Wednesday, April 17, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊዲኬቲ በኮሮና ወረርሽኝ የኮንዶም አቅርቦትና ሥርጭት መጓተት ቢፈጠርም እጥረት እንዳይኖር እየሠራ መሆኑን...

ዲኬቲ በኮሮና ወረርሽኝ የኮንዶም አቅርቦትና ሥርጭት መጓተት ቢፈጠርም እጥረት እንዳይኖር እየሠራ መሆኑን አስታወቀ

ቀን:

በ2020 ዓ.ም. የኮንዶም ሥርጭት በ29 ከመቶ ቀንሷል

የኮሮና ወረርሽኝ የዓለምን የንግድ ሥራዓትና ጉዞዎች ላይ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ መክቱቱን ተከትሎ፣ በኢትዮጵያ የገቢ ዕቃዎች አቅርቦትና ሥርጭት ላይ መጓተት ካስከተለባቸው ውስጥ የኮንዶም ሥርጭት አንዱ እንደነበር ዲኬቲ ኢትዮጵያ አስታወቀ፡፡

የተለያዩ የኮንዶም ምርቶችንና ዓይነቶችን በማቅረብና በማከፋፈል ትልቁን ድርሻ የያዘው ዲኬቲ ኢትዮጵያ፣ እ.ኤ.አ. 2020፣ 42 ሚሊዮን የሚደርሱ ኮንዶሞችን ለገበያ ቢያቀርብም፣ አጠቃላይ መጠኑ ካለፈው ዓመት አንፃር ሲታይ በ20 በመቶ መቀነስ እንደታየበት የዲኬቲ ኢትዮጵያ የሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ማናጀር አቶ ፍትሕ ቶላ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ዲኬቲ መንግሥታዊ ያልሆነ የማኅበራዊ ግብይት ተቋም ሲሆን፣ ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ እንደማንኛውም ከየክልሉ መንግሥታትና ለጋሾች የሚገኘው የፈንድ ዕጥረት እንዳጋጠመው ገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ በመላው አገሪቱ የሚያከፋፍለው የኮንዶም አቅርቦት እጥረት እንዳይኖር እየሠራ መሆኑን አቶ ፍትሕ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

እ.ኤ.አ. 2020፣ 56 ሚሊዮን ኮንዶም ለማደል ቢያቅድም፣ ያሳካው ግን 42 ሚሊዮኑን ብቻ ነው፡፡ ካቀረባቸው አጠቃላይ 42 ሚሊዮን የኮንዶም ዓይነቶች ውስጥ በዋናነት ሕይወት ትረስት፣ ሰንሴሽንና ሰንሴሽን ኤክስትራ የተባሉት ናቸው፡፡ ሕይወት ትረስትና ሰንሴሽን የተባሉት የኮንዶም ዓይነቶች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ተጠቃሚዎች የሚቀርቡ ሲሆን፣ ሰንሴሽን ኤክስትራ የተባለው የኮንዶም ዓይነት የተሻለ ገቢ ላላቸው ተብሎ እንደነበር ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

ነገር ግን ካለፈው ዓመት የተገኘው መረጃው የሰንሴሽን ተጠቃሚ ቁጥሩ ከፍ ብሎ መገኘቱን አቶ ፍትሕ ጠቁመዋል፡፡ እንደ ኃላፊው ገለጻ ድርጅቱ ባደረጉው የገበያ ቅኝት ከፍተኛ ገቢ ላላቸው ተብሎ የቀረበው ሰንሴሽን ኮንዶም ተጠቃሚው በ49.9 ከመቶ ከፍተኛውን ሲይዝ ሕይወት ትረስትና ሰንሴሽን የተባሉት የምርት ዓይነት የተጠቃሚዎች ድርሻ በቅደም ተከተል ሲታይ 24.6 እና 16.3 ከመቶ መሆኑን መረጃው ያሳያል፡፡

