የኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒኬሽን ባለስልጣን ሁለት አዲስ የቴሌኮሙዩኒኬሽን ፈቃዶችን ለመስጠት ባወጣው ጨረታ ሁለት የውጭ ኩባንያዎች ብቻ ተጫራች ሆነው ቀረቡ።
የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን ሁለትየ ቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድ ለመስጠት ያወጣው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ የጊዜ ገደብ መጠናቀቅን ተከትሎ በተሰጠው ጊዌ ውስጥ የጨረታ ምላሽ የሰጡ ኩባንያዎችን ዛሬ ሚያዝያ 18 ቀን 2013 ዓ.ም. ባካሄደው የጨረታ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሠረት ለጨረታ የቀረበውን ሁለት የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድ ለማግኘት የጨረታ ሰነዶቻቸውን ያስገቡት ሁለት ኩባንያዎች የደቡብ አፍሪካው ኤሚቲኤን እና ዓለም አቀፍ ጥምረት ለኢትዮጵያ በሚል መጠሪያ በተመሠረተው ጥምረት አባል የሆኑት ነኬንያው ሳፋሪኮም ፣ ቮዳኮም ከደቡብ አፍሪካ፣ ቮዳፎን ከብሪታኒያ፣ ሰሚቶም ኮርፖሬሽን ከጃፖን ናቸው።
የጨረታ ሰነድ ለማስገባት የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ለሁለት ጊዜ ከተራዘመ በኋላ ሰኞ ሚያዚያ 18 ቀን የተዘጋ ሲሆን ፤ ይህም ማለት ከላይ ከተጠቀሱት ኩባንያዎች ውጪ ሌሎች ኩባንያዎች በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉበት እድል ተዘግቷል ማለት ነው።
በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱት ሁለት ኩባንያዎች ያስገቡት የፋይናንስና ቴክኒካል ሰነድ በጨረታ ኮሚቴው ከተገመገመ በኃላ ውጤቱ ይፋ እንደሚሆን ተገልጿል።
ሁለቱ ኩባንያዎች የሚወዳደሩት አንድ ፈቃድ ለማግኘት በመሆኑ እና የኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒኬሽን ባለስልጣን ያወጣው ጨረታ ሁለት የቴሌኮም አገልግሎት ፈቃድ ለመሰጠት በመሆኑ እና ለውድድር የቀረበቱም ሁለት ኩባንያዎች በመሆናቸው በኩባንያዎቹ መካከል የተለየ ውድድር ሊኖር እንደማይችል ባለሙያዎች ይገልጻሉ።
በመሆኑም በጨረታው የተሳተፉት ኩባንያዎች በመንግስት የተመቀጠውን መመዠኛ ካሟሉ የአገልገሎት ፈቃዱን ሊያገኙ እንደሚችሉ ይገልጻሉ።
ነገር ግን በጨረታው በርካታ ኩባንያዎች ቢሳተፉ የተሻለ ጥቅም ይገኛል ብሎ መንግስት ካመነ ጨረታውን ሊሰርዘው እንደሚችልም ባለሙያዎቹ ገልጸዋል።
መንግስት የቴሌኮም ዘርፉን ለውድድር ክፍት እንዲሆን በወሰነው መሠረት በመካሄድ ላይ የሚገኘው በዚህ ጨረታ አሸናፊ ሆነው የሚገቡ ኩባንያዎች ከ126 ዓመት በላይ በኢትዮ ቴሌኮም በብቸኝነት ተይዞ የነበረው የቴሌኮም ገበያ የሚጋሩ ይሆናል።