Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናምርጫ ቦርድ ካቀዳቸው የምርጫ ጣቢያዊች መካከል ግማሹ ብቻ የመራጮች ምዝገባ እያደረጉ ነው

ምርጫ ቦርድ ካቀዳቸው የምርጫ ጣቢያዊች መካከል ግማሹ ብቻ የመራጮች ምዝገባ እያደረጉ ነው

ቀን:

ግንቦት 28 ቀን 2013 .. እንዲከናወን ዕቅድ ለተያዘለት ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ 50 ሺሕ ገደማ የምረጫ ጣቢያዎች እንዲመሠረቱ የታሰበ ቢሆንም በፀጥታና ሌሎች ምክንያቶች ሳቢያ የተቋቋሙና የመራጮች ምዝገባን እያደረጉ ያሉት የምርጫ ጣቢያዎች ቁጥር 25,151 ብቻ እንደሆኑ ቦርዱ አስታወቀ፡፡

ቦርዱ የመራጮች ምዝገባን በተመለከተ ሚያዚያ 6 ቀን 2013 .. ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል የመራጮች ምዝገባን አስመልክቶ ባካሔደው የምክክር መድረክ ላይ የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ /ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ እንዳስታወቁት፣ ምርጫ ጣቢያዎቹ ሥራ ያልጀመሩባቸው በዋናነት የፀጥታና የቁሳቁስ ማጓጓዝ ችግሮች ሳቢያ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

በተለይ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በአማራና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ያሉ የምርጫ ጣቢያዎችን ለማቋቋም በክልሎቹ የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የፀጥታ ችግሮች ፈተና እንደሆኑ ተነግሯል፡፡

በአፋርና በሶማሌ ክልሎች የፀጥታና የዕቃ ማጓጓዝ ችግሮች በመታየታቸው ሳቢያ ምንም የምርጫ ጣቢያዎች አለመቋቋማቸውና የመራጮች ምዝገባም እንዳልተጀመረ ተነግሯል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...