Tuesday, October 4, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊአዲስ አባባ ውስጥ እስከ 250 ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ አደጋ ማድረስ የሚችል...

  አዲስ አባባ ውስጥ እስከ 250 ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ አደጋ ማድረስ የሚችል የኬሚካል ክምችት መኖሩ ተነገረ

  ቀን:

  ከአዲስ አባባ በ250 ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ በሚገኙ አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ አደጋ ሊያደርስ የሚችል ለበርካታ ዓመታት ተከማችቶ የሚገኝና የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈበት የኬሚካል ክምችት በላፍቶ ክፍለ ከተማ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

  ለረዥም ዓመታት ተከማችተው ይገኛሉ የተባሉት የኬሚካል ዓይነቶች ዲዲቲ፣ ፀረ ተባይና ፀረ አረም፣ አሲድ ውህድና መሰል ኬሚካሎች እንደሆኑ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃጅ ኢብሳ ተናግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ የተከማቹት ኬሚካሎች ከተማዋን የማጥፋት አቅም ያላቸው በመሆናቸው፣ የዓለም አቀፍ አጥኚዎችን ወደ አገር ቤት በማስመጣት የማስወገድ ሥራውን ለመሥራት ቅደመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ አቶ ሃጅ ተናግረዋል፡፡

  ኬሚካሉን ለማስወገድ የበጀት እጥረት በመኖሩ ለማስፈጸሚያ የሚሆን ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ሀብት እያፈላለገ እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

  ዳይሬክተሩ ሲናገሩ፣ በአሁኑ ሰዓት ምንም እንኳ በአዲስ አበባ በተገኘው  ክምችት ላይ ትኩረት ቢደረግም፣ በክልል ከተሞች ጭምር በርካታ የኬሚካል ክምችት እንዳለ እንደተረጋገጠና መንግሥት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕገወጥ ክምችም አለ ብሎ እንደሚያምን ተናግሯል፡፡

  በተመሳሳይ ዜና ኤጀንሲው ከሚያዝያ 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው አገር አቀፍ የንብረት ምዝገባና ማስወገድ ዘመቻ በመንግሥት ተቋማት ከተከማቸ የአገር ሀብት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ለማግኘት መታቀዱን አቶ ሃጅ ተናግረዋል፡፡

  በዚህ ዘመቻ ለበርካታ ዓመታት በመንግሥት ተቋማት ያለአገልግሎት የቆሙ ተሽከርካሪዎች፣ ማሽነሪዎች፣ ኮምፒዩተሮችና መሰል የአገር ሀብቶችን በመመዝገብ መወገድ የሚገባቸውን ለማስወገድ፣ መሸጥ ወይም ማስተላለፍ የሚገባቸውን ደግሞ ለማስተላለፍ ዕቅድ መያዙን የኤጀንሲው ዳይሬክተር ተናግረዋል፡፡

  ለአራት ቀናት በሚቆየው የንብረት ምዝገባና ማጣሪያ ዘመቻ ከ190 በላይ በሚሆኑ የመንግሥት ተቋማት ንብረቶችን የሚመዘግብና የሚያስወገድ ኮሚቴ ከ20 ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የተውጣጣ ግብረ ኃይል መቋቋሙን ተናግረዋል፡፡

  በኢትዮጵያ በበርካታ የመንግሥት ተቋማት በኃላፊነት ደረጃ የተቀመጡ ግለሰቦች፣ ለሀብትና ለንብረት ትኩረት ስለማይሰጡና በክትትል ጉድለት ማነስ በቢሊዮን ብሮች የሚቆጠር የሕዝብ ሀብት እንደሚባክን በኤጀንሲው በኩል ይነገራል፡፡

  ኤጀንሲው በፌዴራል የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ፣ የንብረት አስተዳደርና የግዥ አፈጻጸም ሥርዓት እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ መግለጹን አስመልከቶ ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል፡፡

  በዚህም በአገር አቀፍ ደረጃ ከ10,000 በላይ ተሽከርካሪዎች በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ ሜዳ ላይ ሳር በቅሎባቸው እንደሚገኙና ያለ ምንም አገልግሎት በየመጋዘኑና በሜዳ ላይ የተጣሉ ናቸው፡፡

  አብዛኞቹ ንብረቶች ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ የተቀመጡ እንደሆኑ፣ ከዚያ ሲያልፍም አንዳንዶች በልጅ እያሱ ዘመን ተገዝተው የተቀመጡ እንደሆኑ ተገልጿል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img