Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ከ6.7 ቢሊዮን ብር በላይ እንዳይሸሽ መከላከል መቻሉን አስታወቀ

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ከ6.7 ቢሊዮን ብር በላይ እንዳይሸሽ መከላከል መቻሉን አስታወቀ

ቀን:

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ከተፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ ባከናወነው የሀብት ክትትልና ምርመራ ሥራ፣ 6,762,942,319.23 ብር ለወንጀል መፈጸሚያነት እንዳይውልና በሕገወጥ መንገድ እንዳይሸሽ መከላከል መቻሉን አስታወቀ፡፡

 ዓቃቤ ሕግ ገንዘቡ የሕወሓት ሕገወጥ ቡድን መሆኑን ጠቁሞ፣ መጠኑ 97,573,164.30 ብር በሕግ አግባብ የውርስ ውሳኔ እንዲሰጥበት ለሚመለከተው አካል ማስተላለፉን አስረድቷል፡፡

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በድረ ገጹ እንዳስታወቀው፣ የሕወሓት ሕገወጥ ቡድን በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ከፈጸመ ማግሥት ጀምሮ ሲቆጣጠራቸው የነበሩ ገንዘብና ንብረቶች ለሕገወጥ ዓላማ ሊጠቀምባቸው ይችላል በሚል በተጠረጠሩ ድርጅቶች፣ እንዲሁም በጦርነቱ በተሳተፉ የጦር መኮንኖችና ሌሎች ባለሥልጣናት ላይ በተደረገ የሀብት ክትትልና ምርመራ ውጤታማ ሥራዎች ተመዝግበዋል፡፡

ከሕወሓት ሕገወጥ ቡድን ጋር በመሠለፍ በጦርነት የተሳተፉ ዋና ዋና ተጠርጣሪዎች ገንዘብና ሀብት ላይ በተደረገ ክትትልናማጣራት ሥራ  44,911,466.19 ብር፣ አክሲዮን የገዙበት ገንዘብ  9,326,099.17 ብር፣ በድምሩ ብር 54,237,565.36 እና ሌሎች ብዛት ያላቸው ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲታገድ ተደርጓል ብሏል፡፡

በኤፈርት ሥር በሚተዳደሩና ተያያዥ በሆኑ የተለያዩ ድርጅቶች ላይ በተከናወነ የሀብት ክትትልና ምርመራ ሥራ 3,785,770,669.30 ብርና አክሲዮን የተገዛበት የገንዘብ መጠን 419,946,392.37 ብር፣ በድምሩ 4,205,717,061.67 ብር በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳገድ መቻሉንም ጠቁሟል፡፡ እንዲሁም ግምታቸው ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ የሆኑና ጂቡቲ የነበሩ 179 የደረቅና የፈሳሽ ጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ለማሸሽ ጥረት ሲያደርጉ፣ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማውጣትና የጋራ የሕግ ትብብር ጥያቄ ለጂቡቲ መንግሥት በማቅረብ ወደ አገር ማስመለስ መቻሉን አስታውቋል፡፡

የኤፈርት ድርጅቶች ገንዘብና ንብረት ለተጨማሪ የወንጀል ተግባር መፈጸሚያ እንዳይውሉ ከፍተኛ የመከላከል ሥራ መሥራት መቻሉንና በአሁኑ ወቅት የወንጀልና የሀብት ምርመራው ተጠናቆ ርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ፣ ድርጅቶቹ በፍርድ ቤት በተሾሙ ገለልተኛ አባላት አደራ ቦርድ ሥር ሆነው ለሕጋዊ ዓላማ ብቻ እንዲሠሩ ክትትል እየተደረገ መሆኑን አስረድቷል፡፡

በተመሳሳይ በሕወሓት ሕገወጥ ቡድንና በዚህ ቡድን ሥር በነበሩ አመራሮች ቀጥተኛ ቁጥጥር ይደረግባቸው በነበሩና ቡድኑ የድርጅቶችን ገንዘብ ለወንጀል መፈጸሚያ ሊውሉ ይችሉ የነበሩ ሦስት ስቪል ማኅበራት ላይ በተደረገ የሀብት ክትትልና ምርመራ ሥራ፣ 400,150,617.87 እና አክሲዮን የተገዛበት 5,254,910.10 ብር፣ በድምሩ ብር 405,405,527.97 በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማሳገድገለልተኛ አስተዳዳሪ በፍርድ ቤት በማሾም የማኅበራቱ ገንዘብ ለሕገወጥ ዓላማ እንዳይውል መከላከል መቻልን ጠቁሟል፡፡፡

በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ጄነራል በተከናወነው የሀብት ክትትልና ምርመራ ሥራ፣ የሕወሓት የሆነ  97,582,164.33 ብር በፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማሳገድ ሕገወጥ ቡድኑ ለወንጀል ተግባር እንዳይጠቀምበትና ማሸሽ እንዳይችል መከላከል ከመቻሉም በላይ፣ ሕወሓት የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከምዝገባ የሰረዘው በመሆኑ ይኼንን ገንዘብ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 99 (2) እና (3) መሠረት ዕዳውን ሸፍኖ የሚተርፍ የፓርቲው ገንዘብ ካለ፣ ለሥነ ዜጋና መራጮች ትምህርት እንዲውል በምርመራ ከተሰባሰቡ ማስረጃዎች ጋር አባሪ በማድረግ መጋቢት 17 ቀን 2013 .ም. ለቦርዱ እንዲተላለፍ ማድረጉንም አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...