Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየቡድን ሰባት አገሮች የኤርትራ ጦር ከትግራይ ክልል መውጣቱ ተረጋግጦ ሁሉን አሳታፊ ሥርዓት...

የቡድን ሰባት አገሮች የኤርትራ ጦር ከትግራይ ክልል መውጣቱ ተረጋግጦ ሁሉን አሳታፊ ሥርዓት እንዲመሠረት አሳሰቡ

ቀን:

የኤርትራ ጦር ከትግራይ ክልል መውጣቱ ተረጋግጦ፣ ሁሉን አሳታፊ የፖለቲካ ሥርዓት መመሥረት እንዳለበት የቡድን ሰባት (G7) አባል አገሮች አሳሰቡ።

የቡድን ሰባት አባል አገሮች ማለትም ካናዳ፣ ፈረንሣይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ጃፓን፣ እንግሊዝና አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ዓርብ መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታን አስመልክቶ ባወጡት መግለጫ፣ የኤርትራ ጦር ከትግራይ ክልል እንደሚወጣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (/) ይፋ ማድረጋቸውን በበጎ ጎኑ እንደሚቀበሉት ገልጸዋል። 

ነገር ግን የኤርትራ ጦር ያለ ቅድመ ሁኔታ በፍጥነት ከትግራይ ክልል መውጣት እንዳለበት፣ ከትግራይ ክልል መውጣቱም መረጋገጥ እንደሚኖርበት አሳስበዋል። 

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ሳምንት ወደ ኤርትራ አቅንተው ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ድንበር አልፎ ወደ ትግራይ የገባውን የኤርትራ ጦር በተመለከተ መወያየታቸውን ገልጸውየኤርትራ ጦር በትግራይ ክልል ከያዛቸውድንበር አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ መስማማታቸውን ማስታወቃቸው አይዘነጋም። 

የሁለቱ አገሮች መሪዎች ያደረጉትን ስምምነት ተከትሎም፣ የኢትዮጵያ ጦር ስምምነቱ ከተፈጸመበት ዕለት አንስቶ፣ የኤርትራ ጦር ይዟቸው በነበሩ የድንበር አካባቢዎች በመሰማራት ጥበቃ እንደሚያደርግ አስታውቀው ነበር።

ይሁን እንጂ ተደረሰ በተባለው ስምምነት መሠረት፣ የኤርትራ ጦር ከትግራይ ክልል ስለመውጣቱ ከሁለቱም ወገን እስካሁን የቀረበ ማረጋገጫ የለም። 

የኤርትራ ጦር ከትግራይ ክልል እስካሁን እንዳልወጣ እየተነገረ ሲሆን፣ ይህንን ግንማስረጃ ማረጋገጥ አልተቻለም። 

በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ከፊል የኤርትራ ጦር ከትግራይ ክልል እንዲወጣ ስምምነት መደረሱን፣ የሩሲያ መንግሥት እንደሚያደንቅ የሚገልጽ መረጃ ሠፍሮ ይገኛል። 

በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ግጭቶች መቆም እንዳለባቸውና ሁሉን አሳታፊ የፖለቲካ ሥርዓት በአገሪቱ መፈጠር እንዳለበትም የቡድን ሰባት አገሮች አሳስበዋል።  ትግራይን ጨምሮ በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው ሁሉን አሳታፊ የፖለቲካ ሥርዓት በመፍጠር፣ ተዓማኒነት የሚኖረው ምርጫ ማካሄድና በቀጣይ ብሔራዊ ዕርቅ የሚደረግበት ሥርዓት ማመቻቸት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በምሥራቅና በመካከለኛው የትግራይ ክልል በርካታ አካባቢዎች አስፈላጊውን የሰብዓዊ ዕርዳታ ማድረስ ባለመቻሉ በአካባቢው የምግብ እጥረት መባባሱን በመግለጽ፣ በትግራይ ክልል ግጭት እየተሳተፉ የሚገኙ ሁሉም ኃይሎች በፍጥነት የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እንቅስቃሴ ያለ ገደብ ማድረስ የሚቻልበትን መንገድ በፍጥነት እንዲፈጥሩም አሳስበዋል። 

በክልሉ ሰላማዊ ነዋሪዎች ላይ እየደረሱ ያሉ ግድያዎች፣ አስገድዶ መድፈርና መሰል አስከፊ ኢሰብዓዊ ጥሰቶች አሁንም እየተፈጸሙ ስለመሆናቸው፣ ሰብዓዊ ዕርዳታን የተመለከቱ ዓለም አቀፍ ሕጎች እንደተጣሱ በቅርቡ ከወጡ ሪፖርቶች መገንዘባቸውን በመግለጽ፣ ሁኔታው በእጅጉ እንደሚያሳስባቸው የቡድን ሰባት አባል አገሮች አስታውቀዋል። 

በትግራይ ነዋሪዎችና በክልሉ በሚኖሩ ስደተኛ ኤርትራዊያን ላይ እየደረሰ ያለው ግድያ፣ ፆታዊ ጥቃትና አስገድዶ ማፈናቀል እንደሚያወግዙ ገልጸውበግጭቱ የሚሳተፉ ኃይሎች በተቻለ መጠን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ፣ እንዲሁም ለሰላማዊ ሰዎች ጥበቃ እንዲያደርጉ፣ ሰብዓዊ መብቶችንና ዓለም አቀፍ ሕጎችን እንዲያከብሩ አሳስበዋል።

በክልሉ ኢሰብዓዊ ጥሰቶችን በፈጸሙ ኃይሎች ላይ የሕግ ተጠያቂነት እንዲኖር፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ ያሳየውን ቁርጠኝነት በበጎ በመቀበል ይህ ቁርጠኝነት ወደ ተግባር ተለውጦ ለማየት እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል። 

ከዚህ አኳያም የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በጋራ ሆነው በትግራይ ግጭት የደረሰውን ኢሰብዓዊ ጥሰት ለመመርመር መስማማታቸውን በጎ ጅምር እንደሆነ የጠቀሱ ሲሆንበክልሉ የተፈጸመውን ጥሰት በገለልተኛ አካል ማጣራቱ አስፈላጊ እንደሆነ አስታውቀዋል። 

የቡድን ሰባት አባል አገሮች የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትንና ተፈጽመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን ለመመርመር የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ዝጎጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል። 

ቡድን ሰባት አባል አገሮች መግለጫ በትግራይ ክልል ግጭት እየተሳተፉ ያሉ ኃይሎች የሰብዓዊ ዕርዳታ ለማቅረብ ያልተገደበ እንቅስቃሴ እንዲያመቻቹ እንጂ፣ አሜሪካ በተናጠል ደጋግማ እንዳሳሰበችው፣ በግጭቱ እየተሳተፉ ያሉ ኃይሎች በአስቸኳይ ግጭቱን እንዲያቆሙ አይጠይቅም። 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ስለዘር ፖለቲካ

በሀብታሙ ኃይለ ጊዮርጊስ  ‹‹በቅሎዎች ዝርያችን ከአህያ ነው እያሉ ይመፃደቃሉ›› የጀርመኖች...

አማርኛ ተናጋሪዋ ሮቦት

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሳይንስ ሙዚየም፣ ሚያዝያ 2 ቀን...

ወዘተ

ገና! ከእናቴ ሆድ ሳለሁ፤ ጠላት ሲዝትብኝ ሰምቻለሁ። በዳዴ ዘመኔም፣ በ'ወፌ ቆመችም!'፤ አውዴ ክፉ ነበር...

የአስፕሪን ታሪክ

በቤት ውስጥ የሚገኝ የመድኃኒት መደርደሪያ፣ ምንም ቢሆን፣ እስፕሪንን ሳይጨመር...