“ፃፍ ፃፍ” አትበሉኝ፣
እንዴት እፅፋለሁ?
እንጀራ ስፈልግ፣
ብዕሬን ጥያለሁ።
“አውራ!” በሉኝ እኔን፣
እኔን በሉኝ “አውራ!”
“አውራ!”
“አውራ!”
“አውራ!”
ማውራት ነው የማውቀው፣
ጆሮ እስኪጠላ ሰው፣
ምላሴን ሳላውስ፣
እየሰቀጠጠው ።
“ አውራ!” በሉኝ “አውራ!”
ጆሯችሁ ካልሞተ፣
ባፍ የተነፋውን፣
ተከፍቶ እየዋጠ።
– አሸናፊ ዋቅቶላ