Sunday, September 24, 2023

ታቅደው የሚለኮሱ የቅድመ ምርጫ ግጭቶች አንድምታ

- Advertisement -spot_img

በብዛት የተነበቡ

በቀድሞው ገዥ ፓርቲ ኢሕአዴግ ውስጥ የነበረውን የሥልጣንና የለውጥ ትግል አሸንፈው ልክ የዛሬ ሦስት ዓመት በመጋቢት 2010 ዓ.ም. ወደ የፓርቲ ሊቀመንበርነትና የአገር መሪነት ሥልጣን ላይ የተቀመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (/)፣ በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የፖለቲካ ቅቡልነትን አግኝተዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ፈጣን የሆነ ቅቡልነት የተቸራቸው ወደ ሥልጣን ከመጡበት ዕለት አንስቶ መውሰድ በጀመሯቸው የለውጥ ጅማሮዎች ነበር።  ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ያስከትል የነበረውን እስርና አፈና በመቀየር፣ በትጥቅ ትግል ይንቀሳቀሱ የነበሩና በስደት የተቃውሞ ፖለቲካን ያራምዱ የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ አገራቸው ገብተው ሰላማዊ የፖለቲካ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ከመፍቀድ በተጨማሪ፣ በግል ጥሪ በማድረግና በማነጋገር የወሰዱት አዎንታዊ ዕርምጃ ሙገሳን ካስገኙላቸው ተግባራት መካከል ተጠቃሽ ነው። 

የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለማድረግ የማያስችሉ አፋኝ ሕጎች ላይ ማሻሻያ ማድረጋቸው፣ በተለያዩ የወንጀል ሕጎች የተከሰሱና የተፈረደባቸው የፖለቲካ ልሂቃንና ጋዜጠኞች ምሕረት እንዲያገኙ በማድረግ ወደ ፖለቲካ ተሳትፏቸው እንዲመለሱ አስችለዋል። 

የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ለማሳደግ በወሰዱት የተለየ ተግባር የሚመሩት ካቢኔ (የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት) ስብጥር ሃምሳ በመቶ በሴቶች እንዲወከል ማድረጋቸው፣ ከሞላ ጎደል ለሁለት አሥርት ዓመታት ገደማ ሰላም ያጡትን የኤርትራና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዳግም ወደ ወዳጅነት የመለሰ የዕርቅ ተግባር መፈጸማቸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ተስፋ የፈነጠቁ መሪ ካስባሉ ተግባራት መካካከል ዋነኞቹ ናቸው። 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥልጣን የመጡበት ዓውድ የእርስ በእርስ መጠራጠር፣ የብሔር ግጭቶች የተንሰራፉበትና ሕዝቦች ከመኖሪያ ቀያቸው ተገደው የሚፈናቀሉበት የፖለቲካ ዓውድ ውስጥ ቢሆንምጠቅላይ ሚኒስትሩ የማዕከላዊ መንግሥቱ መቀመጫ ከሆነችው አዲስ አበባ ሆነው ችግሮቹን ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ፣ ችግሮቹ ወደ ነበሩባቸው በርካታ የአገሪቱ ክፍሎች በመዘዋወር መፍትሔ ለማበጀት ያደረጉት ጥረትና የተፈናቀሉ ሚሊዮኖችን መልሰው እንዲቋቋሙ ማድረጋቸውም ይጠቀሳል።

በዚህም የአገሪቱ የፖለቲካ ችግሮችን ሙሉ በሙሉ መፍታት ባያስችላቸውምየተሻለ ዕፎይታ የተገኘበት እንደነበር ከውስጥም ሆነ ከውጭ ሆነው የሚታዘቡ የተስማሙበት እውነታ ነው። ነገር ግን ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጅማሮ በተለያዩ ምክንያቶችና ተዋናዮች ፈተና ሳይገጥመው የተከናወነ አልነበረም። 

የሶማሌ ክልልን ያስተዳድር የነበረው የፖለቲካ ስብስብ ደቅኖት የነበረውን አደጋ፣ የመከላከያ ኃይልን በመጠቀም በኃይል የማስወገድ ዕርምጃ እንዲወስዱ አስገድዷቸዋል።  የትግራይ ክልልን ያስተዳድር የነበረው የሕወሓት የፖለቲካ ኃይል የጠቅላይ ሚኒስትሩን ፖለቲካዊ አስተዳደር የመጎንተልና እረፍት የመንሳት አካሄድ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከተገመተው የፈጠነ ዕርምጃ እንዲወስዱ ያስገደዳቸው ነበር። 

