Tuesday, May 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊችግሮችን ለማወቅ በ22 ዩኒቨርሲቲዎች የፆታ ዳሰሳ ጥናት እየተደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ

ችግሮችን ለማወቅ በ22 ዩኒቨርሲቲዎች የፆታ ዳሰሳ ጥናት እየተደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ

ቀን:

በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከፆታ ጋር የተገናኙ ችግሮችን ለማወቅ በ22 ዩኒቨርሲቲዎች የፆታ ዳሰሳ ጥናት እየተደረገ እንደሆነ፣ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አስታወቁ፡፡

ፕሬዚዳንቷ ይኼን ያስታወቁት የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውና የሴቶች ተሳትፎን በተመለከተ ሰኞ መጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ.ም. በስካይላይት ሆቴል፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር፣ እንዲሁም አሜዚንግ ፕሮሞሽንና ኢቨንት ባዘጋጁት የምክክር መድረክ ላይ ነው፡፡

‹‹ሴቶችን የተመለከቱ ጉዳዮች በአዳራሽ ውስጥ በመሰብሰብ የሚፈቱ አይደሉም›› ያሉት ፕሬዚዳንቷ በአፍ የሚነገረውን ሴቶችን ማገዝ፣ መደገፍና ማብቃት በማለት ወደ ተግባር መለወጥ እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከሴቶች ጋር በተገናኘ ያለውን ችግር ለመረዳት በጥናት ላይ የተመሠረተ ሥራ ማከናወን እንደሚገባ የገለጹት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፣ በ22 ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተውጣጡ ምሁራን ተወዳድረውና ተመርጠው የፆታ ዳሰሳ ጥናት እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ ‹‹ዩኒቨርሲቲ ላይ ካልተሠራ ተተኪ ሴቶችን ማምጣትና ማፍራት አይቻልም፡፡ በመሆኑም ሁሉም እዚህ ላይ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል፤›› ብለዋል፡፡

ከፆታ ዳሰሳ ጥናት በተጨማሪ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በአምስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለሚገኙ 500 የሦስተኛና የአራተኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎች የሙያ ምክር (ሜንተርሺፕ) አገልግሎት ለመስጠት ታቅዷል፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሲሠሩ ‹‹ሜንተርሺፕ›› አንዱ ሲሰጡት የነበረው ተግባር እንደነበረ ያስታወሱት ፕሬዚዳንቷ፣ ሦስት ሴት ወጣት ዲፕሎማት ተማሪዎችን ‹‹ሜንተር›› ለማድረግ ጥያቄ እንዳቀረቡ አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው ‹‹ትቺያለሽ!›› እና ‹‹በፈተና የተሞረደ ማንነት ለለውጥ የተመቸ ስብዕናን ይገነባል›› ተብሎ  በተዘጋጀው መድረክ ላይ የከተማው አስተዳደር ሐሳቡን መደገፍ ትክክለኛ ተግባር መሆኑን በመረዳት፣ ከተባባሪ ተቋማት ጋር መድረኩን እንዳዘጋጀ ገልጸዋል፡፡

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ምን ያህል ሴቶች ከፍተኛ ተሳትፎ እንዳላቸው በአዲስ አበባ ከተማ እየተገነቡ ያሉ ትልልቅ ፕሮጀክቶች ተጠቃሽ እንደሆነ የገለጹት ምክትል ከንቲባዋ፣ ቀንም ሌትም እየተሠሩ በሚገኙት የመስቀል አደባባይ፣ የዓድዋ ፓርክ፣ የታላቁ ቤተ መንግሥት የመኪና ማቆሚያ ፕሮጀክቶች ሴቶች ከፕሮጀክት መሪነት እስከ ፈጻሚነት ተሳትፈውበታል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ በርካታ ሴቶች በአምራች ኢንዱስትሪው ውስጥ እንደሚገኙ ካለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር እስከ ተያዘው ዓመት ጥር የተደረገ አንድ ጥናት ጠቅሰው ያቀረቡት የኢቲጂ ዲዛይነሮችና አማካሪዎች አክሲዮን ማኅበር መሥራች እሸቱ ተመሥገን (ዶ/ር)፣ የኮንስትራክሽን ዘርፉን የሚቀላቀሉት የሴት ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ጥናቱ አሳይቷል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመስቀል አደባባይ የመግቢያ ክፍያ ለምን?

ወጣቶች፣ ሕፃናትና አረጋውያን ሳይቀሩ መንፈሳቸውን የሚያድሱበት እንዲሁም ሐሳባቸውን በነፃነት...

በሕገ መንግሥቱ የተዋቀረው ‹‹የብሔር ፖለቲካ›› እና ‹‹ሥርዓቱ›› ያስከተለው መዘዝና መፍትሔው

(ክፍል አራት) በዓቢዩ ብርሌ (ጌራ) ባለፈው ጽሑፌ (በክፍል ሦስት) አሁን ያለው...

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብና የመንግሥት መሪ ምሥል

በበቀለ ሹሜ በ2015 ዓ.ም. መጋቢት ወር ውስጥ ይመስለኛል በ‹ሸገር ካፌ›...

ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ያደረገው አዋጅ የፍትሐዊነት ጥያቄ አስነሳ

በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ስምንት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ በማድረግ ተቋማዊና...