Monday, March 27, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዳሸን ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር ሹመትን አፀደቀ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አቶ ነዋይ በየነ የዳሸን ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር ሆነው እንዲያገለግሉ የቀረበለትን የሹመት ጥያቄ አፀደቀ፡፡

በቅርቡ በተደረው የዳሸን ባንክ ጠቅላላ ጉባዔ የተመረጡት አዳዲስ ቦርድ አባላት አቶ ነዋይ የዳሸን ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው እንዲያገለግሉ የመረጧቸው መሆኑን በማሳወቅ፣ ብሔራዊ ባንክ የቀረበለትን ጥያቄ ተቀብሎ ማፅደቁን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡

አቶ ነዋይና አዲስ የቦርድ አባላት ሆነው በባንኩ ጠቅላላ ጉባዔ አባላት የተመረጡት በታኅሳስ 2013 ዓ.ም. እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ ተመራጭ የቦርድ አባላቱ ደግሞ አቶ ነዋይን የቦርዱ ሊቀመንበር ሆነው እንዲያገለግሉ ከሰየሟቸው በኋላ ሹመታቸው እንዲፀድቅ የብሔራዊ ባንክ ይሁንታ ሲጠበቅ ነበር፡፡

አቶ ነዋይ ባንኩን በቦርድ ሊቀመንበርነት ለማገልገል የተመረጡትም በድጋሚ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ዳሸን ባንክ በአሁኑ ወቅት 25ኛ ዓመት በዓሉን በማክበር ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በ2012 የሒሳብ ዓመት ሪፖርቱ መሠረት የባንኩ ጠቅላላ የሀብት መጠን 68.8 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡ ጠቅላላ የካፒታል መጠኑን 8.31 ቢሊዮን ማድረስ የቻለው ዳሸን ባንክ፣ ከታክስ በፊት ከ1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን መግለጹ ይታወሳል፡፡ ባንኩ ከ450 በላይ ቅርንጫፎች አሉት፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች