Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበኮሮና ወረርሽኝ ላይ ያተኮረ የዳሰሳ ጥናድ ሊካሄድ ነው

በኮሮና ወረርሽኝ ላይ ያተኮረ የዳሰሳ ጥናድ ሊካሄድ ነው

ቀን:

በኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝ ሥርጭት ላይ ትኩረት ያደረገ አገራዊ ዳሰሳ በሁሉም ክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች እንደሚካሄድ በጤና ሚኒስቴር የኮሮና ወረርሽኝ ጥናትና ምርምር ግብረ ኃይል አስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

የኮሚቴው ሰብሳቢ አበባው ገበየሁ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ከሚያዝያ 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ወር ያህል የሚካሄደው የዚሁ ጥናት ዋና ዓላማ፣ በወረርሽኝ የተጠቁ የማኅበረሰብ ክፍሎችን በአካባቢ፣ በፆታና በዕድሜ ለይቶ ለማወቅ እንዲሁም ምልክት ሳያሳዩ ታመው የነበሩ ሰዎች ምን ያህል ናቸው የሚሉ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ነው፡፡

ጤና ሚኒስቴር ከኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ከሚያካሂዱት  ጥናት የሚገኘው መረጃ በንፅፅር ታይቶ የበሽታው ሥርጭት ብዙ ያልደረሰባቸውን አካባቢዎችና የኅብረተሰብ ክፍሎች በመለየት ተገቢ ዕርምጃ ለመውሰድ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ለወረርሽኙ ተጋላጭ የሆኑና ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች በመለየት ቅድሚያ ክትባት እንዲያገኙ በማድረግ ረገድም ከጥናቱ የሚገኘው መረጃ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተነግሯል፡፡

እንደ ሰብሳቢው ማብራሪያ፣ በአሁኑ ጊዜ በመካሄድ ላይ ያለውን የክትባት ሥራ አጠናክሮ ለመቀጠል የጥናቱ መጀመር ጥሩ አጋጣሚ ሆኗል ተብሎ ይታሰባል፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዓምና ባከናወነው የአቅም ግንባታ ሥልጠናና ያለጥቅም የተቀመጡ ማሽኖችን ቶሎ ወደ ሥራ በማስገባት የአገሪቱ የምርምር አቅም ከፍ እንዲል አድርጓል፡፡

ከዚህም ሌላ የግል ጤና ተቋማት በኮሮና ወረርሽኝ ላይ ምርመራና ሕክምና ሥራ ውስጥ በመሳተፋቸው ጉልህ ድርሻ እንዳበረከቱ፣ በአሁኑ ጊዜ ያለው የአገሪቱ የመመርመር አቅም አፍሪካ ውስጥ ከደቡብ አፍሪካና ከሞሮኮ ቀጥሎ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡

የዛሬ ዓመት መንግሥትና ሕዝብ እጅና ጓንት ሆኖ በሽታውን ለመመከት ያሳየው ትብብር ለተወሰነ ጊዜ ዕድል እንደሰጠ፣ ሌሎች አገሮች በተጠቁት ልክ ኢትዮጵያ አለመጠቃቷም ተቋማትን ለማዘጋጀትና ባለሙያዎችን ለማሠልጠን ትንፋሽ እንደሰጠም ተነግሯል፡፡

ነገር ግን በተፈጠረው አገራዊ ፈተናና በኅብረተሰቡ መዘናጋት የተነሳ በሽታው በጣም በሚያስፈራ ሁኔታ እንደገና መሠራጨት እንደጀመረ፣ በዚህም የተነሳ የጤና ተቋማት በታካሚዎች መጨናነቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ አኳያ የመከላከሉ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና ኅብረተሰቡም ዓምና ያሳያውን ዓይነት ጥንቃቄ አሁንም እንዲቀጥልበት ሰብሳቢው አበክረው አሳስበዋል፡፡

ዶ/ር አበባው እንዳሉት፣ ግብረ ኃይሉ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ዓምና ለስድስት ወራት ያህል በ15 ከተሞችና በሁሉም ክልሎች የኅብረተሰቡን የእጅ ንፅህና አጠባበቅ፣ ማስክ አጠቃቀምና ርቀት መጠበቅ ላይ ትኩረት ያደረገ ክትትል አድርጓል፡፡ በክትትሉ የማስክ አጠቃቀም ወደ 46 በመቶ፣ ርቀትን መጠበቅ 20 በመቶ፣ የእጅ መታጠብ ደግሞ ከአሥር በመቶ በታች ሆኖ ተገኝቷል፡፡

በተለይ በምግብና መጠጥ ቤቶች፣ በገበያ ቦታ፣ በሃይማኖት ተቋማትና በየመንገዱ የኅብረተሰቡ የማስክ አጠቃቀም በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ፣ በባንክና በጤና ተቋማት ሠራተኞች  ዘንድ አጠቃቀሙ የተሻለ ሆኖ እንደተገኘ፣ ትምህርት ቤቶች ከተከፈቱ በኋላ ተማሪዎች ማስክ በጥንቃቄ እንዲጠቀሙ ተደርጎ እንደነበርና ከዚህ አኳያ በአንድንድ ትምህርት ቤቶች የማስክ አጠቃቀም 79 በመቶ እንደነበር፣ በአሁኑ ጊዜ ግን ወደ 76 በመቶ ዝቅ ማለቱንም ጠቁመዋል፡፡

ከክልል ከተሞች አንፃር ሲታይ በአዲስ አበባ የተሻለ የማስክ አጠቃቀም ሲታይ አሰላ፣ አዳማና ጅማ ከተሞችም እንዲሁ የተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

ሌሎች ከተሞች ማለትም ሰመራ፣ ባህር ዳር፣ ሐረር፣ ጋምቤላ፣ ሐዋሳ፣ ወላይታሶዶና ጂግጂጋ ከተሞች የማስክ አጠቃቀማቸው ዝቅተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አማካሪና የግብረ ኃይሉ ኃላፊ ወ/ሮ ሰሮ አብደላ፣ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ቤት ለቤት በሚካሄደው በዚሁ የዳሰሳ ጥናት 160 መረጃ ሰብሳቢዎች እንደሚሰማሩ፣ ሰብሳቢዎቹም የሁለት ቀናት ሥልጠና እንደሚያገኙ ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...