Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና ተመድ በትግራይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ ምርመራ ሊጀምሩ ነው

  የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና ተመድ በትግራይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ላይ ምርመራ ሊጀምሩ ነው

  ቀን:

  በትግራይ ክልል ተፈጽሟል የተባለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ጥቃት ለመመርመር በጋራ የተስማሙት የኢትዮጵያዊ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን ባለሙያዎች፣ በጥቂት ቀናት ውስጥ ገለልተኛ ምርመራቸውን እንደሚጀምሩ አስታወቁ፡፡

  የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሚዲያ ከፍተኛ አማካሪና ቃል አቀባይ አቶ አሮን ማሾ ለሪፖርተር እንደገለጸው፣ ሁለት አካላት በጋራ ለማድረግ የተስማሙት ስምምነት ቴክኒካዊ ጉዳይ ተጠናቋል፡፡ የጋራ ምርመራው ተዓማኒነትና ተጠያቂነት ባለበት አሠራር በትግራይ ክልል ውስጥ ብቻ እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡

  ተፈጽሟል የተባለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በጋራ ለመመርመር የ90 ቀናት ዕቅድ እንደተያዘ ያስታወቁት ቃል አቀባዩ፣ ሆኖም እንደሚደረገው ምርመራ ዓይነት ከተጠቀሰው ቀናት የበለጠ ጊዜም ሊወስድ እንደሚችል ጨምረው አስረድተዋል፡፡

  በሁለቱ ተቋማት በተናጠል የተሰጠው የጋራ መግለጫ እንደሚያስረዳው፣ ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በትግራይ ክልል የተከሰተውን ግጭት ሁለቱም አካላት በአንክሮ ይከታተሉ ነበር፡፡ ግጭቱን ተከትሎ በንፁኃን ዜጎች ላይ ያጋጠመው ሥጋትና ከአካባቢው የሚደርሷቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጥቆማዎች ያሳስቧቸው እንደነበር አስታውቀዋል፡፡ በግጭቱ የተሳተፉ አካላት በርካታ እንደ መሆናቸው መጠን፣ የገለልተኛ አካላት በጉዳዩ ላይ ምርመራ ማድረግ አስቸኳይ እንደሆነም በመግለጫቸው ተጠቁሟል፡፡

  ሁለቱ አካላት በጋራ ለማከናወን የተስማሙት የምርመራ ሒደት ተቋማቱ የተነሱላቸው የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃና ያጋጠሙ የመብት ጥሰቶችን፣ ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ አንፃር ለመፈተሽ እንደሆነ መግለጫው ያስረዳል፡፡

  በትግራይ ክልል የሚደረገው ምርመራ በግጭቱ ወቅት የተፈጠሩ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ተያያዥ ጉዳዮችን፣ ሁለቱ የሰብዓዊ መብት ተቋማት በተቋቋሙባቸው ሥልጣንና ኃላፊነት ገደብ ልክ ብቻ የሚመረምሩት እንደሆነ በመግለጫው የተጠቀሰ ሌላው ጉዳይ ነው፡፡

  የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በቅርቡ በአክሱም ከተማ የደረሰውን ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አስመልክቶ የመጀመርያ ደረጃ ሪፖርት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

  ሪፖርቱን በተመለከተ አስተያየታቸውን የሰጡት ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በትግራይ ክልል የተከሰተውን አጠቃላይ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ፣ በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅትና በኮሚሽኑ የጣምራ ምርመራ ቡድን አማካይነት እንደሚጣራ የፌዴራል መንግሥት መስማማቱ ትክክለኛ ዕርምጃ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

  ዳንኤል (ዶ/ር) አክለውም አብዛኞቹ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በሕይወት መስዋዕትነት ጭምር አገራቸውንና ሕዝብን የሚያገለግሉ ቢሆንም፣ በተወሰኑ የሠራዊቱ አባላት ለተፈጸሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ተጠያቂነት ለማረጋገጥ፣ ለጣምራ ምርመራ ቡድኑ የሰብዓዊ መብቶች ምርመራ ተገቢውን ዕገዛ ማድረግ እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...