Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአውሮፓ ኅብረት ለኤርትራ የፈቀደውን የመንገድ ግንባታ የፋይናንስ ድጋፍ ለመሰረዝ ማቀዱ ተሰማ

የአውሮፓ ኅብረት ለኤርትራ የፈቀደውን የመንገድ ግንባታ የፋይናንስ ድጋፍ ለመሰረዝ ማቀዱ ተሰማ

ቀን:

የአውሮፓ ኅብረት ለኤርትራ መንግሥት የፈቀደውን ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ የሚያገናኝ የመንገድ ግንባታ የሚውል የፋይናንስ ድጋፍ ለመሰረዝ ማቀዱ ተሰማ።

ኅብረቱ ሰሞኑን ባካሄደው ወይይት ላይ ለኤርትራ ከተፈቀደው የፋይናንስ ድጋፍ ያልተለቀቀው ቀሪ 120 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንዲሰረዝ የሚል ክርክር ተነስቶበት የመጨረሻ ውሳኔ ለማሳለፍ ቀጠሮ እንደተያዘለት፣ ከኅብረቱ የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።

የፋይናንስ ድጋፉ የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት ... 2018 የሰላም ስምምነት አድርገው ዳግም ግንኙነትመጀመራቸው ለኤርትራ መንግሥት የተፈቀደ እንደነበር ይታወሳል።

ኢትዮጵያና ኤርትራን ለሚያገናኘው አዲስ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ከፈቀደው የፋይናንስ ድጋፍ ውስጥ፣ ለመጀመርያው ምዕራፍ የሚውል መጠነኛ የፋይናንስ ድጋፍ ከዓመት በፊት ለኤርትራ መንግሥት መለቀቁን መረጃው ያመለክታል።

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በዚህ የፋይናንስ ድጋፍ ላይ የመከረው የኅብረቱ የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽንከተለቀቀው ውጪ ያለው ቀሪ 120 ሚሊዮን ዶላር እንዲሰረዝ የሚል ክርክር እንደተካሄደበት መረጃዎቹ ያመለክታሉ።

የአውሮፓ ኅብረት ዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽን አባላት ቀሪው የፋይናንስ ድጋፍ ሊሰረዝ ይገባል በማለት በሚያቀርበው ምክንያት በኤርትራ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ አለመሻሻሉን የሚጠቅስ ሲሆንየኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ግጭት ውስጥ መሳተፉና ከትግራይ ክልል እንዲወጣ በአውሮፓ ኅብረትና በሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የቀረበውን ጥሪ ተቀብሎ ለመተግበር ዳተኝነት አሳይቷል የሚል ምክንያትም አባሪ ሆኖ ተነስቷል።

ኅብረቱ ለኤርትራ ከፈቀደው የፋይናንስ ድጋፍ ቀሪው 120 ሚሊዮን ዶላር ጉዳይ ላይ በዚህ ሳምንት የመጨረሻ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆንእንዲሰረዝ የተጠየቀው ቀሪ የገንዘብ መጠን በአፍሪካ ቀንድ ለሚገኙ ሌሎች ዓላማዎች እንዲውል ተጠይቋል። 

በዚህ መሠረት 62 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነው የሱዳንን የዴሞክራሲ ሽግግር ለመደገፍ፣ 18 ሚሊዮን ዶላር ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው ወደ ሱዳን ለተሰደዱ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እንዲውል፣ ቀሪው 20 ሚሊዮን ዶላር በደቡብ ሱዳን ያለውን የምግብ አቅርቦት ችግር ለመፍታትና የተቀረው 20 ሚሊዮን ዶላር በአፍሪካ ቀንድ ለተፈናቀሉ ሰዎችና ስደተኞች ድጋፍ እንዲውል አማራጭ ሐሳብ ቀርቧል። 

ነገር ግን ኅብረቱ በዚህ ጉዳይ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጠው በቀጣዮቹ ቀናት እንደሆነ መረጃው ያመለክታል።

የአውሮፓ ኅብረት ከትግራይ ክልል ቀውስ ጋር በተገናኘ 80 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚሆን የቀጥታ በጀት ድጋፍ በኢትዮጵያ ላይ እንዲታገድ 2013 ዓ.ም. የመጀመርያ ወራት መወሰኑ ይታወሳል።

የኤርትራ መንግሥት ከትግራይ ክልል ጋር በተገናኘ ለቀረበበት ወቀሳየኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ ክልል ለመግባት የተገደደው የሕወሓት ቡድን ወደ አስመራ የተኮሰው ሮኬት በኤርትራ ብሔራዊ ደኅንነት ላይ ሥጋት በማጫሩ እንደሆነ የሚገልጽ ደብዳቤ ከቀናት በፊት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት አስገብቷል።

ይህ ምክንያት ለመንግሥታቱ ድርጅት አባል አገሮች በሙሉ እንዲደርስ የሚጠይቀው ደብዳቤውከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በተደረገው ስምምነት መሠረት የኤርትራ ጦር ከትግራይ ለቆ የሚወጣ መሆኑንም ያመለክታል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...