Sunday, February 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊዋና ኦዲተሩ ከ12 ዓመታት አገልግሎት በኋላ በክብር ተሰናበቱ

ዋና ኦዲተሩ ከ12 ዓመታት አገልግሎት በኋላ በክብር ተሰናበቱ

ቀን:

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤትን ለአሥራ ሁለት ዓመታት በዋና ኦዲተርነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ገመቹ ዱቢሶ በጡረታ ተሰናበቱ፡፡

ዋና ኦዲተር ገመቹ ለአሥራ ሁለት ዓመታት ተቋሙን በመምራት በመንግሥት ባለበጀት ተቋማት ላይ የሚታየውን የኦዲት ጉድለትና የአፈጻጸም ግድፈት በማጋለጥ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ ከፍተኛ የሆነ ዝና ያተረፉ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ኃላፊዎች በተገኙበት፣ ለአቶ ገመቹና ተቋሙን ለስድስት ዓመታት በምክትል ዋና ኦዲተርነት ላገለገሉት ወ/ሮ ባዩሽ ተስፋዬ የሽኘት ፕሮግራም አካሂደዋል፡፡

በሽኘት ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ መሐመድ የሱፍ፣ ፓርላማው ጠንካራ የኦዲት አሠራር ለማስፈን የሚያደርገውን ጥረት በማገዝ፣ ለቋሚ ኮሚቴው ትልቅ አቅም የፈጠሩ ናቸው በማለት ገልጸዋቸዋል፡፡

አቶ መሐመድ፣ አቶ ገመቹ በኦዲት ሥራ ብዙ ለውጥ እንዲመጣ ያደረጉ፣ ‹‹አስፈጻሚዎችን ከእንቅልፍ ያነቁ ሰው ናቸው›› በማለት ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

‹‹አቶ ገመቹ ቆራጥና ጀግና፣ ለግልጽነት ወደኋላ የማይል፣ አገሪቱን ትልቅ መስመር ያስያዘ ሰው ነው፤›› በማለት አቶ መሐመድ ገልጸዋቸዋል፡፡

 ‹‹እሱን ለመግለጽ ቃል ያጥረኛል፤›› ያሉት አቶ መሐመድ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ለተጠያቂነትና ግልጽነት ያደረጉት ጥረት፣ በተለይም ፓርላማውንና ሥራ አስፈጻሚውን በመግፋት ትልቅ የሆነ አገራዊ የሆነ መነቃቃት የፈጠሩ ኦዲተር ነበሩ በማለት አስረድተዋል፡፡

በድሮው አሠራር የኦዲት ማስተካከያ የማይልኩ ተቋማት በርካታ የነበሩ ቢሆንም፣ በአቶ ገመቹ ጊዜ ሁሉም ተቋማት ቀጥ ብለው እንዲያመጡ አድርገዋቸዋል ሲሉ አቶ መሐመድ ተናግረዋል፡፡

በማቋቋሚያ አዋጁ መሠረት ለሁለት ስድስት ዓመታት ተቋሙን ያገለገሉት አቶ ገመቹ፣ ከመጋቢት 3 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በምክትላቸው እንደተተኩ ተገልጿል፡፡

ቀጣዩ ዋና ኦዲተር በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት የሚሾም ሲሆን፣ ከግንቦት ምርጫ በፊት ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ አቶ መሐመድ አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የመንግሥት ውዝግብ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት...

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ምሥረታ ዝግጅቶችና ከገበያው የሚጠበቁ ዕድሎች

ኢትዮጵያ ከ50 ዓመት በኋላ ዳግም የምታስጀምረውን የካፒታል ገበያ ዘመኑን...

አዲሱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት የሚያደርጉባቸውን ቀዳሚ ጉዳዮች ይፋ አደረጉ

አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ትኩረት አድርገው የሚሠሩባቸውን ቀዳሚ...

መንግሥት የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ጥሰው የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያስቆም ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ...