Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
እኔ የምለዉየዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ሀ. . . ሁ. . .

የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ሀ. . . ሁ. . .

ቀን:

መስፍን ብቱ

 ‹‹ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ

      አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ››

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማለትም በወያኔ ላይ የተቀዳጀነውን ድል ገና ሳናጣጥም በርካታ የምራቡ መንግታትና የሰብዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የኢትዮጵያ መንግት የሚሰጣቸውን መረጃዎች ሳይሆን የወያኔ አፈ ቀላጤዎች የሚሉትን በማመን በትግራይ ጦርነት ጉዳይ የተባበሩት መንግታት ድርጅት የጥታው ምክር ቤት ዓለም አቀፍ ጣልቃ ገብነት ማስፈለግ አለማስፈለጉ ላይ እየተወያየበት ነው። በሌላ በኩል የግብ መንግት ለአውሮፓ ሚዲያ የሰት ዜና እያራጨ በዓባይ ግድብ ጉዳይ ላይ የአውሮፓ ብረት የወሰደውን አቋም ለማስቀየር እየሞከረ ነው። እነዚህን ከባድ ችግሮች መንግት በየጊዜው በሚሰጠው መግለጫ ብቻ እንወጣቸዋለን? ወይስ ውስጣችንን መርምረን ድክመቶቻችንን ማረም አለብን? አንድ ከልጣን የወረደ ኃይል (ወያኔ) የሚለውና የሚሰብከው እንዴት ከአንድ መንግት ይበልጥ ሊደመጥ ቻለ? ይህ ጽፍ ለዚህ ሁሉ ችግር የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ አራራችንና አደረጃጀታችን ነው ከሚል መደምደሚያ ተነስቶ የሚከተለውን ሳብ ያቀርባል።

ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ሁልጊዜ አልነበረም። የሰው ልጅ የአገዛዝ ሥርዓት (መንግት) ካቋቋመም በኋላም ወዲያው አልተከሰተም። ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ አያሌ አገዛዞች ተመርተው ርስ በርሳቸው በነበራቸው አለመተማመን ወይም ፉክቻና ጦርነቶች በደረሰው ፍጅትና ውድመት የተነሳ በሰላም ተቻችሎ መኖር ማስፈለጉ ጎልቶ በወጣበት ጊዜ የሰላም መረቶቹን ለማስጠበቅ፣ በተፎካካሪ ይሎችም መል ሊኖር የሚገባው ግንኙነት/ወዳጅነት እንዴት ሊሆን እንደሚገባውና እንደሚጠበቅ የተነደፈ ልት ነው። አገራችንም በተለይም ከአውሮ ያላን ጋር ግንኙነት ከመረተችበት ጊዜ ጀምሮ የጀመረችው ክስተት ነው።

ይሁን አንጂ በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ የሚሳተፉ አገዛዞች/መንግታት ሁሉም ቅን ፍላጎት ነበራቸው/አላቸው ማለት አይደለም። በተለይም ኃያላኑ ዲፕሎማሲን የሁልጊዜ የኃያልነት ፍላጎታቸውን ማሟያ አርገው ይወስዱታል። ደካማ መንግታት ደግሞ በዚህ እኩልነት በሌለበት፣ ኃያላን በገነኑበት ዓለም የአገራቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ እንደ አንድ መሪያ አርገው ይወስዱታል። በዚህ በኃያላንና በደካማ መንግታት መል ባለው ግኑኙነት ውስጥ አያሌ ጉዳዮች ይስተናገዳሉ። ልማት፣ ድህነትን ማጥፋት የሚለው የሃ አገሮች ዓላማ ከዚሁ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ጋር የተሳሰረ ሆኗል። ኃያላኑ በፊናቸው የልማትንና የድህነት ማጥፋትን ጉዳዮች ፍጎታቸውን በሃ አገሮች ላይ ለመጫን ይጠቀሙባቸዋል። ሃ አገሮችም ምንም መፈናፈኛ ሲያጡ ለዚሁ ኃያላን አገሮች ጫና እጅ ይሰጣሉ።

