Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየወርቃማው ዘመን ሙዚቃ አንጓ አየለ ማሞ

የወርቃማው ዘመን ሙዚቃ አንጓ አየለ ማሞ

ቀን:

በኢትዮጵያ የዘመናዊ ሙዚቃ ጉዞ የ1950ዎቹና 1960ዎቹ ሥራዎች ገናን በመሆናቸው ወርቃማው ዘመን የሚል ቅጽልን አትርፈዋል፡፡ በዚህ ዓረፍተ ዘመን ስማቸው የገነነው እነ ጥላሁን ገሠሠ፣ እነ ብዙነሽ በቀለ ይጠቀሳሉ፡፡ ለዘመኑ ልዕልና አስተዋጽዖ ካደረጉት ጋር የሙዚቃ ባለሙያዎች የዜማና ግጥም ፈጣሪዎችና አቀናባሪዎች እንዲሁም የክብር ዘበኛ፣ የፖሊስ ሠራዊት፣ የምድር ጦርና የሌሎች የሙዚቃ ክፍሎችም መሳ ለመሳ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በዚያ ወርቃማ ዘመን ከነበሩት አስተዋዋቂዎች አንዱ፡-

‹‹ጥላሁን ገሠሠ ዘፈኑ ነገሠ

 ብዙነሽ በቀለ ድምፅ እንዳንቺ የለ

 ተፈራ ካሳ ድምፀ ለስላሳ

 እሳቱ ተሰማ ድምፁ የተስማማ

 ማሕሙድ አህመድ ድምፀ ነጐድጓድ…›› እያለ ሲያስተዋውቅ መኖሩ የዘመኑ ሙዚቃ ነፀብራቅ የሚያሳይ ነው፡፡

ለዚህ ወርቃማ ዘመን ስኬት አስተዋፅዖ ካደረጉት መካከል የዜማና ግጥም ደራሲው አየለ ማሞ ከግንባር ቀደምቱ ተርታ ይሰለፋል፡፡ ኪነጠቢቡ አየለ ማሞ ገናና በሆነበት የዜማና ግጥም ደራሲነቱ ብቻ አይደለም የሚታወቀው፣ ማንዶሊን በሚባለው የሙዚቃ መሣርያ ተጫዋች፣ ድምፃዊ፣ ተወዛዋዥና የተወዛዋዥ አሠልጣኝነቱም ይታወቃል፡፡ 

 1934 .ም. ጥር 12 ቀን በቀድሞው አጠራር በሸዋ ጠቅላይ ግዛት፣ ሰላሌ አውራጃ ልዩ ስሙ ሳላይሽ ጊዮርጊስተወለደው አየለ ማሞ፣ ዕድገቱ በአዲስ አበባ ሲሆን በአዲስ አበባ ደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን በዲያቆንነት አገልግሏል፡፡

የወርቃማው ዘመን

 

በታዋቂው የሙዚቃ ሰውና ገጣሚና ደራሲ ሻምበል ዮሐንስ አፈወርቅ አማካይነት በ1949 ዓ.ም. በክብር ዘበኛ ኦርኬስትራ በድምፃዊነት ተቀጥሮ ለዘመናት አገልግሏል፡፡ አየለ ከድምፃዊነት ባሻገር ከተወዛዋዥነት እስከ ተወዛዋዦች አሠልጣኝነት ደርሷል፡፡

ገጸ ታሪኩ እንደሚያሳየው፣ በማንዶሊን ለመጀመርያ ጊዜ የዘፈነውን በልዩ መለያነት የሚታወቅበትን ‹‹ወይ ካሊፕሶ…›› ግጥምና ዜማ የሰጡት ሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ ናቸው።

‹‹ወይ ካሊፕሶ ካሊፕሶ ወይ ካሊፕሶ

ወይ ካሊፕሶ የአማራ ካሊፕሶ

ሰው ከሥራ እቤቱ ተመልሶ

የክት ልብሱን በሚገባ ለብሶ

አታሞውን አደራጅቶ ደግሶ

መደሰት አለበት በካሊፕሶ››

(ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ‹‹የአማራ ካሊፕሶ›› የምትለዋን ሐረግ ‹‹የሐበሻ ካሊፕሶ›› ሆና እየተዘፈነች ነው፡፡)

አየለ ማሞማንዶሊን የሙዚቃ መሣርያ ጋር የተዋወቀው በሙዚቃ ክፍሉ ውስጥ ሻለቃ ግርማ ሐድጎ ሲጫወቱ ባየ ጊዜ ነበር፡፡ በኋላ ላይ ሻምበል ዮሐንስ አፈወርቅማንዶሊን አጨዋወትን ከጣሊያናዊ ሲማሩ ማንዶሊኗን ይዞ አብሯቸው ይሄድ እንደነበር እሳቸው ተምረው ሲጨርሱም ማንዶሊኗን ይዞ ሲመለስ እሳቸው እንደሚያደርጉት እያደረገ መለማመድ ጀመረ ይላል ስለ አየለ ማሞ የተጻፈው ዜና ሕይወት፡፡

