Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትበቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ የሚሳተፉ ክለቦች በገንዘብ ችግር መፈተን ቀጥለዋል

  በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ የሚሳተፉ ክለቦች በገንዘብ ችግር መፈተን ቀጥለዋል

  ቀን:

  በአውሮፓ የተለያዩ ሊጎች ላይ የሚሳተፉ ክለቦች በሚሳተፉበት ውድድር ላይ ተፎካካሪ ለመሆን ቡድኑን ምሉዕ ማድረግ ቀዳሚው ሥራ ነው፡፡ ለዚህም ተጫዋቾችን ከተለያዩ ክለቦች ማስፈረም የራሱ ሒደት አለው፡፡ በእግር ኳስ ገንዘብ ትልቅ አቅም ለመፍጠር ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡ በዓለም ላይ ትልልቅ ክለቦች ከእግር ኳስ በሚገኝ ገቢ አገራቸውን ሲጠቅሙ ይስተዋላል፡፡

  በተለያዩ አገሮች ሊጎች የሚሳተፉ ክለቦች በውድድር ዘመን የሚያመጡት ውጤት በካዝናቸው ካላቸው ገንዘብ ጋር ገላጭ ነው ተብሎ ይታመናል፡፡

  በ1990 ዓ.ም. ጀምሮ መከናወን የጀመረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አንድ ክለብ ከ10 እስከ 20 ሚሊዮን ብር ድረስ ወጪ ማድረግ ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ከዚህም ወስጥ ክፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው የተጫዋቾች ክፍያ ነው፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ክለቦች የተጫዋቾችን የወር ደመወዝ መክፈል ስለተሳናቸው ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ክስ ሲቀርብ ነበር፡፡

  የ2013 ዓ.ም. የቤትኪንግ ውድድር ከጀመረ በኋላ ጅማ አባ ጅፋር፣ አዳማ ከተማ፣ ሰበታ ከተማ እንዲሁም ሀዲያ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ክፍተኛ የገንዘብ ቀውስ የገጠማቸው ክለቦች ናቸው፡፡ ክለቦቹም ጨዋታ እስከማቆም አድማ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

  የፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር ውድድር ከጀመረ ወር አልፎታል፡፡ በቅርቡ ከባህር ዳር ወደ ድሬዳዋ የተዘዋወረው ውድድሩ ከጀመረ ሳምንት አልፎታል፡፡ በሊጉ ተሳታፊ የሆነው ሀዲያ ሆሳዕና በገንዘብ ችግር ምክንያት ለተጫዋቾቹ ደመወዝ መክፈል ባለመቻሉ ተጫዋቾች ቡድኑን ለቀው መበተናቸው ሲነገር ቆይቷል፡፡

  በዘንድሮ ውድድር ዓመት በርካታ ወይም ግማሽ በግማሽ በሚያስብል ዓይነት የአዳማ ተጫዋቾችን በማስፈረሙ ሲተች የነበረው ሀዲያ ሆሳዕና፣ ከተጫዋቾች ደመወዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ ውዝግብ ውስጥ ገብቷል፡፡ የሁለት ወር ደመወዝ አለመክፈሉ ቅሬታ የተነሳበት ክለቡ፣ ሰኞ ሚያዝያ 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ክፍያውን መፈጸሙ ቢጠቀስም ቀደም ብሎ ተጫዋቾቹ ክለቡ ሲቀላቀሉ ሊከፈላቸው የሚገባ ገንዘብ አለመከፈሉን ጠቅሰዋል፡፡ ይኼን ተከትሎም ከክለቡ ክፍተኛ ኃላፊዎች ጋር መምከራቸው ተጠቁሟል፡፡ በድሬዳዋ እየተሳተፈ የሚገኘው ሀዲያ ሆሳዕና በቅርቡ ችግሩን ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

  ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከታችኘው ሊግ ወደ ፕሪሚየር ሊግ የሚያድጉ ክለቦች፤ ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾች እንቅጠር በሚል የዳቦ ስም፤ ወደ ላኛው ሊግ ያሳደጓቸውን ተጫዋቾች ጥለው ሌሎችን ለማስፈረም በሚሊዮን ረብጣ ብሮችን ሲያወጡ ይስተዋላል፡፡  ይኼም ክለቦችን ለከፍተኛ ዕዳ ሲያጋልጣቸው ማየቱ የተለመደ ነው፡፡

   በአንጻሩ በክለቡ ወስጥ ታዳጊዎችን መያዝ፣ ለወጣቶች ዕድል መስጠትና የክለቦቻቸውን መዋቅር ማስተካከል ላይ እምብዛም በመሆናቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመፍረስ ይዳረጋሉ፡፡

  በሌላ በኩል አንድ አሠልጣኝ ወደ አንድ ክለብ ሲዘዋወር ተጫዋቾችን ቀድሞ ከነበረበት ክለብ ይዟቸው የሚያዞራቸው ተጫዋቾች መኖራቸው እየተለመደ የመጣ ነገር ነው፡፡ ይኼም የክለቦችን ካዝና ከማራቆት ባሻገር አሠልጣኝ ከተጫዋች ጋር የሚኖረውን የጥቅም ትስስር የሚያጎለበት እንደሆነ  አስታየታቸውን የሚሰጡ አሉ፡፡

  ዘንድሮ በቴሌቪዥን መስኮት የመተላለፍ ዕድል ያገኘው ፕሪሚየር ሊጉ 18ኛ ሳምንቱን ይዟል፡፡ በአንጻሩ በተወሰኑ ክለቦችና ተጫዋቾች መካከል የተፈጠረው የደመወዝ ክርክር ውዝግብ የሊጉን በጎ ገጽታ እንዳያጠለሽ የብዙኃን ፍራቻ ነው፡፡       

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...