ይሁን እንጂ ቀደም ሲል በተለይም የተራማጆች እንቅስቃሴ በመላው ዓለም ጠንካራ በነበረበት ጊዜ በአውሮፓና በዩናይትድ ስቴትስ እንዲሁም በሌሎች ብታም አገሮች ኃያላን መንግታት እንደፈለጋቸው ሃ አገሮችን እንዳይጫኑነዚህ ኃያላን አገሮች የነበሩት የሲቪል ብረሰብ ድርጅቶች መንግቶቻቸው የሚደርጉትን ጫና እየተቃወሙ ይንቀሳቀሱ ስለነበር አንዳንድ ኃያላን መንግታት ሁልጊዜ እንደፈለጉት ሳይሆንላቸው ቀርቷል። ለምሳሌ የዩናይትድ ስቴትስ መንግት በትናም፣ ላኦስና ካምፑቺያ ይደረጉ የነበሩ የነነት ትግሎችን ለማውደም ከፍተኛ ጦርነት ውስጥ ገብቶ በነበረበት ወቅት ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠመውና በኋላም ጦርነቱን እንዲያቆም ካስገደዱት ሁኔታዎች ዋነኛው በዚያው በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ተነስቶ የነበረው ጠንካራ የሲቪል ብረሰብ ጦርነት ትግል ነው። የአውሮፓ መንግታትም ቢሆኑ በጭፍን የዩናይትድ ስቴትስን የውጭ ፖሊሲ እንዳይከተሉ ከፍተኛ ጫና ያደረገው በአውሮፓ የነበረው ጠንካራ የሲቪል ብረሰብ እንቅስቃሴ ነበር። በአውሮፓ የነበረው የሲቪል ብረሰብ እንቅስቃሴ የአሪቱ መንግት ደገፈውም አልደገፈውም በራሱ ከነነት ታጋዮች ጋር ቀጥታ ወዳጅነት ፈጥሮ ከፍተኛ የሞራል ድጋፍ አድርጓል። ለምሳሌ በአውሮፓ በባዎቹና ሰማንያዎቹ ውስጥ ጠንካራ ርታይድ ሶሊዳሪቲ እንቅስቃሴ ነበር። በጊዜው የምራቡ መንግታት ከአፓርታይድ መንግት ጋር ጠንካራ ግንኙነት ፈጥረው ጠንካራ የኮኖሚ ትብብርም ነበራቸው። የማንዴላ ኤኤንሲ ከአውሮፓ መንግታት ጋር ሳይሆን ግንኙነቱና ወዳጅነቱ ከ አፓርታይድ እንቅስቃሴው ጋር ነበር። በዚህም የኤኤንሲ ፕሬዚዳንት ኦሊቨር ታምቦ በ አፓርታይድ እንቅስቃሴው እየተጋበዘ አውሮፓ መጥቶ በየጊዜው ንግግር ያደርግ ነበር። ይኼ በብዙ የአውሮፓ አገሮች የተደረገ ነው። በዩናይትድ ስቴትስም እንዲሁ። ከዚህ የምንረዳው ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ የሚከናወነው በመንግታቱ ብቻ ሳይሆን በሲቪል ብረሰብም እንደሆነ ነው።

የደቡብ አፍሪካን ጉዳይ ለምሳሌ አነሳን እንጂ በአፍሪካ ይደረጉ የነበሩ የነነት እንቅስቃሴዎችን፣ (አንጎላ፣ ሞዛምቢክ፣ ናሚቢያ፣ ጊኒ ቢሳው ዚምባብዌ ወዘተ. . .) የፍልስጤም ዝብ የነነት ትግልን፣ በደቡብ አሜሪካ በየአገሩ የነበሩ ተራማጅ እንቅስቃሴዎችን፣ በእስያም እንደ ፊሊፒንስ፣ ኢንዶኔያ፣ ህንድ፣ ቲሞርና በሌሎችም አገሮች ይደረጉ ለነበሩ የነነት እንቅስቃሴዎች ድጋፍ የሚያደርጉ የሶሊዳሪቲ እንቅስቃሴዎችም ነበሩ። እነዚህ የሶሊዳሪቲ እንቅስቃሴዎች የአውሮፓ መንግታት እንደፈለጉት የዩናይትድ ስቴትስን መንግት የውጭ ፖሊሲ በጭፍን እንዳይደግፉ አድርጓቸው ነበር።

ከዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ዓላማዎች ዋነኛው በላም አብሮ የመኖር (Peaceful Co-existence)፣ ዓለም አቀፋዊ ትብብር (International Cooperation) አልፎ አልፎም ዓለም አቀፋዊ ሶሊዳሪቲ ሲሆን ከሲቪል ብረሰቡ አንር ግን ዋነኛው ዓለም አቀፍ ሶሊዳሪቲው ነው። እነዚህ ዋና ዋና ክስተቶች የሚከናወኑት ግን በአንድና አንድ መንገድ ብቻ ነው፡፡ መገናኛ (Communications) ነው። ያለ መገናኛ ዲፕሎማሲ የሚባል ነገር የለም። መንግታቱም ሆኑ የሲቪል ብረሰቡ ዲፕሎማሲን የሚያካሂደው በመገናኛ ነው። ማንኛውም መንግት በዲፕሎማሲ መስክ ሲሰማራ በተለያዩ ፈርጆች ሆኖ እነዚህ ፈርጆች ግን በሙሉ በግንኙነት የሚከናወኑ ናቸው።

በዓለም አቀፍ ግንኙነት ላይ የሚሳተፍ መንግትም ሆነ የሲቪል ብረሰብ ድርጅት ግንኙነቱ ፍሬያማ እንዲሆን ከሁሉ አስቀድሞ ስለግንኙነቱ ግንዛቤ ሊኖረው ይገባል። ግንኙነት ያለ ግንዛቤ፣ ግንዛቤም ያለ ተቋም አይሆንም፡፡ ይሁን ቢባል እንኳ የአውሮፓ ቅኝ ገዎች በአፍሪካ የነበሩ ቅድመ ቅኝ ግዛት መሪዎቻችንን (ጣያኖች በውጫሌ ውል ሊያጭበረብሩ እንደሞከሩት) እንዲሁም አሜሪካ መጀመያ የደረሱት ፈረንጆች ነዋሪዎችን እንዳጭበረበሯቸው መሞኘት ሊሆን ነው። ግንኙነት ያለ ግንዛቤ፣ ግንዛቤም ያለ ተቋም ሊሆን አይችልም ስንል ምን ማለታችን ነው?

ግንዛቤ አንድ

በዓለም ዓቀፍ ዲፕሎማሲ ግንኙነት ሲባል እንዲያው ለይስሙላ የሚደረገው በየበዓሉ ብሉልኝ ጠጡልኝ፣ በነሱም በዓል እየተገኙ መብላትና መጠጣት፣ ሚስቶቻችንም የአገር ልብሳቸውን የሚያሳዩበት አይደለም። እንዲህ ያለው ግንኙነት በግንዛቤ ላይ ያልተመረተ ዲፕሎማሲ ነው። በዲፕሎማሲ ራ አንደኛው የግንኙነት መርሆ ‹‹የምትናገረውን ወቅ›› ነው። ሁለተኛው አዳማጭህን ወቅ፡፡ ስተኛው ደግሞ ስለዚህም አቀራረብህን ወቅ ነው። አሁን ትኩረት የምንሰጠው ‹‹የምትናገረውን ወቅ›› የሚለው ላይ ይሆናል። ምክንያቱም ሁለቱ መርሆዎች ማለትም አዳማጭህን ወቅና አቀራረብህን ወቅ የተባሉት ቴክኒካ ስለሆኑ ነው። እንግዲያው ግንኙነቱ ምን ምን ግንዛቤን ይጠይቃል?

የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ስለጎረቤት አገሮች ማለትም ኤርትራ፣ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ጂቡቲ፣ ደቡብ ሱዳንና ኬንያ ጠንቅቆ ማወቅን ይጠይቃል። ታሪካቸውን፣ ስለኮኖሚያቸው፣ በአሮቹ ውስጥ ስላሉ የፖለቲካ ኃይሎች ሁኔታ፣ ሞክራሲ መኖሩ ወይም አለመኖሩ ስለዚህም ይህ ደግሞ በአሮቹ ሁኔታ ላይ ያለው አንድምታ፣ ከአፍሪካ ው ካሉ ይሎች በተለይም ከያላኑ ጋር ስላላቸው ግንኙነትና የግንኙነት ታሪክ፣ ስለውጭ ፖሊሲያቸው፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስላላቸው ትብብርና መተሳሰር፣ በአገራቸው ስላሉ ኢትዮጵያውያን ሁኔታ፣ ወዘተ.  ጠንቅቆ ማወቅ የመጀመያው ነው። የዚህ ክፍል መደምደሚያ ደግሞ በኢትዮጵያ ላይ ያላቸው አስተያየት ምን እንደሆነ ማወቅ ነው።

