Monday, March 20, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የሮሃ ሕክምና ማዕከል ግንባታ ጅማሮ

ትኩስ ፅሁፎች

በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በዓድዋ ፓርክ ሜዳ ላይ ያርፋል ለተባለው ሮሃ የሕክምና ማዕከል ሚያዚያ 2 ቀን 2013 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ ምክትል የከተማ አስትዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዮሐንስ ጫላ (ዶ/ር) እንዲሁም የሮሃ ሕክምና ማዕከል መሥራች ሚስተር ብሮክ ዋሽንግተን የመሠረት ድንጋይ አኑረዋል፡፡ ሆስፒታሉ በዓመት ከ100 ሺሕ በላይ ታካሚዎች ያስተናግዳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ከአገር ውስጥ ዜጎች በተጨማሪ ከውጭ ለሚመጡ ቱሪስት ታካሚዎች የሚያገለግል መሆኑ ተገልጿል፡፡ ማዕከሉ አምስት የተለያዩ ሆስፒታሎችን የሚይዝ ከመሆኑ በተጨማሪ፣ ከኢትዮጵያ ወደ ውጭ አገሮች ሄደው ለሚታከሙ ዜጎቿ  በዓመት የምታወጣውን 400 ሚሊዮን ዶላር ያስቀራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በ300 ሚሊዮን ዶላር (12 ቢሊዮን ብር) ወጪ የሚገነባው የሕክምና ማዕከል፣ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ከ15 በላይ ስፔሻሊት፣ ሰብስፔሻሊቲ ምርምርና የሥልጠና የልህቀት ማዕከል ይኖረዋል፡፡ አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል የሚያደርግ ነውም ተብሏል፡፡ የልብ፣ የጭንቅላት፣ የጀርባና አጥንት ሕክምና፣ የካንሰር እንዲሁም ዘርፈ ብዙ የሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡ ግንባታው አምስት ዓመት የሚፈጅ ነው፡፡

የሮሃ ሕክምና ማዕከል ግንባታ ጅማሮ

የሮሃ ሕክምና ማዕከል ግንባታ ጅማሮ

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች