Sunday, March 26, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ፓርላማው የንግድ ተደራሽነትን በከፍተኛ ሁኔታ ያሳድጋል የተባለለትን  ሕግ አፀደቀ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ60 ዓመታት በላይ በሥራ ላይ የቆየውንና ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ተነሳሽነት በከፍተኛ ሁኔታ ያሳድጋል የተባለለትን የንግድ ሕግ አፀደቀ፡፡

በሥራ ላይ ያለው የንግድ ሕግ ለበርካታ ዓመታት የማሻሻያ ውይይት ሲደረግበት መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ማሻሻያው በተለይ አገሪቱ ለዓመታት የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት የምታደርገውን ጉዞ ለማሳለጥ፣ በንግዱ ዘርፍ የሚታዩ ሕገወጥ አሠራሮችን ለማሻሻልና ፍትሐዊ የንግድ ሥርዓት ለመዘርጋት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ክፍል መምህርና በንግድ ሕጉ መሻሻል ወቅት ተሳታፊ የነበሩት ታደሰ ሌንጮ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንዳሉት፣ የሕጉ መሻሻል ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የንግድ ሥራ አመቺነት ከማሻሻል ባለፈ ከፍተኛ የሆነ የኢንቨስትመንት ተደራሽነትና የካፒታል ፍሰትን የሚያመጣ ነው፡፡

የተሻሻለው ሕግ ቀድሞ በሥራ ላይ የነበረውን ባለአምስት መጽሐፍ በሁለት እንዲከፈል ያደረገ ሲሆን፣ የመጀመርያዎቹን መጻሕፍት ነጋዴንና የንግድ ሥራዎችን፣ የንግድ ማኅበራትን የሚመለከትና የኪሳራ (Insolvency) በማለት የንግድ ሕግ ውስጥ እንዲካተቱ አድርጓል፡፡

በቀድሞው ሕግ ውስጥ በንግድ ሕግ ሥር የነበሩ የመጓጓዣ ኢንሹራንስና የባንክ ጉዳዮች በአዲስ የፋይናንስ ሕግ ተብለው በዝግጅት ላይ ይገኛሉ፡፡

በቀድሞው ሕግ ማኅበር ለመመሥረት የፈለገ አካል በተለይም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ለመመሥረት የሚፈልግ አካል ፈቃዱን ለማግኘት ቢያንስ ሁለት ግለሰቦች መኖር እንዳለባቸው የነበረው አስገዳጅ ሕግ ተቀይሮ፣ በአዲሱ ሕግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ለመመሥረት የሚፈልግ ግለሰብ አንድ ሰው ብቻ በመሆን መመሥረት መቻሉ መሠረታዊ የሚባል ለውጥ እንደሆነ ታደሰ ዶ/ር ገልጸዋል፡፡

‹‹ይህ አሠራር በንግድ አደረጃጀት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ አብዮት ነው፤›› ሲሉ  የሕግ ምሁሩ አስረድተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የተሻሻለው ሕግ በአክሲዮን ማኅበራት ውስጥ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ለመሆን የአክሲዮን ባለቤት መሆን እንደ ግዴታ መሥፈርት ይታይ የነበረውን፣ በሙያቸውና በዕውቀት የአክሲዮን ድርጅቱን አቅጣጫ ያስይዛሉ ተብለው ከታሰቡ ግለሰቦች እስከ 35 በመቶ የሚሆኑትን ከውጭ ሊያመጣ እንደሚቻል ይፈቅዳል ብለዋል፡፡

የተሻሻለው የንግድ ሕግ ከዚህ በፊት ያልነበረና ግዙፍ ባለአክሲዮን ድርጅቶች ከዳይሬክተሮች ቦርድ በተጨማሪ ተቆጣጣሪ ቦርድ እንዲያቋቁሙ መፈቀዱ፣ የድርጅቶቹን የቁጥጥር ሥራ ይበልጥ ጠንካራ እንዲሆን እንደሚያደርግ አክለው ገልጸዋል፡፡

በዓለም ባንክ ለቢዝነስ ሥራ አመቺነት መሥፈርት እንደ ትልቅ የሚታየው የአነስተኛ አክሲዮን ባለቤቶች መብትና ጥበቃ፣ በቀድሞው ሕግ የንግድ ጥበቃ እንዳልነበራቸውና በአሁኑ በተሻሻለው ሕግ ግን ጥበቃ እንዲደረግላቸው መሻሻሉ ትልቅ የሚባል ጉዞ ነው ብለዋል፡፡

ዝቅተኛ የአክሲዮን ድርሻ ባለቤቶች በቀደመው ሕግ ውስጥ አክሲዮን መሸጥ ቢፈልጉ በአብዛኛው (Majority) ድምፅ እየተዋጡ ለመሸጥ ወይም ለመለወጥ የማይችሉ ሲሆን፣ በአዲሱ በተሻሻለው ሕግ ግን የመሸጥና የመለወጥ መብታቸው ሙሉ በሙሉ እንደሚጠበቅላቸው ታደሰ (ዶ/ር) አስረድተዋል፡፡ 

የተሻሻለው የንግድ ሕግ የኪሳራ ሕግን ያካተተ ሲሆን፣ ድርጅቶች ዕዳቸውን መክፈል ሲያቆሙ የኪሳራ ሥነ ሥርዓት ውስጥ ገብተው በተቀመጠው ሕግ መሠረት የድርጅቶቹ ንብረት ተሰብስቦና በሐራጅ ተሸጦ ለገንዘብ ጠያቂዎች በቅደም ተከተላቸው የሚከፈልበት፣ የኪሳራ ሥነ ሥርዓት እንደተካተተበት ገልጸዋል፡፡

የቅደመ ኪሳራ ሥነ ሥርዓት ድርጅትን ከኪሳራ የሚታደግ፣ እንዲያገግሙ የሚያደርግ፣ እንዲሁም ድርጅቱን ከመዘጋት የሚታደል፣ ዕዳውን እንደገና በማስተካከል ድርጅቱን መልሶ የማደራጀትና ህልውናን የማስቀጠል ሥራ የሚከናወንበት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች