Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልየአዲስ አበባ ቅርሶችና የዓለም ቅርስ ቀን

የአዲስ አበባ ቅርሶችና የዓለም ቅርስ ቀን

ቀን:

በምሕፃሩ ዩኔስኮ ተብሎ የሚጠራው ዓለም አቀፉ የባህል ተቋም፣ በየአገሩ የሚገኙትን ጥንታዊ ቅርሶች ተገቢው ክብካቤ እንዲያገኙ፣ ይበልጥም እንዲጠበቁ የሚያነቃቃ የኅብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲሰፋ ለማድረግ በየዓመቱ ሚያዝያ 10 ቀን (አፕሪል 18) የዓለም ቅርስ ቀን ተብሎ በአባል አገሮቹ እንዲከበር ደንግጓል፡፡

ስብጥር ባህላዊ ገጽታዎችን፣ የባህል ብዝኃነትን ሁሉም እንዲያከብሩ ለማድረግ በተመሠረተው የዓለም ቅርስ ቀን አማካይነት በተለይ ወጣቱ ትውልድ ቅርስና ውርሱን አውቆ እንዲዘልቅ ለማድረግም ታልሞበታል፡፡

ክብረ በዓሉ የታሪክና የባህል አካል ስለሆኑት ሐውልቶችና ሌሎች ቦታዎች እንዲሁም ጥንታዊ ቤቶችን በተመለከተ ለኅብረተሰቡ ስለ ቅርስ ጥበቃና ክብካቤ ግንዛቤ ማስጨበጫ መሰናዶዎች፣ ጉብኝቶችና ተያያዥ ሥራዎች ይከናወንበታል፡፡

- Advertisement -

 የዘንድሮው በዓል በዓለም ዙሪያ በባህልና ቅርስ ተኮር መንግሥታዊም ሆኑ ያልሆኑ ተቋማትና ማኅበራት አማካይነት መሪ ቃሉን ‹‹የባህል ብዝኃነትና የጋራ ቅርሶችን መጠበቅ የጋራ ኃላፊነት›› በማድረግ ያከብሩታል፡፡ መካነ ቅርሶቻቸውንም ያስተዋውቁበታል፡፡

የዘንድሮውን የዓለም ቅርስ ቀን በመሪ ቃሉ መሠረት የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮና የኢትዮጵያ ቅርስ ባለ አደራ ማኅበር በጋራ እንደሚያከብሩት በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ቅርሶችና የዓለም ቅርስ ቀን

በከተማዋ የሚገኙ ቅርሶችን በባለቤትነት ከመጠበቅና ከመንከባከብ አንፃር ከመሥራት ባለፈ ኅብረተሰቡ ስለቅርሶች ግንዛቤ እንዲኖረው ለማስቻል የቅርስ ቀን መከበሩ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

የቅርስ ቀን ከዛሬ ሚያዝያ 10 ቀን እስከ ሚያዝያ 12 ድረስ በእግር ጉዞ፣ በጉብኝትና ‹‹መሠረተ ልማትና ቅርስ›› በሚል ርዕስ በሚዘጋጅ የመድረክ ውይይት እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

መንግሥታዊ ያልሆነው የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር ሃቻምና የዓለም ቅርስ ቀንን ለመጀመርያ ጊዜ በጽሕፈት ቤቱ ባዘጋጀው የፎቶግራፍ ዐውደ ርዕይ ያከበረው፣ ‹‹ ታሪክን እንዘክር፣ ባህላችንን እናወድስ፣ ስለ ቅርሶቻችን እናውራ፣ ማንነታችንን እንጠብቅ፣ የቀደሙ አባቶቻችንን እናመስግን›› በማለት እንደነበር ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር ቅርስ የማስጠበቅ ጉዞና ፈተናዎቹ

የተፈጥሮ፣ የታሪክና የባህል ቅርሶችን ለመጠበቅና ለመንከባከብ እየሠራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር (ኢቅባማ) የሦስት አሠርታት ዕድሜን አስቆጥሯል፡፡ ማኅበሩ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው በቅርስነት የተመዘገበውን የራስ ከበደ መንገሻ ነባር ቤትን ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ 1996 .. ተረክቦ ታሪካዊ ቅርስነቱን በጠበቀ መልኩ ጥገና በማድረግ በጽሕፈት ቤትነት እየተገለገለበት ይገኛል፡፡

ይሁን እንጂ፣ ከማኅበሩ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው፣ በአዲስ አበባ የዘመን አሻራን የያዙ የተወሰኑ ታሪካዊ ቤቶች በየዘመኑ ከመኖር ወደ አለመኖር እየተቀየሩ ናቸው፡፡ ቀደም ባሉት ዓመታት የሻቃ በልሁ ቤት (ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን አጠገብ የነበረ) የደጃዝማች ብሩ ኃይለማርያም ቤት (ከጣሊያን ምህርት ቤት ጀርባ የነበረ) ራስ ናደው ከሠሯቸው ቤቶች አንዱ (ከሊሴ ገብረ ማርያም ትምህርት ቤት ጀርባ የነበረ) የወ/ ስንዱ ገብሩ ቤት (ልደታ አካባቢ የነበረ) እና ሌሎችም ጥንታዊ ቤቶች ፈርሰዋል፡፡ ዘንድሮን ጨምሮ በሁለት ዓመታት ውስጥ ጥንታዊ ሕንፃዎች በ‹‹ልማት›› ስም ከመፍረስ የታደጋቸውም የደረሰላቸውም መንግሥታዊ ተቋም የለም፡፡

ከወራት በፊት ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደውና ‹‹የማንነታችን መገለጫና የታሪካችን ምስክር የሆኑ ጥንታዊ ቤቶች በቅርስነት ተጠብቀው እንዲቆዩ የተለያዩ ጥረት አድርጌያለሁ፤›› የሚለው የቅርስ ባለአደራ ማኅበር፣ ከእነዚህ መካከል የእቴጌ ጣይቱ ሆቴል ለግለሰብ እንዲሸጥ ሲደረግ ሆቴሉን የገዛው ሰው ሆቴሉን በነበረበት ሁኔታ ጥንታዊ ቅርፁን ተንከባክቦ እንዲይዘው ግዴታ ከሚያስገባ ውል ጋር እንዲገዛ አሳስቦ ተቀባይነት ማግኘቱ ይገኝበታል፡፡

ኢቅባማ፣ ታሪካዊ ቅርሶችን ለመጠበቅ በግንባር ቀደምትነት ካከናወናቸው ተግባራት ውስጥ የሚጠቀስለት፣ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት የተገነባው የአዲስ አበባው ለገሃር ባቡር ጣቢያ ሕንፃ፣ በመንገድ ሥራ ምክንያት እንዲፈርስ በተደገሰለት ጊዜ ማኅበሩ ትልቅ ጉባዔ በማዘጋጀትና በቅርስ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ በምሁራን እንዲቀርብ ማድረጉ ነው፡፡ ለገሃር ባቡር ጣቢያ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር ምን ያህል ትስስር እንዳለውና ለዘመናዊው ሥልጣኔ መግቢያ ታሪካዊ ቅርስነቱን የሚያጎሉ ሐሳቦች እንዲንሸራሸሩና ውይይት እንዲካሄድባቸው ያስቻለው መድረክ ባለሥልጣናቱን ስላሳመናቸው ጥንታዊው ሕንፃ እንዳይፈርስ አስደርጓል፡፡

በሌላ በኩልም በአዲስ አበባና ለተለያዩ ከተሞች ጥንታዊ ቤቶችና አብያተ መንግሥት ላይ ጥናት አካሂዷል፡፡  በየካና በአራዳ በሚገኙ 73 ቤቶች ላይ የኢንቬንተሪ ሥራ አካሂዶ በየክፍለ ከተሞቹ በቅርስነት መመዝገባቸው፣ በድሬዳዋ ከተማ ከሚገኙ ጥንታዊ ቤቶች ውስጥም 35 በቅርስነት አስመዝግቧል፡፡ ታሪካዊ ቤቶች አንዱ የሆነው የልጅ ያሱ መኖሪያ ቤት በመልሶ ማልማት ሳቢያ እንዲፈርስ ተወስኖበት ማኅበር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ቤቱን ከመፍረስ አድኖ በአሁን ወቅት በሙዚየምነት እንደሚያገለግል አውስቷል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው 88 ዓመት ዕድሜ ያለውና በቅርስነት የተመዘገበው ‹‹ሉምባርዲያ ሆስቴል›› በመባል የሚታወቀው የሼህ አህመድ ሳላህ ሕንፃን የልደታ ክፍለ ከተማ ሊያፈርሰው ሲነሳ፣ ማኅበሩ ከሁለት መንግሥታዊ ተቋማትና ከሕንፃው ወራሾች ጋር በመሆን በተለያዩ ፍርድ ቤቶች በመቅረብ እንዳይፈርስ ጠንካራ ክርክር በማድረግ እስካሁን ሕንፃው ዕድሜ እንዲያገኝ አድርጓል፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም ጥንታዊውንና ታሪካዊውን ቤት የማዳኑ ክርክር መቀጠሉንም ሳይገልጽ አላለፈም፡፡

እንደ ቀደሙት ዓመታት ታሪካዊ ቅርሶችን ለማስጠበቅ ያከናወነው ተግባርም አሁንም የማኅበሩ አጀንዳ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በኢትዮጵያ የመጀመርያው ሲኒማ ቤት እንደሆነ በታሪክ የሚነገርለት ‹‹ሰይጣን ቤት›› እነ አንበሳ ፋርማሲ ሊፈርሱ ነው የሚል መረጃ የደረሰው ማኅበሩ፣ የሚመለከታቸውን ኃላፊዎችና የአዲስ አበባ ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮን በማነጋገር ቅርሱ እንዳይፈርስ አስተዋጽኦ ማድረጉም ተወስቷል፡፡

የባለአደራው ማኅበር ጽሕፈት ቤት ሆኖ እያገለገለ የሚገኘው በቅርስነት የተመዘገበው የራስ ከበደ መንገሻ ቤትን በሚመለከት፣ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ያቀረበው ‹‹ይገባኛል›› ጥያቄ ማኅበሩ መደበኛ ተግባሩን እንዳያከናውን ከፍተኛ ሁከት እንደፈጠረበት በጠቅላላ ጉባዔው ወቅት ፕሬዚዳንቱ መጠቆማቸውና ‹‹ሁከት ይወገድልኝ›› በሚል ክስ በመመሥረትና ከጠበቃ ጋር ውል በማድረግ ክርክሩ መቀጠሉንም መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ቅርሶችን ለመታደግ ከፍተኛ ፍላጎት ያደረባቸው ሁለት የአንጋፋና የወጣት የቅርስ ተሟጋች ቡድኖች በአንድ ላይ በመቀናጀት ነበር የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበርን (ኢቅባማ) በሚያዝያ 1984 መመሥረታቸው ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...