በዚህም ይመሩት የነበረውን የፓርቲዎች ጥምረት ኢሕአዴግ ወደ ውህድ ብሔራዊ ፓርቲ የመቀየር ተግባር የፖለቲካ ሒደቱ መንገራገጭ ውስጥ መግባት የጀመረበትን አጋጣሚ ፈጥሯል።

ይህ ክንውን አጠቃላይ ምርጫ በሚካሄድበት ዓመት በድንገትና በፍጥነት የተከናወነ መሆኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፖለቲካ ትግል አጣማሪ የነበሩትን አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ፣ በርካታ የኦሮሞ የፖለቲካ ልሂቃንን ያስከፋና የጠቅላይ ሚኒስትሩን የፖለቲካ መንገድ ከመጠራጠር አልፈው ከመስመር መውጣትን እንዲወስኑ ምክንያት ሆኗል።

ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕርምጃ ሥልጣንን የማሰባሰብና ጉልበትን የማጠናከር ተደርጎ በአንድ ወገን ሲወሰድበሌላ ወገን ደግሞ የፌዴራላዊ ሥርዓቱን የመቀየርና የብሔረሰቦችን የፖለቲካ ሥልጣን በማዳከም ወደ አሀዳዊ ሥርዓት የመሸጋገር ጅማሮ ተደርጎ ተቆጥሯል።

ከዚህ ሒደት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነትን ለማበጅት አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ብልፅግና የሚል ስያሜ የተሰጠውን ውህድ ፓርቲ በመፍጠር ሒደት ውስጥና የፓርቲውን መመሥረት ተከትሎ፣ ከአገሪቱ የፖለቲካ ምኅዳር ጨርሰው ያልጠፉ ነገር ግን ትርጉም ባለው ደረጃ ተቀዛቅዘው የነበሩ ደም አፍሳሽ ግጭቶችና መፈናቀሎች ዳግም መቀስቀስና መንሰራፋትን ይዘዋል። 

በሰኔ ወር 2011 ዓ.ም. የአማራ ክልል አመራሮችና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም መገደል ውህድ ፓርቲው ብልፅግና ከመፈጠሩ አስቀድሞ የተከሰተና የፖለቲካ ዓውዱን ያጨፈገገ ክስተት ሲሆንከዚህ በኋላም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ በአመራሮች ላይ ያነጣጠረና ብሔር ተኮር ግድያን መሠረት ያደረገ የትጥቅ ትግል ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በጥቅምት ወር 2012 ዓ.ም. በምዕራብ ወለጋ የሚኖሩ 54 የአማራ ተወላጆች መገደልበቀጣዩ ወር በዚሁ አካባቢ የሚማሩ 17 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መታገትና መሰል ቀውሶችን ተከትሎ፣ የፌዴራል መንግሥት ድርጊቱን ፈጽሟል ብሎ በወነጀለው በአካባቢው በሚንቀሳቀስ የኦነግ ጦር ብሎ ራሱን በሚጠራው ታጣቂ ኃይል ላይ የኃይል ዕርምጃ መውሰድ ጀምሯል። 

በደቡብ ክልልም (በወላይታ) ተመሳሳይ ግጭቶችና ብሔር ተኮር ጥቃቶች መከሰት፣ በምሥራቅ ኦሮሚያ በርካታ አካባቢዎች ተመሳሳይ ጥቃቶች ደጋግሞ በመፈጠሩ በርካቶች እንዲገደሉ፣ ንብረታቸው እንዲወድምና እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ የምርጫ ዝግጅት እየተካሄደ የነበረ በመሆኑ፣ በርካታ ልሂቃን በዚህ የፖለቲካ ዓውድ ውስጥ የሚካሄድ ምርጫ ሥጋት ፈጥሮባቸው ነበር። 

ይሁን እንጂ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮሮና ወርሽኝ በመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም. በኢትዮጵያ መስፋፋቱን ተከትሎ ምርጫውን ለማካሄድ እንደማያስችል ተገልጾ ሕገ መንግሥታዊ መፍትሔ ፍለጋ ውስጥ የገባው የፌዴራል መንግሥትበሰኔ ወር ላይ ምርጫው እንዲራዘም የሕገ መንግሥት ትርጓሜ በመስጠት ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ምርጫው እስኪካሄድ ድረስ በኃላፊነት እንዲቆይ ተወስኗል።

