ወደ ውጭ የሚጓዙ ዜጎችን ያስቀራል የተባለውንና ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ይገነባል የተባለውን ሮሃ ሕክምና ማዕከል ግንባታ የመሠረት ድንጋ ተቀመጠ። የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ /ር) ናቸው።
ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ አገሮች የሚጓዙ ዜጎችን ያስቀራል የተባለው “የህክምና ማዕከል ሮሀ የህክምና ማዕከል” የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ሙሉ ወጪውን ችሎ የሚገነባው ሮሃ ግሩፕ የተባለ የአሜሪካ ኩባንያ መሆኑንም፣ ዛሬ ሚያዝያ 2 ቀን 2013 ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ ሲቀመጥ ተነግሯል።
ግንባታው በአምስት አመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል። የሕክምና ማዕከሉ የልብ ቀዶ ጥገና፡ የካንሰርና ዘርፈ ብዙ የሕክምና አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል፡፡ለ7,500 ዜጎች የስራ ዕድል ከመፍጠሩም በተጨማሪ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከልም እንደሚሆንም የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሀንስ ተናግረዋል ፡፡
በየሕክምና ማዕከሉ ተኝተው ለሚታከሙ 1500 አልጋ ፡እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡ ማዕከሉ የሚገነባው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ሀያት ሆስፒታል አካባቢ አድዋ ፓርክ ሜዳ ላይ ነው።
- Advertisement -
- Advertisement -