Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየኦሮሚያ ክልል ምርጫው ያለ ሥጋት እንዲካሄድ እንደሚያደርግ አስታወቀ

የኦሮሚያ ክልል ምርጫው ያለ ሥጋት እንዲካሄድ እንደሚያደርግ አስታወቀ

ቀን:

በግንቦት ወር የሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መንገድ ያለ ምንም ሥጋት እንደሚካሄድ፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ የዜጎች ሞት፣ መፈናቀልና የሰላም ዕጦት በቀጣዩ ምርጫ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ከዚያም ሲያልፍ ዕጩዎቻቸውን በሚጠብቃቸው ልክ ማሳተፍ እንዳልቻሉ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲገልጹ ሰንብተዋል፡፡

ይሁን እንጂ በኦሮሚያ ክልል የፀጥታ መደፍረስ ሥጋት ለመጪው አገራዊ ምርጫ እንቅፋት እንዳይሆን በክልሉ ያሉ አመራሮች በስፋት እየተንቀሳቀሱና እየሠሩበት እንደሆነ፣ የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ግዛቸው ገቢሳ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በክልሉ በተለይም በምዕራብ ወለጋ ዞን ሦስት ወረዳዎችና በሆሮ ጉዱሩ ዞን አራት ወረዳዎች ጫካና ተራራን ተገን አድርገው የመሸጉና ለመሸሽ አመቺ የሆኑ ቦታዎችን ተጠቅመው ጥቃት የሚያደርሱ አካላትን፣ በመከታተል ዕርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በተጠቀሱት ቦታዎች መሽገው ጥቃት ከሚያደርሱት ሽፍታዎች በተጨማሪ ኅብረተሰቡ ወስጥ ሰርገው የገቡ፣ በድብቅ ማንነት የፖለቲካ አስተሳሰባቸውን የሚያራምዱና በድንገተኛ ጥቃት ጭፍጨፋ የሚያካሂዱ፣ ዘረፍ ላይ የተሰማሩ፣ ግለሰቦችን በማስፈራራት የአገር ሀብት ሲያወድሙ እንደነበር  አስታውሰዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ክልሉ እያደረገ ባለው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ሽፍታዎች በየቀኑ እየተለቀሙና በርካታ የጦር መሣሪያዎች በቁጥጥር ሥራ እየዋሉ እንደሆነ፣ መንግሥት የሕግ የበላይነትን እያስጠበቀ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን፣ ምርጫውን ያለ ምንም ሥጋት ለማካሄድ አመራሩ ከታች አስከ ላይ ተናቦ በመሥራት ላይ ነው ሲል ኃላፊው አክለው ተናግረዋል፡፡

እነዚህን ኃይሎች በማኅበራዊ ሚዲያ ስም ተሰጥቷቸው የልብ ልብ እንዲሰጣቸው ከማድረግ ባለፈ፣ አቅም የሌላቸውና ምንም ዓይነት መሠረት የሌላቸው፣ እርስ በርስ የማይተዋወቁ፣ እንዲሁም የማይግባቡ የተበታተኑ ኃይሎች ናቸው በማለት ምክትል ኃላፊው ገልጸዋቸዋል፡፡

ለአብነትም በቅርቡ ‹‹በምሥራቅ ወለጋ ነቀምት ከተማ አባ ቶርቤ በሚል ቅጥያ ስም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አካላት ከተደመሰሱ በኋላ የተፈጠረውን መረጋጋት ማየት ይቻላል›› ብለው፣ በአሁኑ ጊዜ የምርጫ ዝግጅት ሥራው በሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...