Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትፕሪሚየር ሊጉን እያመሰ የሚገኘው ኮቪድ-19 ወረርሽኝ

ፕሪሚየር ሊጉን እያመሰ የሚገኘው ኮቪድ-19 ወረርሽኝ

ቀን:

በአንድ ጀምበር ዓለምን ያናወጠና የሰው ልጅን ሕይወት እየቀጠፈ የሚገኘው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቷል፡፡ ቀናት በነጎዱ ቁጥር የሰዎችን ቁጥር እየቀጠፈ ከመምጣቱም በዘለለ፣ የሰው ልጅን የዕለት ከዕለት ሕይወት ማመሰቃቀሉን ተያይዞታል፡፡ በዓለም ላይ ከ2.99 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ የቀጠፈው ወርርሽኙ፣ ከበሽታው ያገገሙትን ሕይወት ሳይቀር እየፈተነ ከመጣ ሰነባብቷል፡፡

በወረርሽኙ ምክንያት ኪሳራ የገጠማቸው በርካታ የቢዝነስ ተቋማት ቢኖሩም ማንሰራራት ተስኗቸው እስከወዲያኛው የጠፉም የትየለሌ ናቸው፡፡ ወረርሽኙ መከሰቱን ተከትሎ አገሮች ሕዝባቸውን ከቤት እንዳይወጡ ዕገዳ ቢጥሉም፣ ዕገዳው ግን መዝለቅ ባለመቻሉ ቫይረሱን መቆጣጠር የሚያስችል መንገድን እየተከተሉና ማኅበረሰቡ ክትባት እየተከተቡ የዕለት ከዕለት ኑሮ እንዲገፉ በማድረግ ጥንቃቄ እያደረጉ መኖሩን ቀጥለዋል፡፡

በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅነት ያለው ስፖርታዊ ክንውንም በወረርሽኙ ጉዳት ከደረሰባቸው ዘርፎች ውስጥ ተጠቃሽ ነው፡፡ በርካታ ረብጣ ገንዘቦች የሚዘዋወርባቸው የእግር ኳስ ውድድሮችም የዚህ ወርርሽኝ ገፈት ቀማሽ ሆነዋል፡፡ በእንግሊዝ  የሚገኘው ኪኖት ማስተር ስተዲ የተባለ ዩኒቨርሲቲ ባደረገው ጥናት መሠረት፣ እ.ኤ.አ 2019/20 ውድድር እስከ አምስተኛ ደረጃን ይዘው የሚያጠናቅቁ ክለቦች አራት ቢሊዮን ዩሮ ሊያጡ እንደሚችሉ አስልቶ ነበር፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የአገሮቻቸውን የጤና ተቋማት የሚያወጡትን ሕግ ተከትለው ውድድራቸውን ያለምንም ተመልካች እንዲያከናወኑ የተፈቀደላቸው ክለቦች ጨዋታዎችን ከጀመሩ ዓመት አልፏችዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም 2012 ዓ.ም. ላይ ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንቱ ላይ ደርሷል፡፡ ክለቦች ጤና ሚኒስቴር ያወጣው ፕሮቶኮል ጠብቀው ውድድራቸውን በአምስት ስታዲየሞች እያከናወኑ ይገኛል፡፡ ከአዲስ አበባ የጀመረው የዘንድሮ ውድድር አንድ ክለብ ተጫዋቾችን በ72 ሰዓት ወስጥ እያስመረመረ ውድድሩን እንዲያከናውን ያዛል፡፡

ይኼን ተከትሎም ውድድራቸውን በድሬዳዋ እያከናወኑ የሚገኙት ክለቦች፣ በርካታ ተጫዋቾች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት እየታመሰ መሆኑ እየተደመጠ ነው፡፡ ይኼ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ የወላይታ ድቻ፣ አዳማ ከተማ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ድሬዳዋ ከተማ፣ ሐዋሳ ከተማና የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ተጫዋቾች በጥቂቱ ከሦስት የሚበልጡ ተጫዋቾቻቸው በቫይረሱ መያዛቸው ተገልጿል፡፡ ከተጫዋቾቹ ባሻገርም ጨዋታዎቹን ሊመሩ በከተማዋ የተገኙ ዋናና ረዳት ዳኞች በቫይረሱ መያዛቸው ተነግሯል፡፡

