Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከአምስት ሚሊዮን በላይ የኮቪድ-19 ክትባቶች ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ተገለጸ

ከአምስት ሚሊዮን በላይ የኮቪድ-19 ክትባቶች ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ተገለጸ

ቀን:

የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ከዓለም አቀፍ ተቋማትና ከአፍሪካ ኅብረት ጋር በመቀናጀት፣ ከአምስት ሚሊዮን በላይ ክትባቶች ለማስገባት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ይህንን የገለጸው ዓርብ ሚያዝያ 8 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡ ከ430 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ክትባቱን መውሰዳቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በተለያዩ ምክንያቶች ከቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ወገኖችም ክትባቱን ለማድረስ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

የጤና ሚኒስትር ሊ ታደሰ (ዶ/ር) ስለክትባቱ ከተለያዩ አገሮች የሚወጡ የተሳሳቱ መረጃዎችን በመንቀፍ፣ ክትባቱን የወሰዱ የእምነት አባቶችና እናቶች ለሌሎች ዜጎች አርዓያ መሆን መቻላቸው የሚበረታታ ዕርምጃ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹ወረርሽኙ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ መሠራጨቱን ተከትሎ፣ የመከላከያ መንገዶች ተፈጻሚነት ተግባራዊ ቢሆኑም፣ አሁንም በማኅበረሰቡ ዘንድ ግን ወረርሽኙን ችላ ማለት ይታያል፤›› ሲሉ ሚኒስትሯ አሳስበዋል፡፡

ዓምና የወጣው መመርያ እንደ አዲስ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ተግባራዊ መደረግ ከተጀመረ አንስቶ ማስክ የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን፣ እንዲሁም ያለ ጥንቃቄ የሚደረጉ ስብሰባዎች መቀነሳቸውን ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

የጤና ባለሙያዎች፣ ሠራተኞችና ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ ለሆኑ፣ እንዲሁም፣ ዕድሜያቸው 55 እና ከዚያ በላይ ሆነው ተጓዳኝ የጤና ችግር ያለባቸውን ሰዎች ክትባቱን እንዲወስዱ መደረጉን የገለጹት ሚኒስትሯ፣ ክትባቱን አስመልክቶ ከሚወጡ የተሳሳቱ መረጃዎች መቆጠብ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በቅርቡም በሚደረገው ምርጫ ላይ ሰዎች ራሳቸውን ከወረርሽኙ እንዲጠብቁ ለማስቻል፣ ምርጫ ቦርድ ኮቪድን ታሳቢ ያደረገ የምርጫ መመርያ ማውጣቱን አስታውሰዋል፡፡

የወረርሽኝ ሥርጭት ለመግታት የሃይማኖት ተቋማትና የእምነት አባቶች ትልቅ ድርሻ ስላላቸው፣ ለማኅበረሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር ኃላፊነታቸውን መውጣት ይገባቸዋል ሲሉ ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከቁጥጥር ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ከ73 ሺሕ የሚበልጡ ግለሰቦች ማስክ ባለማድረግና አካላዊ ርቀትን አለመጠበቅ የተመዘገበ ሲሆን፣ ከ400 በላይ ድርጀቶች ሕጋዊ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው፣ 30 ግለሰቦችና 16 ተቋማት ጉዳያቸው በሕግ እየታየ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ወረርሽኝ ለመከላከል ከሚደረገው ሥራ ጎን ለጎን የጤና ተቋማትን አቅም ለማሳደግ በተደረገ ርብርብ የኦክስጂን አቅርቦትን ወደ 2,500 ሲሊንደር ማሳደግ መቻሉን፣ ተጨማሪም 215 የመተንፈሻ ማሽኖች ለተቋማት እየተሠራጩ እንደሚገኙ፣ ይህም በኮቪድ ፅኑ ሕክምና የሚያገኙ ታካሚዎችን ከ653 ወደ 892 ከፍ ማድረግ እንደተቻለ በመግለጫው ወቅት ተብራርቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

‹‹ደስታ›› የተባለችው አማርኛ ተናጋሪ ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም

‹‹እንደ ሮቦት ዋነኛው አገልግሎቴ ውስብስብ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አሠራሮችን...