በአቅርቦቱ ደረጃ በመድሐኒት ማከፋፈያ ሱቆች ወይም ፋርማሲ ሲታይ ምርቶቹ ያላቸው ድርሻ በ46 ከመቶ የያዘው ሕይወት ትረስት ሲሆን፣ ሰንሴሽንና ሰንሴሽን ኤክስትራ ያላቸዋ ደረጃ በቅደም ተከተል 57.9 እና 65.3 ከመቶ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በ2020 ዓ.ም. የኮንዶም ተጠቃሚነት በ29 ከመቶ እ.ኤ.አ. 2019 በተደረገው የመረጃ ቅኝት ማነሱ፣ ቢረጋገጥም በማኅበረሰቡ ያለው የኮንዶም ተጠቃሚነት የግድ ቀንሷል ወደሚል ድምዳሜ አያደርስም ብለዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ የመረጃ ማሰባሰብ ሥራው ራሱ በተፈጠረው የወረርሽኙ ተፅዕኖ መረጃ መሰብሰቡ ላይም ተፅዕኖ የነበረው መሆኑን በመጥቀስ አቶ ፍትሕ አስረድተዋል፡፡ ተቋሙ የዚህ ዓመትን መረጃ በተመለከተ በኢትዮጵያ የበጀት ዓመቱ የመጀመርያ ሩብ ዓመት በአገሪቱ የተከፋፈለው የኮንዶም ምርት ከ10.1 ሚሊዮን በላይ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ወቅት ዲኬቲ 17 ሚሊዮን የሚደርሱ የኮንዶም ምርቶች ያሉት ሲሆን፣ ከ26 ሚሊዮን በላይ የሆነ የኮንዶም ምርት ወደ አገር ውስጥ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡ ምንም እንኳን በድርጅቱ ላይ ኮሮና ወረርሽኝ ያሳደረበት ተግዳሮት ቀላል ባይሆንም ምርቶቹን በማከፋፈል ሒደቱ ምንም ዓይነት የዋጋ ለውጥ አለማድረጉን ገልጿል፡፡

ነገር ግን ምርቶችን በሚሸጡ የሽያጭ ቦታዎች፣ ሱቆች እንዲሁም በተወሰኑ ፋርማሲዎች ያለምንም ምክንያት ዋጋ ጭማሪ መስተዋሉን ጠቁመዋል፡፡

ይሁን እንጂ ዲኬቲ በሽያጭ ሥፍራዎች በመከታተል የዋጋ ቁጥጥር የማድረግ ሥልጣን እንደሌለው ጠቅሰው፣ የድርጅቱ ወኪል አከፋፋዮችን ግን የሚከታተሉ በመሆኑ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ እንደማይኖር ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

ሪፖርተር ባደረጋቸው ቅኝቶች የኮንዶም ምርትን ለተጠቃሚዎች የሚያቀርቡ ሱቆች፣ ፋርማሲዎችና ሱቅ በደረቴዎች ከሦስት ብር እስከ አምስት ብር ይሸጡ የነበሩ ሲሆን፣ ሕይወት ትረስትና ሰንሴሽን የተባሉ ምርቶችን ከአሥር ብር እስከ 15 ብር እየሸጡ መሆኑን አውቋል፡፡

የኮንዶም ግብዓት በአገሪቱ የሥነ ተዋልዶና የኤች አይቪ ሥርጭትን ለመግታት በመንግሥትና በለጋሽ አገሮች በድጎማ የሚቀርብ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ከፌዴራሉ የኤችአይቪ መከላከልና ቁጥጥር ተቋም (ሀብኮ) የ2020 መረጀ እንደሚያሳየው፣ ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ ዜጎች አጠቃላይ ቁጥሩ 622,326 ነው፡፡ በዓመቱም የሚያዙ ሰዎች ብዛት 11,715 ሲሆን፣ በ2020 ዓ.ም. ብቻ በቫይረሱ 12,685 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...