Friday, March 24, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኅብረት ባንክ የዲጂታል አውሮፕላን ትኬት ክፍያ አገልግሎት ማቅረቡን ገለጸ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ኅብረት ባንክ ከሶል ጌት ትራቭል ጋር በመሆን አማራጭ የዲጂታል አውሮፕላን ትኬት ክፍያ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን አሠራር መዘርጋቱን አስታወቀ፡፡

ጉዞ ጎ›› የተባለው አገልግሎት የኅብረት ባንክ ደንበኞች የተለያዩ አየር መንገዶችን ትኬት ግዥ በየትኛውም ጊዜና ቦታ በሞባይል ባንኪንግ ወይም አሠራሩን ካመቻቸው ኅብረት ባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ክፍያ መፈጸም የሚያስችለው ስለመሆኑም ገልጿል፡፡

አገልግሎቱን ያለ ምንም ክፍያ ለደንበኞች የሚሰጥ መሆኑን ያስታወቀው የባንኩ መግለጫ፣ በሒልተን ሆቴል የሚገኘው የኅብረት ባንክ ቅርንጫፍ ሳምንቱን ሙሉ የ24 ሰዓት አገልግሎት እንደሚሰጥም አስታውሷል፡፡

ደንበኞች እንደምርጫቸው በሞባይልም ሆነ በቅርንጫፎች በኩል ክፍያ ቢፈጽሙም የአሠራር ሲስተሙ ግን አንድ ዓይነት መስመር የተከተለ በመሆኑ በዚህ አሠራር ደንበኛው ክፍያ ከፈጸመ በኋላ ወዲያው ትኬቱን ጉዞ ጎ› የሚያገኙ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

የዚህ ዓይነቱን አሠራር ኅብረት ባንክ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ላለፉት አራት ዓመታት የተገበረው መሆኑንና አሁንም አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሆነ ገልጾ፣ ከ ‹‹ጉዞ ጎ›› ጋር የተተገበረው የአየር ቲኬት ክፍያ ሲስተምን ለየት የሚያደርገው የተለያዩ አየር መንገዶችን የበረራ አገልግሎቶች ከእነ ዋጋቸው ጭምር ለደንበኞች ምርጫ ማቅረቡ እንደሆነም አመልክቷል፡፡

ከወቅቱ ነባራዊ ሁኔታ ብሎም ኅብረት ባንክ ከሚከተለው የዲጂታላይዜሽን መርህ አንፃር እንዲህ ያሉ አገልግሎቶች ለደንበኞች አስፈላጊ እንደሆኑ ባንኩ እንደሚያምን አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች