Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናመገናኛ ብዙኃን የኢንቨስትመንት ማበረታቻ እንዲያገኙ የሚያስችል ደንብ እየተዘጋጀ እንደሆነ ተገለጸ

መገናኛ ብዙኃን የኢንቨስትመንት ማበረታቻ እንዲያገኙ የሚያስችል ደንብ እየተዘጋጀ እንደሆነ ተገለጸ

ቀን:

የመገናኛ ብዙኃን ፖሊሲ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከፀደቀ በኋላ፣ ዘርፉ እንደ ሌሎች ዘርፎች የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎን እንዲያገኝ የሚያስችል የኢንቨስትመንት ደንብ እየተሻሻለ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ማክሰኞ መጋቢት 21 ቀን 2013 ዓ.ም. በካፒታል ሆቴል የሚዲያ ፖሊሲው ዋና ዋና ሐሳቦችና በማስታወቂያ ሥርጭት ላይ፣ ‹‹የመገናኛ ብዙኃን ኃላፊነት›› በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት ባዘጋጀበት ወቅት ነው፡፡

በውይይቱ ወቅት የመግቢያ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ ሰብሳቢ አቶ አማረ አረጋዊ፣ ምክር ቤቱ በቅርቡ የፀደቀውን የመገናኛ ብዙኃን ፖሊሲ መሠረት በማድረግ ሚዲያው ምን ዓይነት የሥነ ምግባር መርሆዎችን ሊከተል ይገባል? በማስታወቂያ ሥርጭት ላይስ የመገናኛ ብዙኃን ኃላፊነት ከሕግ አንፃር ምን ሊሆን ይገባል? የሚለውን የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር ውይይቱን እንዳዘጋጀ ገልጸዋል፡፡

በፓናል ውይይቱ ላይ በቅርቡ ስለፀደቀው የመገናኛ ብዙኃን ፖሊሲ የመነሻ ጽሑፍ ያቀረቡት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከፍተኛ አማካሪ አቶ ግዛው ተስፋዬ፣ የሚዲያ ፖሊሲው ከፀደቀ በኋላ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር በፖሊሲው ላይ ከፍተኛ ምክክር እንደተደረገ አስታውቀዋል፡፡ ዘርፉ እንደ አንድ የኢንቨስትመንት መስክ እንዲያዝ ከገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት እንደተደረገ ያስታወቁት ከፍተኛ አማካሪው፣ በዚህም የኢንቨስትመንት ደንብ ማሻሻያዎች ረቂቅ እንደተጠናቀቀ አስታውቀው፣ በቀጣይ ረቂቁ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ ወደ ሥራ የሚገባ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

የኢንቨስትመንት ደንቡ መሻሻል መገናኛ ብዙኃን እንደ ሌላው ዘርፍ ማበረታቻዎችን እንዲያገኙ ዕድል የሚፈጥርላቸው እንደሆነ ያስረዱት አቶ ግዛው፣ በዚህም ተቋማቱ የማስፋፊያ ቦታ፣ ብድር፣ የቀረጥ ቅነሳ እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ቅድሚያ ተጠቃሚነት ዕድል የማግኘት ሥራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

አዲሱ ፖሊሲ ከመገናኛ ብዙኃን ባለቤትነት አንፃር የተሻሉ ነገሮች እንዳካተተ ያስረዱት ከፍተኛ አማካሪው፣ ከዚህ በፊት የንግድ መገናኛ ብዙኃን ባለቤቶች ከአንድ በላይ ስብጥር እንዳይኖራቸው የሚከለክለው አሠራር ተቀይሮ በአዲሱ ፖሊሲ አንድ የንግድ ድርጅት በአንድ ጊዜ የሬዲዮ፣ የቴሌቪዥን፣ የጋዜጣና የመጽሔት ባለቤት መሆን የሚችልበት ሁኔታ ተመቻችቷል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በማስታወቂያ ሥርጭት ላይ የባለድርሻ አካላት ሚና ምን ሊሆን ይገባል? በሚለው ሐሳብ ላይ የማስታወቂያ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳንኤል ብርሃኑ የውይይት ሐሳብ አቅርበዋል፡፡ ማስታወቂያ ሦስት ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ሥራ ላይ የሚውል አንድ ዘርፍ እንደሆነ ያስታወቁት አቶ ዳንኤል፣ እነዚህም ማስታወቂያ አስነጋሪ፣ አዘጋጅ (ኤጀንት) እና የሚያሠራጨው አካል (መገናኛ ብዙኃን) እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡

መገናኛ ብዙኃን ከአገሪቱ ሕግና ሥርዓት አንፃር ማስታወቂያን ገምግመው ለአየር ማብቃት እንዳለባቸው በውይይቱ ወቅት የተነሳ ሲሆን፣ የማስታወቂያ አዘጋጆችም ከደረጃ፣ ከጤናና ከሌሎች ጥንቃቄ ከሚያሻቸው ምርቶች ጋር የተገናኘ ሥራዎችን ሲያከናውኑ ተገቢውን ፈቃድና ተያያዥ ጉዳዮችን ማጤን እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡

በፓናል ውይይቱ ላይ የተሳተፉት የማስታወቂያ ባለሙያዎች፣ ዘርፉን መንግሥት እንደ አንድ ዘርፍ ሊቆጥረውና ሊደግፈው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ከማስታወቂያ ጉድለቶችና ስህተቶች ጋር የተገናኘን ተጠያቂነት ወደ ማስታወቂያ አዘጋጅ የመግፋት ዝንባሌ በስፋት ይታያልም ብለዋል፡፡

ተገቢውን የደረጃና የፈቃድ ሁኔታ ከአምራችም ሆነ ከአስመጪ ጠይቀን ሥራችንን እያከናወን ብንገኝም፣ በተለይም የማስታወቂያ አሠራጭ የሆኑት ተቋማት ባልተገባ የጥቅም ትስስር ከተቋማት ጋር በሚፈጥሩት ግንኙነት ዘርፉን እያቀጨጩት ይገኛሉ ሲሉ ባለሙያዎቹ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...