ባጠናው የማንዶሊን አጨዋወት በርካታ ድምፃውያንን ከጥላሁን ገሠሠ ጀምሮ አጅቧል፡፡ በግጥምና ዜማ ደራሲነቱም ከጥላሁን ገሠሠ፣ ብዙነሽ በቀለ፣ ማህሙድ አህመድ ጀምሮ እስከ ኅልፈቱ ድረስ ለበርካታ ድምፃውያን የአማርኛና ኦሮምኛ ግጥምና ዜማ ደርሷል፡፡

ጥላሁን ‹‹ጠይም ናት ጠይም መልከ ቀና፣ ይገርማል ቁመናና ዛላሀገር በነፃነት ኮርታ ስትኖር ነውብደሰት ብከፋም ቢመጣ መከራ፣ ለውዲቷ ለእናት ኢትዮጵያ፣ ወዘተ፣ ከአብዮታዊ ዘፈኖች መካከል፡-

 ‹‹አባረህ በለው ያንን አመፀኛ ተገንጣይ ወንበዴ

 መድረሻ አሳጣው አስኪደው በዳዴ›› ይጠቀሳል፡፡

ጥላሁን የመጨረሻው ሥራው እንደሚሆን አስቦት የነበረው ግን ሞት ስለ ቀደመው ያልፈጸመው የምስጋና መዝሙር፡-

‹‹ምስጋና ላቅርብ በዝማሬ ይድረስልኝ

 በዓለምና ለዘላለም ክበርልኝ›› የአየለ ማሞ ሥራ ነበር፡፡

ለብዙነሽ በቀለ ‹‹አምሮበታል ሙሽራው›› ለማህሙድ አህመድ ‹‹ያባብላል ዓይኗ ያባብላል፣ ንገሯት መላ ትስጠኝ፣ ለሕብስት ጥሩነህ ‹‹እንቡጥ ኝ፣  እናቴን አደራ›› ይጠቀሳሉ፡፡

ከማንዶሊን ውጪ ቤዝ ጊታርና ሊድ ጊታርም መጫወት የሚችለው አየለ ማሞስድሳ አራት ዓመታት በፊት ክብር ዘበኛ ሙዚቃ ክፍልን ሲቀላቀል በመጀመሪያ የተጫወተውና የተፈተነበትን ‹‹የእኔ ውብ ዓይናማ›› ዘፈን እንደነበር፣ ከዚያም ‹‹ያለሰለሴ ባዬቲ›› (ኦሮምኛ)‹‹እማማ ድንቡሎ›› የተሰኘጉራጊኛ ዘፈንመድረክ ላይ መጫወቱ ይወሳል፡፡

አየለ ማሞ ክቡር ዘበኛ ውስጥ ድምፃዊ ብቻ አልነበረም፡፡ ተወዛዋዥም ጭምር እንጂ፡፡ ከተወዛዋዥነትም አልፎ እስከ አሰልጣኝነት ዘልቋል፤ በርካታ ሙያተኞችንም አፍርቷል፡፡

‹‹ሳቅ ፈገግታ ደስታን ሁሌ የምናየው ሁሌ የምናየው፣

ሀገር በነፃነት ኮርታ ስትኖር ነው ሁሉም የሚያምረው››

ኪነጠቢቡ አየለ ማሞ፣ ‹‹ክብር ዘበኛ›› ወደ ማዕከላዊ ዕዝ ከተለወጠ በኋላና ከሦስት አሠርታት በፊት የነበረውን የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ ተቋሙ ሲቆም የክስታኔ ባንድን በመቀላቀል ከወጣት አርቲስቶች ጋር መጫወቱን ገጸ ታሪኩ ያሳያል፡፡እነ ግሩም መዝሙር፣ ሔኖክ ተመስገን አዲስ አኩስቲክ የሙዚቃ ባንድ ጋር ‹‹ትውስታ›› በሚል መርሐ ግብር በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ተጫውቷል።

ይህም መሰናዶ በ1950ዎቹና በ60ዎቹ ከነገሡት የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ትሩፋቶች መካል ዘመን ከተደመጡት ሙዚቃዎች መካከል በአዲስ አኩስቲክ ባንድ አማካይነት በጥበባዊ የጃዝ ሙዚቃ ቅላፄ ሲቀናበሩ አንዱ ተግባሪ አየለ ማሞ ነበር፡፡ የጃዝ ሙዚቃ ቡድኑ በአዲስ አበባ ጣይቱ ሆቴል በየሳምንቱ ዓርብ መሰናዶውን ባቀረበበት ጊዜያት ሁሉ አየለ አልተለየም፡፡

ሁለገቡ ኪነጠቢብ አየለ ማሞ ባደረበት ሕመም በ79 ዓመቱ ያረፈው መጋቢት 29 ቀን 2013 .ም. ሲሆን ሥርዓተ ቀብሩ በማግስቱ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...