ይኼንን ውሳኔ ከገዥው ፓርቲ ውጪ የሆኑ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች ሲቃወሙት፣ ትግራይ ክልልን የሚያስተዳድረው ሕወሓት በክልሉ የተናጠል ምርጫ ማካሄዱ በገዥው ፓርቲና በሕወሓት መካከል የነበረው ፖለቲካዊ ጥል እንዲካረር ምክንያት ሆኗል። 

የብልፅግናና የሕወሓት ጥል በከረረበት ወቅትበኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የነበረው ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ በአዲስ አበባ መገደሉ፣ በእሳት ላይ ቤንዚን ሆኖ ከአርባ በላይ የኦሮሚያ ከተሞች በግጭት እሳት ጋዩ። 

የድምፃዊውን ግድያ ተከትሎ የተቀሰቀሱ ግጭቶችን አስተባብረዋል ተብለው የተጠረጠሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እነ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባና እስስንድር ነጋ የመሰሉ የፖለቲካ አመራሮች በቁጥጥር ሥር ውለው እስር ቤት እንዲገቡና የፍርድ ሒደታቸውን እንዲከታተሉ ምክንያት ሆኗል።

በሌላ በኩል በትግራይ የፌዴራል መንግሥቱንና ክልሉን በሚመሩ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል የተፈጠረው ጥል እየተፋፋመ በመቀጠሉ፣ በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም. መጨረሻ ወደ ጦርነት ገብተዋል።

ይህ ጦርነት እየተካሄደ በነበረበት ወቀት ብቻ በሌሎች አካባቢዎች የነበሩ ግጭቶች ከሞላ ጎደል ሰክነው የነበሩ ቢሆንም፣ በትግራይ ክልል ጦርነት የበላይነትን የያዘው የፌዴራል መንግሥት ሕወሓትን ከክልሉ ሥልጣን አስወግዶ መቀሌን መቆጣጠሩን ከገለጸ በኋላ በየአካባቢው የነበሩ ግጭቶች ዳግም ማገርሸት ጀምረዋል።

በአሁኑ ወቅትም ከትግራይ ክልል በተጨማሪ በመተከል፣ በከሚሴናአጣዬበምዕራብ ወለጋ፣ በደቡብ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ መለስተኛ ግጭቶች፣ በአፋርና በሶማሌ ክልሎች መካከል ሰሞኑን የተከሰተው የአስተዳደር ወሰንን መነሻ ያደረገ ግጭት የሚስተዋሉ ሲሆን፣ የአገሪቱ ሕዝብም በእነዚህ የግጭት ነበልባሎች እየተሠቃየ ነው።

አገሪቱ በዚህ የፖለቲካ ሁኔታ ውስጥ ባለችበት ወቀት በመጪው ሰኔ ወር እንዲካሄድ ቀን ለተቆረጠለት አጠቃላይ ምርጫ፣ ከትግራይ ክልል በስተቀር በሌሎቹ የአገሪቱ ከባቢዎች ለማካሄድ የዝግጅት ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው።

ከምርጫ አስቀድሞ ግጭቶች ለምን ይከሰታሉ?

ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ የሚካሄዱ ምርጫዎች በተደጋጋሚ ጊዜ በቅድመ ምርጫ ግጭቶች ታጅበው የመካሄዳቸውን ሚስጥር የመረመሩ የፖለቲካ ምሁራንበአፍሪካ አገሮች የሚከሰቱ የቅድመ ምርጫ ግጭቶች ድንገቴ እንዳልሆኑ ደርሰውበታል።

የሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪ ሚካኤል ዋማንና ኢድዋርድ ጎልድረንግ ... 2020 የቅድመ ምርጫ ግጭቶችን በተመለከተው ‹‹Pre-Election Violence and Territorial Control›› በተሰኘ የምርምር ሥራቸው በናይጄሪያ፣ በኬንያ፣ በኮትዲቯርና በማሊ በተካሄዱ የቅርብ ዓመታት ምርጫዎች ላይ ጥናት በማካሄድ፣ በእነዚህ አገሮችም ሆነ የዴሞክራሲ መሠረት ባልተጠናባቸው ሌሎች የአፍሪካ አገሮች የሚከሰቱ ቅድመ ምርጫ ግጭቶች ታቅደውና በምርጫው ውጤት ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር ይበጃሉ ተብለው በፖለቲካ ኃይሎች ተነድፈው ጥቅም ላይ ይውላሉ የሚል ድምዳሜ ላይ አድርሷቸዋል።

በተለይ አጠቃላይ ምርጫውን በአገር አቀፍ ደረጃ ለማሸነፍ ከፍተኛ የፓርቲዎች ፉክክር በሚኖርበትና በአንፃሩ በክልል ደረጃ ያለን ምርጫ ለማሸነፍ የሚኖረው የፓርቲዎች ፉክክር ዝቅተኛ በሚከሰትበት፣ አጠቃላይ የምርጫ ምኅዳር ውስጥ ያለውን ክፍተት ለመሙላት ቅድመ ምርጫ ግጭቶች ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ተመራማሪዎቹ ያደረጉት ጥናት ያመላክታል።

የተገለጹት ዓይነት ሁለት የፉክክር ዓውዶች ተጣምረው በአንድ ምርጫ ወቅት ሲከሰቱ፣ የቅድመ ምርጫ ግጭቶችን ቀስቅሶ ጥቅም ላይ በማዋል ከፍተኛ ፉክክር በሚደረግበት አገር አቀፍ ምርጫ ላይ የመሸነፍ ክፍተቶችን ለመሙላት፣ ወይም የማሸነፍ አቅምን ለማጎልበት ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ይገልጻሉ። 

በመሆኑም ዝቅተኛ የፉክክር ደረጃ በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች የበላይነት ያላቸው ፓርቲዎች የበላይነታቸውን ለማስጠበቅ ግጭት በመቀስቀስ፣ በአካባቢው የሚወዳደሩ ሌሎች ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ እንዳያካሂዱ እክል እንዲፈጠር ያደርጋሉ፣ በበላይነት በሚቆጣጠሩት አካባቢ በምርጫ የሚሳተፉ ፓርቲዎችን ሊመርጡ የሚችሉ ነዋሪዎች በሥጋት ምክንያት ውሳኔያቸውን እንዲቀይሩ፣ ወይም በመራጭነት የሚሳተፈውን ነዋሪ በአጠቃላይ በፀጥታ ሥጋት ምክንያት በመራጭነት እንዳይሳተፍ ለማድረግ ግጭቶችን እንደሚጠቀሙ ያብራራሉ።

በሌላ በኩል በአገር አቀፍ ደረጃ ለማሸነፍ ጉልበት የፈጠሩ ወይም ቀደም ብለው በመንግሥት ሥልጣን ላይ የነበሩ ፓርቲዎች ያላቸውን መዋቅር በመጠቀም፣ በአካባቢያዊነት ቁጥጥር ሥር የወደቀ የፖለቲካ አካባቢን ሰብረው በመግባት ለአገር አቀፍ የምርጫ ፉክክር የሚያስፈልጋቸውን ድምፅ ለማግኘት ግጭትን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ያክላሉ። 

በአመዛኙ ግን ቅድመ ምርጫ ግጭቶች በአካባቢ ላይ ያላቸውን የቀደመ ቁጥጥር ለማስጠበቅ በሚታትሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አዘውትሮ ጥቅም ላይ ሲውል እንደሚታይ ይገልጻሉ። 

በተጨማሪም በምርጫ የሚፎካከሩ ኃይሎች የማሸነፍ አቅም ባልተመጣጠነባቸው አካባቢዎች፣ አዘውትረው ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚደረጉ መሆናቸውን ያስረዳሉ።

ከላይ በቀረበው የምርምር ግኝት የሚስማሙትና በኢትዮጵያ ምርጫዎችና ግጭቶች ላይ የተለያዩ ምርምሮችን ያደረጉት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የግጭት አፈታት ሥልቶች ተመራማሪ፣ በኢትዮጵያ በተለይም ላለፉት ሁለት ዓመታትና አሁንም እየተስተዋሉ ያሉ ግጭቶች ማጠንጠኛ በአመዛኙ ከጥናት ግኝቱ ጋር የሚስማማ እንደሆነ ይገልጻሉ።

በአሁኑ ወቅት እየተስተዋሉ ያሉ ግጭቶች በተለይ በናይጄሪያ አዘውትረው ከሚከሰቱ የምርጫ ወቅት ግጭቶች ጋር በእጅጉ የሚቀራረቡ መሆናቸውን የሚገልጹት እኚህ ባለሙያ፣ የዚህ ምክንያትም ናይጄሪያና ኢትዮጵያ ተቀራራቢ የፖለቲካ ሥሪት የሚከተሉ አገሮች ከመሆናቸው የሚመዘዝ መመሳሰል እንደሆነ ይጠቁማሉ። 

በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴንጎ ኦባ ሳንጆ የመጀመርያ የሥልጣን ዘመን ተከስተው ያለፉ ፖለቲካዊ ሁነቶች ጋር ተቀራራቢ እንደሆነ ይገልጻሉ። 

ናይጄሪያን ያስተዳድር የነበረው ወታደራዊ መንግሥት ተወግዶ ... 1999 ወደ ሥልጣን የመጡት የቀድሞው ኦሊ ሴንጎ ኦባ ሳንጆ፣ ለሁለተኛ የሥልጣን ዘመን ለውድድር በቀረቡበት ወቅት አስቀድሞ ከነበረው የባሰ የቅድመ ምርጫ ግጭት ... 2003 ተከስቶ እንደነበር ይገልጻሉ።

በወቅቱ በተካሄደው የምርጫው ፉክክር ውስጥ የተሳተፉት ጥቂት ፓርቲዎች ቢሆኑምየቅድመ ምርጫ ግጭቶቹም በእነዚሁ ፓርቲዎች መካከል በተለይም በወቅቱ አገሪቱን ይመራ በነበረው የኦባ ሳንጆ ፓርቲ አመራሮች መካከል የተፈጠሩ መገፋፋት ለቅድመ ምርጫ ግጭቱ አንዱ ምክንያት ሲሆንበተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከልም ግጭት እንደተካሄደ ይገልጻሉ።

በወቅቱ ከነበሩ የግጭት ባህሪያት መካከል የክልል ፖለቲከኞችን የሚመሩ የሚሊሻ ኃይሎች በሚሰጣቸው ተልዕኮ መሠረት ግድያዎችንና ማፈናቀሎችን ይፈጽሙ እንደነበር ያስረዳሉ። 

ግጭቶቹ በአንድ በኩል ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ ይመስላሉ፣ በሌላ በኩል ብሔርን መሠረት ያደረጉ ይሆናሉ፣ በተጨማሪም የተመረጡ ታዋቂ ሰዎችንና ፖለቲከኞች ላይ ያነጣጠሩ ግድያዎች በመፈጸም ይከናወኑ እንደነበር ባለሙያው ያስረዳሉ።

በናይጄሪያ አሁንም ቢሆን የምርጫ ወቅት ግጭት የቀረ አለመሆኑን፣ ነገር ግን በአገሪቱ ከተካሄዱት ያለፉ ምርጫዎች ጋር ሲነፃፃር እየቀነሰ መምጣቱን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የሚታዩ ግጭቶች መነሻ የምርጫ መቃረብ እንደሆነ የሚገልጹት እኚህ ባለሙያበናይጄሪያ እንደተስተዋለው ሁሉ በኢትዮጵያም የተከሰቱ የቅድመ ምርጫ ግጭቶች በሁለትሚከፈሉ ናቸው።

አንደኛው የግጭት ባህሪ ተፎካካሪ ፓርቲዎች አንዱ አንዱን ለማሸነፍ ሲሉ የሚቀሰቅሱት ሲሆንሌላኛው በአንድ ገዥ ፓርቲ ውስጥ በሚፈጠር የፖለቲካ ልዩነት ምክንያት የሚፈጠር ነው፡፡ መልክ ዓምድርን መሠረት ያደረገ የምርጫ ውጤት በማግኘት በፓርቲ ውስጥ የፖለቲካ የበላይነትን ለማግኘት ተብሎ የሚቀሰቀስ እንደሆነ ያስረዳሉ።

በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ሁለቱም የግጭት ባህሪያት ቢስተዋሉም፣ አሁን አሳሳቢ ሆኖ ብቅ ያለው በፓርቲ ውስጥ ያለውን ፉክክር በበላይነት ለመደምደም በመፈለግ የሚቀሰቀሱ አካባቢን መሠረት ያደረጉ ግጭቶች መሆናቸውን ይናገራሉ።

መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችሉ የወንበር ብዛቶችን በማስላት የሚቀሰቀሱ እንደሚመስሉ የሚናገሩት እኚሁ ባለሙያለዚህ ክርክራቸው ማስረገጫም ግጭቶቹ አንድ ቦታ ላይ የፀኑ አለመሆናቸውን ይጠቅሳሉ።

spot_img
- Advertisement -

ትኩስ ጽሑፎች

ተዛማጅ ጽሑፎች

- Advertisement -
- Advertisement -