ሁለተኛው ኃያላን አገሮችና የነሱ አጋሮችን ታሪክና የአሁኑን ሁኔታቸውን ማወቅ። ለምሳሌ ዩናይትድ ስቴትስ የተባለው አገር እንዴት እንደ ተመረተ፣ እንዴት የመጀመያ ነዋሪዎቹ እንደ ተጨፈጨፉና ቁጥራቸው እንዲመነምን እንደ ተደረገ፣ የባሪያ ንግድና የባርነት ጉልበት ለአገሪቱ የካፒታል ክምችት ዋናው መረቱ እንደ ነበር፣ በጥቁር አሜሪካውያን ላይ አሁንም የሚታየው ዘረኝነት፣ ኢንስትላይዜሽን እንዴት እንደ ተጀመረና እንዳደገ፣ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ እንግሊዝን ተክቶ እንዴት ያልና ራሱን የምራቡ ብሎም የዓለም መሪ አድርጎ እንደቆጠረ፣ ከእስራኤል ጋር የተፈጠረው ቁርኝት እንዴትና ለምን እንደተከሰተ፣ ወዘተ. በሚገባ ማወቅ። ስለሌሎቹም ኃያላን አገሮች እንዲሁ። እነዚህ አገሮች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚከተሏቸው ፖሊሲዎች በተለይም በኢትዮጵያ ላይ ያላቸው ፖሊሲ ምን እንደሆነና ለምን እንደዚያ እንደሆነ ማወቅ።

ስተኛው ደግሞ በዓለም ላይ ስላሉ ሁለትዮሽ፣ የአካባቢና ዓለም አቀፋዊ ቡድኖች ሁኔታ፣ ታሪክና ምን ምን እንደሚሩ፣ ይኼስ አገራችንንና የአገራችንን ጥቅም እንዴት ሊጠቅም ወይም ሊጎዳ እንደሚችል ጠንቅቆ ማወቅ ነው። የነዚህ ቡድኖች ታሪካዊና ፖለቲካዊ ምክንያቶች ምን ምን እንደነበሩ ማወቅ። ከዘመኑ የዓለም ታሪክ አንር ደግሞ ቢያንስ ቢያንስ የአውሮፓውያን የቅኝ ግዛት ቅርጫ ጀምሮ እስካሁን እስካለ ዋና ዋና የዓለም አቀፍ ታሪክ ማለትም ስለቅኝ ግዛት መስፋፋት፣ ስለአንደኛውና ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ታሪኮች፣ ከዚያ በኋላ በዓለም ላይ ስተከሰቱት ዋና ዋና አዝማሚያዎች፣ ስለቀዝቃዛው ጦርነት፣ ስለድረ ቀዝቃዛው ጦርነት ሁኔታና ስለግሎባላይዜሽን መግነን፣ ወዘተ. በሚገባ ማወቅ እነዚህ ሁኔታዎችም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃ አገሮች ላይ ያስከተሉትን አንድምታ ጠንቀቆ ማወቅ በዓለም አቀፍ ግንኙነት ውስጥ ግዴታ ነው።