የ2013 ዓ.ም. የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድደር ለማከናወን ድሬዳዋ የከተሙት ክለቦቹ፣ ጥንቃቄ ከማድረግ አንፃር ግዴለሽነት እንደሚስተዋልባቸው ተጠቁማል፡፡ ተጫዋቾቹ መዝናኛ ቦታዎች ላይ ማሳለፍ፣ ሕዝብ የሚሰበሰብበት ሥፍራ ማዘውተር እንዲሁም አንድ ክፍል ለሁለት መጋራትና ጎል ከተቆጠረ በኋላ አጉል መተቃቀፍ ይስተዋልባችዋል ተብሏል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ሊጉን በበላይነት የሚመራው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር፣ የተጫዋቾችን ጥንቃቄ የጎደለው እንቅስቃሴ በመታዘብ፣ ክለቦች ጠንከር ያለ ዕርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል፡፡

ከዚህም በሻገር ማንኛውም ክለብ በ72 ሰዓት ውስጥ ተጫዋቾቹን በመንግሥት የጤና ተቋማት ጋር አስመርምሮ መምጣት እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ ሆኖም ክለቦች በድሬዳዋ ከተማ የሚያደርጉት ምርመራ ውጤትና ሐረር በሚገኘው ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተደረገው የምርመራ ውጤት ለየቅል ሆኖ በመገኘቱ ውዝግብ ተፈጥሯል፡፡

ሐሙስ ሚያዝያ 7 ቀን 2013 ዓ.ም. የቀጣይ ዓመት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠው አክሲዮን ማኅበሩ፣ በድሬዳዋ እየተከናወነ በሚገኘው ውድድር ወቅት ክለቦች ምርመራ ማድረግ ያለባቸው በ78 የመንግሥት የጤና ተቋማት ብቻ መሆኑን አስረድቷል፡፡ በዚህም መሠረት ክለቦች ከተጠቀሱት የመንግሥት ጤና ተቋማት ውጪ የተደረጉ ምርመራዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም ብሏል፡፡

በድሬዳዋ ምርመራ የተደረገላቸው 11 ተጫዋቾች ናሙና ወደ አዲሰ አበባ የተላከ ሲሆን ምርመራውም በሒደት እንዳለ ጊዜው ሲደርስ እንደሚገለጽ፣ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ክፍሌ ሰይፉ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡

በተለይ ድሬዳዋ በኢትዮጵያ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከፀናባቸው ከተሞች አንዷ በመሆኗ፣ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚሻ አስተያየቶች ሲዘነዘሩ ይስተዋላል፡፡

ቀደም ብሎ በጤና ሚኒስቴር ፕሮቶኮል ውስጥ አሥር ተመልካቾች በስታዲየም ተግኝተው ክለባቸውን መደገፍ እንደሚችሉ ፈቃድ ቢሰጥም፣ አሁን ላይ ካለው ሁኔታ አንፃር ማንም ገብቶ መመልከት እንደማይችል አስቀምጠዋል፡፡

ከስምንት ጨዋታ ያነሰ ዕድሜ የቀረው የዘንድሮ ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የመጨረሻ ጨዋታዎች ሐዋሳ ከተማ ይከናወናሉ፡፡ በወቅታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት አንፃር ድሬዳዋን ተከትሎ ሐዋሳ ክፍተኛ ተጠቂዎችን ያስተናገደች ከተማ መሆኗ ይታወቃል፡፡ ከዚህም አንፃር ክለቦች ተጫዋቾቹን መቆጣጠርና ጠበቅ ያለ ክትትል ማድረግ ካልቻሉ፣ በሐዋሳ ከተማ የከፋ ጊዜ ሊገጥማቸው እንደሚችል ይገመታል፡፡  

በኢትዮጵያ እየተስፋፋ በመጣው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የበርካታ ሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈ እንደሚገኝ በየወቅቱ የሚወጡት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

‹‹ደስታ›› የተባለችው አማርኛ ተናጋሪ ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም

‹‹እንደ ሮቦት ዋነኛው አገልግሎቴ ውስብስብ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አሠራሮችን...