Wednesday, February 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየዋሊያዎቹ የዘጠና ደቂቃ ወሳኝ ምዕራፍ

የዋሊያዎቹ የዘጠና ደቂቃ ወሳኝ ምዕራፍ

ቀን:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ካሜሩን ለምታስተናግደው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ መብቃት የሚያስችለውን ትኬት ለመቁረጥ በዕለተ ማክሰኞ መጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ከአይቮሪኮስት አቻው ጋር የሚያደርገው የ90 ደቂቃ የሜዳ ላይ ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡ የማዳጋስካር አቻውን ባለፈው ረቡዕ መጋቢት 15 ቀን በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም አስተናግዶ በማራኪ ጨዋታ አራት ለዜሮ በሆነ ሰፊ ውጤት የረታው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዓርብ  አቢጃን ገብቷል፡፡

በአውሮፓና መሰል አገሮች በታላላቅ ሊጎች በመጫወት ላይ የሚገኙ ተጨዋቾችን ያሰባሰቡት ዝሆኖቹ፣ በባህር ዳር ስታዲየም በዋሊያዎቹ ሁለት ለአንድ መሸነፉቸው ይታወሳል፡፡ የአይቮሪኮስት ብሔራዊ ቡድን ካጋጠመው ሽንፈት በኋላ ለሁሉም ፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ጥሪ ያደረገ ሲሆን፣ ከትናንት በስቲያ ከምድቡ የማለፍ ተስፋዋ ከተሟጠጠው ኒጀር ጋር የምድቡን አምስተኛ ጨዋታ አድርገዋል፡፡

ወደ አቢጃን ያቀናው የኢትዮጵያ ቡድን፣ ከእንቅስቃሴው በመነሳት ቡድኑ ለ23ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የማለፍ አቅም እንዳለው ብዙዎች ተስፋ አድርገዋል፡፡ አንዳንዶች አሁን ላይ ከሦስት አሠርታት በኋላ በ2012 ዓ.ም. ወደ አፍሪካ ዋንጫ መድረክ ብቅ ያለበትን ጊዜ ማለም ጀምረዋል፡፡

ይህንኑ አሠልጣኝ ውበቱ አባተና ተጫዋቾቻቸው በተለይም ከማዳጋስካሩ ጨዋታ በኋላ በልበ ሙሉነት ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ አሠልጣኙ ከማደጋስካሩ ጨዋታ በኋላ ከሰጡት አስተያየት፣ ‹‹ውጤቱ በቀጣይ ከአይቮሪኮስት ጋር ለምናደርገው የምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ትልቅ የሞራል ስንቅ ነው፣ ወደ አቢጃን የምንሄደው ለኳስ ጨዋታ እስከ ሆነ ድረስ ተጋጣሚን አግዝፎ ማየት ተገቢ ነው የሚል እምነት የለኝም፣ አያስፈልግምም፤›› በማለት በተጫዋቾቻቸው ያደረባቸውን እምነት ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በማዳጋስካር አቻው ላይ ያስመዘገበው ድል ሁሉም ኢትዮጵያውያን ልዩነቶቻቸውን አጥብበው በአንድ ልብ ቢቆሙ የማይወጡት ዳገትና ስኬት እንደሌለ ማሳያ ስለመሆኑ ነው ሲናገሩ የተደመጡት፡፡

የዋሊያዎቹ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታቸውን የሚያደርጉት ከምዕራብ አፍሪካዊቷ ኮትዲቯር ጋር እንደመሆኑ ቀደም ሲል በአገሪቱ የነበረውን የውስጥ ችግር አስመልክቶ፣ ከቀደምት የእግር ኳስ ከዋክብት መካከል ዲዲየር ድሮግባና ሌሎችም አገራቸው በእርስ በርስ ግጭት ውስጥ በነበረችበት ወቅት፣ ብሔራዊ ቡድናቸው ያሳካውን ድል መነሻ በማድረግ ለተቀናቃኞች ያስተላለፉትን የሰላም ጥሪ በመጥቀስ፣ ኢትዮጵያውያንም የድሉን አስፈላጊነትና ትርጉም ሊያጤኑት እንደሚገባ ተማፅኖዋቸውን ሲሰጡ ተደምጠዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...

ይኼ አመላችን የት ያደርሰን ይሆን?

እነሆ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። ‹‹አዳም ሆይ በግንባር ወዝ ትበላለህ››...