አራተኛው በዓለም ላይ ስላሉ ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶች በተለይም ስለተባበሩት መንግታት ድርጅት (ተመድ) ሲስተም፣ መዋቅሩና በሩ ስላሉት አያሌ ድርጅቶች ጠንቅቆ ማወቅ ነው። የተባበሩት መንግታት ድርጅት በምን ታሪካዊ ሁኔታ እንደ ተመረተ፣ ስለድርጅቱ አወቃቀርና አራር፣ በጥታው ምክር ቤትና ጠቅላላ ጉባው የልጣንና የሚና ልዩነቶች፣ ድርጅቱ እስከ ዛሬ ስላወጣቸውና በተለያዩ የመበትና የሌላውም ጉዳዮች ላይ ስለደነገጋቸው ዴክላሬሽኖችና ኮቬንሽኖች፣ አገሮች በድርጅቱ ውስጥ ስላላቸው መብትና ግዴታ በሚገባ ማወቅ። በየአጉሩ የተቋቋሙት ክልላዊ ድርጅቶች (ለምሳሌ የአውሮፓ ብረት የአፍሪካ ብረት ወዘተ.) ከተመድ ጋር ያላቸው ግንኙነት ምን እንደሆነ ጠንቅቆ ማወቅ።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ የሲቪክ ማበራት አሉ። ብዙዎቹ አገራዊ ቢሆኑም ራቸው ግን ዓለም አቀፋዊ ነው፡፡ ለምሳሌ ኦክስፋም። እነዚህ ድርጅቶች ከሰብዊ መብት ጀምሮ እስከ ልማት ድረስ ከፍተኛ ራ ይራሉ። በተለይም የተለያዩ የብረሰብ ክፍሎች (ሴቶች፣ ሕፃናት አርብቶ አደሮች ወዘተ.) ሰብዊ መብት መከበርን በሚመለከት አስመጋኝ ርተዋል። ስለነዚህም ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል። እነዚህ ድርጅቶች በተመረቱባቸው ብታም አገሮች ውስጥ ስላላቸው ሚና፣ ጋዊ መረታቸው፣ ከየመንግቶቻቸው ስላላቸው የበጀትና ሌላውም መብት ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል። በየአገሩ ያሉት እንዲህ ያሉ ድርጅቶች ጋዊ መረታቸው እንደ አገሩ ግና ፖለቲካዊ ባህል ይለያያል።

ከዚሁ ጋር መነሳት ያለበት ጉዳይ ቢኖር ውጭ አገር ስለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ነው። ከንጉ ዘመን ጀምሮ በስደት በየአገሩ የኖሩ ኢትዮጵያውያን ብዙዎቹ የገሩን ዜግነት በመውሰድ በአንድ በኩል ኑሯቸውን ሲገፉ በሌላ በኩል ደግሞ ለአገራቸው የተቻላቸውን ያህል አስተዋጽኦ ለማድረግ ይጥራሉ። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቁጥራቸው እጅግ ብዙ በመሆኑ ሊያደርጉ የሚችሉትም አስተዋጽኦ ከፍተኛ ሊሆን ይችላል። ይህ ሊሆን የሚችለው ግን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው መንግት የእነዚህ ኢትዮጵያውያንን ፖቲካዊ ስሜትና አስተሳሰብ በሚገባ ከተረዳ ነው። ስለሆነም እነሱን በኢትዮጵያ መካሄድ ባለበት የልማትና የሞክራሲ ድገት ደት ተካፋይ እንዲሆኑ ማድረግ መቻል ያስፈልጋል። በዳያስፖራ ውስጥ ያሉት ኢትዮጵያውያን አንድ ዓይነት አመለካከት ስለሌላቸው ብሎም የተለያየ የፖለቲካ ፍላጎት ስላላቸው ሁሉንም ማስማማት አይቻልም። ስለዚህ አብዛኛው ሊሳተፍበት የሚችል ፖሊሲ መንደፍ ተገቢ ይሆናል።

