Sunday, April 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየሕክምና ዘርፉን የሚያግዘው አፍሪካዊ ማዕከል

የሕክምና ዘርፉን የሚያግዘው አፍሪካዊ ማዕከል

ቀን:

በኢትዮጵያ ጠንካራ የሕክምና አገልግሎት ለመፍጠር ጅማሬዎች ቢኖሩም፣ መሬት ወርዶ የተሠሩ ሥራዎች ባለመኖራቸው ምክንያት የሕክምና ዘርፉ ፈተና ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል፡፡

ይኼንን ችግር ለመፍታት የዓለም ጤና ድርጅት ከጤና ሚኒስቴር ጋር ስምምነት በመፈጸም፣ አዲስ አበባ በሚገኘው የኮቪድ-19 የፊልድ ሆስፒታል ውስጥ የአፍሪካ ድንገተኛ አደጋዎች ማሠልጠኛ ማዕከል በማቋቋም ሥልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡

የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር)፣ በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ማቲሾ ሞኤቲ (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች የሕክምና ዘርፉ ላይ ያሉ የአፍሪካ አገር ባለሙያዎች ተገኝተው ሚያዝያ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ሥልጠናው መጀመሩን አብስረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የጤና ሚኒስትሯ እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ እየተከሰተ ያለውን ሰው ሠራሽም ሆነ የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመከላከልና ጠንካራ የሆነ የድንገተኛ ሕክምና ምላሽ ለመስጠት ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡

በተለያዩ ዘርፎች ላይ ያሉ የሕክምና ባለሙያዎችን እንደ አንድ ቡድን በመመደብ ሥልጠናዎችን እንዲወስዱ የሚደረግ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ፣ በሥልጠናው ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የተውጣጡ የሕክምና ባለሙያዎች እየተሳተፉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ የሕክምና ዘርፉ ጠንካራ የሆኑ አሠራሮች እንዲኖሩት ላለፉት ሦስት ዓመታት የተለያዩ ሥልጠናዎችን በመስጠት ሰፊ ሥራ መሥራቱንና እነዚህንም ሥራዎች አጠናክሮ ለመቀጠል የአፍሪካ ድንገተኛ አደጋዎች የሥልጠና ማዕከል ጉልህ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ዶ/ር ሊያ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የአሠልጣኞች ሥልጠና እየተካሄደ መሆኑን፣ ይኼንንም ተከትሎ በሥልጠናው ላይ የሚሳተፉ የሕክምና ባለሙያዎች ምን ያህል እንደሆኑ ለማወቅ በጤና ሚኒስቴርና በዓለም ጤና ድርጅት በኩል ዝርዝር መረጃዎች እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በሕክምና ዘርፉ ላይ ያሉትን ችግሮች ለመቅርፍና መሠረታዊ ለውጦችን ለማምጣት የሥልጠና ማዕከሉ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው፣ በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ሞኤቲ ተናግረዋል፡፡

የሕክምና ባለሙያዎች ያላቸውን ልምድ በመለዋወጥ፣ ክህሎታቸውን በማሳደግና የድንገተኛ አደጋ ምላሽን የመስጠት አቅምን ማጎልበት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር የድንገተኛና ፅኑ ሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር አለኝታ  ገብረየሱስ (ዶ/ር) እንዳሉት፣ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የሕክምና አገልግሎት ባለሙያዎችን በማቀናጀት እንዴት መሥራት ይቻላል? የሚለውን ለማወቅ ለአራት ቀን ያህል ሥልጠናውን መውሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት የሚከሰቱ የጤና ዕክሎችን እንዴት አድርጎ መመለስ ይቻላል የሚለውን ለማወቅ የተለያዩ ሥልጠናዎችን መውሰዳቸውን፣ በአሁኑ ወቅት የወሰዱት ሥልጠናም ለሥራቸው ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው፣ ሥልጠናውም ባለሙያዎች እርስ በርስ ልምድ በመለዋወጥ ዘርፉ ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲያድግ እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...