ ፖሊሲ በሙያ፣ በዕውቀትና በፖሊሲ ታግዞ በግልጽ አቋም በድርድር መመራት አለበት ብሎ እንደሚያምን ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኩባንያ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ባንኮች ውጤታማነት

የጠቅላላ ጉባኤ፣ የጥቆማና ምርጫ ኮሚቴ፣ የተቆጣጣሪ ቦርድ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...