ግንዛቤ ሁለት ዘላቂ ልማትና የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ  

ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ከሚጠይቃቸው ግንዛቤዎች አንደኛው ስለልማት በተለይም ስለዘላቂ ልማት ሊኖር የሚገባው ግንዛቤ ነው። የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች ስለዘላቂ ልማት በቂ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል። ምክንያቱም አገሪቱ ከዓለም አቀፍ ግንኙነት ከምትፈልጋቸው ጉዳዮች አንደኛው ልማቷን የምታስፋፋበትን ድህነትን የምትቀንስበትን መንገድና ድጋፍ ማግኘት ነው። ይኼ ጉዳይ ሁለት ጽታዎች አሉት። አንደኛው ጉዳይ የውጭ ካፒታልን ወይም ድጋፍን የሚመለከት ነው። የኛ ዲፕሎማቶች ለኢትዮጵያ ርዳታና ድጋፍ እንዲገኝ የሚጥሩትን ያህል ያደጉ አገሮች ዲፕሎቶች ደግሞ ለአገራቸው ካፒታሊስቶች ገበያና ርካሽ ጉልበትም ይሻሉ። አንደኛው ራቸውም ይኸው ነው። ዲፕሎማቶቻችን ወይም የሚመለከታቸው ባለልጣናት ስለዘላቂ ልማት በቂ ግንዛቤ ከሌላቸውርዳታ ወይም በድጋፍ ስም በመቶ ገመዶች የተተበተቡ ስምምነቶች ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ። ሁለተኛው ገጽታ ደግሞ በቀጥታ ድጋፍ/ርዳታ ስም የሚደረጉ ስምምነቶች በሚገባ ካልተመረመሩና ጉዳት ላያመጡ የሚችሉ መሆናቸው ካልተረጋገጠ ጉዳታቸው ያመዘነ ሊሆን ይችላል። ለዚህ ሁሉ ዋስትናው ዲፕሎማቶቻችን ስለዘላቂ ልማት ያላቸው በቂ ግንዛቤ ነው።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ መታየት ያለበት አያሌ የተመድ ኮንቬንሽኖችና ዴክላሬሽኖች በቀጥታ ዘላቂ ልማትን የሚመለከቱ ስለሆነ እነዚህን ድንጋጌዎች ጠንቅቆ ማወቅ ቁልፍ ጥያቄ ይሆናል። በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማስቀረት የወጣው (CEDAW)፣ ስለልማት መብት (Right to Development)፣ ስለሕፃናት መብት፣ ስለአካባቢ ጥበቃና ዘላቂ ልማት፣ ስለብዝ ዝብና እንዲሁም የተለያዩ ድንጋጌዎች ስላሉና በመላው ዓለም ያሉ መንግታትም ማክበር ያለባቸው በመሆኑነዚህ ድንጋጌዎች በተለይም ደግሞ ስለዘላቂ ልማት በቂ ግንዛቤ ሊኖር ይገባል። በአፍሪካ ደረጃም ቢሆን በአፍሪካ ብረት የተደነገጉ የአፍሪካ መንግታት የፈረሟቸው አያሌ ድንጋጌዎች ስላሉ በነዚህም ላይ በቂ ግንዛቤ ሊኖር ይገባል።

ግንዛቤ የአፍሪካ የቀና ስምምነቶችና ድርጅቶች

በአፍሪካ ውስጥ በመላ አጉሩም ሆነ በቀና ደረጃ የተዋቀሩ ድርጅቶች አሉ። የአፍሪካ ብረት አንዱ ሲሆን ከላይ እንደ ጠቀስነው አያሌ ድንጋጌዎችን አውጥቷል። በቀና ደረጃም በየቀናው የተዋቀሩ ድርጅቶች አሉ። ኢትዮጵያ ያለችበት የቀና ድርጅት ኢጋድ (IGAD) የሚባለው ሲሆን ከኤርትራ በቀር ሁሉም የአካባቢው አገሮች በአባልነት ይገኙበታል። ሌላው የቀና አደረጃት ደግሞ በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ተመርተው የተቋቋሙ ናቸው። ለምሳሌ በናይል ቤዚን ባሉ አገሮች መል ናይል ቤዚን ኢኒሺዬቲቭ (Nile Basin Initiative) ተብሎ ሁሉም የናይል አገሮች ከኤርትራ በተቀር በአባልነት ያሉበት ነው። በሌሎቹም የአፍሪካ ቀናዎች ተመሳሳይ ድርጅቶች ተቋቁመዋል። ስለሆነም ስለነዚህ የቀና ድርጅቶች በተለይም ደግሞ ኢትዮጵያ ስላለችባቸው ድርጅቶች ጠንቅቆ ማወቅ ከዲፕሎማቶቻችንም ሆነ ከመንግት ባለልጣናት ይጠበቃል። ስለሌሎቹም ቀና ድርጅቶች (ECOWAS, SADC,) በሚገባ ማወቅ ይጠበቃል።

በህዳሴው ግድብ በተነሳው ውዝግብ ምክንያት ስለዓባይ ብዙ ተብሏል። ሆኖም ዓባይን አስመልክቶ እስካሁን ስለተደረጉ ስምምነቶች ከተወሰኑ የመንግት ባለልጣናትና በጉዳዩ ጥናት ካደረጉ ምሁራን በተቀር በሚዲያ ትኩረት ተሰጥቶት አያውቅም ነበር። ከግብ ጋር ንትርክ ሲጀመር ግን በሚዲያ ከተጀመረው ቅስቀሳ የተነሳ ስለዓባይ ያልተገጠመ ግጥም ያልተዘፈነ ዘፈን የለም። ነገር ግን ከስሜት አልፎ ዝቡ በጉዳዩ ላይ ሊያውቅ የሚችለውን ያህል እንዲያውቅ ተደርጓል ወይ? ቢባል አልተደረገም ነው። የሱዳን ጁንታ ከግብ ጋር አብሮ የኢትዮጵያን ግዛት ከወረረ በኋላ ስለሱዳን በሚዲያ የሚነገረው ትክክል ያልሆነ ብዙ ነገር አለ። የማይዘብም አለ። ከሱዳን የሲቪል ብረሰብ ጥምረት የሱዳንን ወታደራዊ ርምጃ በመቃወም መግለጫ መውጣቱን፣ በዓባይ ጉዳይ ኤክስፐርት የሆኑ የሱዳን ምሁራን (ለምሳሌ ዶ/ር ሳላህ ሻዛሊ) የሱዳን ባለልጣናት በጉዳዩ ላይ ስለሚሰጡት የተቃውሞ መግለጫ ኛ ሚዲያ አይዘግብም። ለዚህም ምክንያት በአንድ በኩል ስለዓለም አቀፍ ሶሊዳሪቲ ያለው ደካማ አመለካከት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የኛው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሚያደርገው ገለጻ ይኼንን ጉዳይ ስለማያካትት ነው። 

የግንኙነት ግንዛቤ

ቀደም ብለን ስለግንኙነት መረታዊ መርሆዎች ያነሳነውን (ማለትም የምትለውን ወቅ፣ አዳማጭህን ወቅ፣ አቀራረብህን ወቅ ያልናቸውን) እያስታወስን በዚህኛው ክፍል የምናነሳው ደግሞ ግንኙነትን ስለማደራጀት ነው። አንዳልነው የዲፕሎማቶቻችን ማወቅ ብቻውን መገለጫ ካላገኘና ጥቅም ላይ ካልዋለ የጋን ውስጥ መብራት ይሆናል። ስለሆነም ግንኙነት እንዴት ነው የሚደራጀው ስለሚለው ግልጽ መሆን ያስፈልጋል።

ግንኙነት አደረጃጀት ይጠይቃል። አንድ አምሳደር ወይም ባለልጣን ብቻውን የሚያደርገው አይደለም። ከሁሉ አስቀድሞ የዓለም አቀፍ ግንኙነቱ በሚገባ መዋቀር አለበት። ግንኙነቱ የሚጠይቀው አደረጃጀት መኖር አለበት። ይኼኛው አደረጃጀት ድሮ ጀምሮ ሊኖር ይችላል ብለን ገምተን ስለሚቀረው ብቻ እናንሳ። ከሁሉ አስቀድሞ መግለጫ መስጠት ችግር ወይም ግጭት ሲኖር ብቻ የሚደረግ መሆን የለበትም። ኢትዮጵያ የተቀረው ዓለም እንዲያውቅላት የምትፈልገው ግጭትና ጦርነት ሲነሳ ‹‹ከደሙ ንህ ነኝ›› ለማለት ብቻ መሆን የለበትም። በአገሪቱ ውስጥ ስለሚካሄደው የኮኖሚ፣ ሶሻል፣ ፖሊቲካና ስለሌላውም ሁኔታ ሁሉ በየጊዜው ዓለም እንዲያውቅላት በምትፈልገው ጉዳይ ሁሉ ገለጻ መሰጠት አለበት። ይኼን በማያቋርጥ መንገድ ለማካሄድ አደረጃጀትና መዋቅር ይጠይቃል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይራ ለማከናወን በሚገባ መደራጀት አለበት።

ይህን ራ የሚሩ በዓለም አቀፍ ግንኙነት የለጠኑ ወይም እዚያው መሪያ ቤቱ ውስጥ በሚዘጋጅ ልዩ ኮርስ ልጥነው የተዘጋጁ ራተኞች መኖር አለባቸው። ልጠናው ስለዓለም አቀፍ ግንኙነት ብቻ ሳይሆን አንድ የውጭ ጉዳይ መሪያ ቤት የሚሰጠውን ገለጻ ስለማደራጀትም መሆን አለበት። ዲፕሎማቶች ገለጻ ለማድረግ ችሎታው ያስፈልጋቸዋል። የዲፕሎማሲ ችሎታና አገርን መውደድ ይለያያሉ። በዓለም አቀፍ ግንኙነት ወጤት ከተፈለገ ችሎታ ላይ ትኩረት ማድረግ ይጠይቃል። ከችሎታዎቹ አንዱና እንዲያውም ቁልፍ ከሆኑ ጎኖች አንደኛው የዓለም አቀፍ ቋንቋዎችን (ቢያንስ እንግሊዝኛ ወይም ፈረንይኛ) ጠንቅቆ ማወቅን ይጠይቃል። ከሚኒስትሩ ጀምሮ ቁልፍ ቁልፍ ቦታ ላይ ያሉ የመሪያ ቤቱ ባለልጣናት እንዲሁም አምባሳደሮች እንግሊዝኛ ወይም ፈረንይኛ ቃላት ፍለጋ ሳያስቡ በቀጥታ መናገር (Fluent) የሚችሉ መሆን አለባቸው (እንዲህ ያለው ችሎታ ከሌለ አምባሳደሮቹ የቋንቋ ትምህርት መውሰድ ይኖርባቸዋ)፡፡ የየተመደቡበትን አገር ቋንቋም የሚናገሩ ቢሆን ይመረጣል። የቋንቋ ችሎታ ካለ ከላይ ከጠቀስናቸው ግንዛቤዎች ጋር ብቁ ዲፕሎማቶችን ማፍራት ይቻላል።

ከዚህ በተረፈ በውጭ ግንኙነትና (ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ው ያሉትንም ይጨምራል) ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ላይ የተመደቡት የመንግት ኃላፊዎች በየጊዜው (ለምሳሌ በዓመት ሁለቴ) እንዳስፈላጊነቱ በተለያዩ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ልጠና ያስፈልጋቸዋል። የዓለም ሁኔታ ተለዋዋጭ እንደ መሆኑ መጠን ከሁኔታው ጋር መራመድ ብቻ ሳይሆን ሁኔታውን መቅደምም ያስፈልጋል። በአንድ አገር ወይም አካባቢ አንድ አዲስ ሁኔታ ቢፈጠር (ለምሳሌ የቦሊቪያ ፕሬዚንት ኢቮ ሞራለስ በመፍንቅለ መንግት ቢወርድ በአገሪቱም ሆነ በአካባቢው ምን ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል መመተር ያስችላ) በአካባቢ ወይም በተለያዩ አገሮች ላይ በላፊነት እንዲሩ የሚመደቡት ደግሞ ስለዚያ አካባቢም ሆነ አገር ጥልቀት ያለው ልጠና መውሰድ ይገባቸዋል።

ኤምባሲዎቻችን ውጭ ባሉበት አገር ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች በተለይም የዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ከሚሰጡት ጋር እንዲሁም ንዳንድ የተመረጡ ሲቪል ማበራትና በተለይም ከሚዲያው ጋር የጠበቀ ግንኙነት ማድረግ ይኖርባቸዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዚህ ዓላማ በየጊዜው የሚወጣ በራሪ ቢኖረው ይበልጥ ይጠቅማል። እንዲህ ያለ ግንኙነት ካለ እነዚህ አካላት ስለአገሪቱ ሁኔታ በየጊዜው መረጃ መስጠት ያስችላል። ስለሆነም አንድ ሁኔታ አገራችን  ውስጥ ቢፈጠር እንግዳ አይሆንባቸውም፡፡

የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲያችን በምን ዓይነት አወቃቀር እንደሚራ ባላውቅም ከላይ የጠቀስነው አራርና መዋቅር ብሎም ችሎታው ያላቸው ዲፕሎማቶች እንደሌሉን ግን አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል። እንደ ወያኔ ያለ በዝብ የተጠላ፣ ዓለም አቀፍ ውቅና ሊያገኝ የማይገባው፣ ከሁሉም በይ ደግሞ ከልጣን የወረደ በዓለም አቀፍ ግንኙነቱ በልጦን የሚነዛውን ውሸት ተደማጭነት እንዲኖረው ማድረግ ከቻለ እኛው ራሳችን የቤት ራችንን ቀደም ብለን እንዳልራን ግልጽ ነው። ‹‹ታዲያ ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ…›› የሆነብንም ለዚህ ነው።

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን፣ በኢሜይል አድራሻቸው  [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

‹‹ደስታ›› የተባለችው አማርኛ ተናጋሪ ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም

‹‹እንደ ሮቦት ዋነኛው አገልግሎቴ ውስብስብ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አሠራሮችን...