Tuesday, April 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበበዓሉ መዳረሻ በርካታ የንግድ ተቋሞች እየተሳተፉ ነው

በበዓሉ መዳረሻ በርካታ የንግድ ተቋሞች እየተሳተፉ ነው

ቀን:

በተለያዩ ኤግዚቢሽንና ባዛሮች ላይ ሸማቾች እዚህም እዚያ እየተዘዋወሩ ያላቸውን ጥሪት አውጥተው ለመግዛት ሲሯሯጡ ይታያሉ፡፡ በነዚህም ቦታዎች ላይ ከተለያዩ ቦታ የተውጣጡ ነጋዴዎችም ምርቶቻቸውን ለመሸጥ እንቅስቃሴያቸውን ከጀመሩ ሳምንታት ተቆጥረዋል፡፡

ይኼም በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት ለሚከበረው የትንሳዔ በዓል ድባብ እንዲኖረው አድርጎታል፡፡ የበዓሉን ድባብ አስመልክቶ ሁለተኛ ዙር አገር አቀፍ የሞዴል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽን ‹‹የሚሠሩ እጆች ይበረታታሉ›› በሚል መሪ ቃል በመቻሬ ሜዳ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የከተሞች የሥራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረ መስቀል ጫላ እንደገለጹት፣ ምርትና አገልግሎቶች ለተጠቃሚዎች እንዲተዋወቁና ለሽያጭ እንዲውሉ ከሚደረግባቸው ሥልቶች መካከል ኤግዚቢሽንና ባዛሮች ትልቁን ድርሻ ይይዛሉ፡፡ በተለይም የገበያ ትስስሮችን ከመፍጠር አኳያ አስተዋጿቸው ትልቅ ነው ብለዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከሚያዝያ 18 ቀን 2013 ዓ.ም. የተጀመረውና ለሰባት ቀን የሚቆየው አገር አቀፉ ኤግዚቢሽንና ባዛር ከ280 በላይ ሞዴል የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉ መሆኑን የገለጹት አቶ ገብረ መስቀል፣ የ4.8 ሚሊዮን ብር የገበያ ትስሰር እንደሚፈጠርላቸው አስረድተዋል፡፡

በኤግዚቢሽንና ባዛሩ ላይ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ፣ በእንጨትና ብረታ ብረት፣ በጨርቃ ጨርቅ፣ በቆዳና ቆዳ ውጤቶች፣ በምግብና መጠጥ ዝግጅት፣ በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በፈሳሽ ሳሙናና በሌሎች ምርቶች ላይ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ምርቶታቸውን ይዘው መቅረባቸውን ገልጸዋል፡፡

ኤግዚቢሽንና ባዛሩ በታቀደው መሠረት ለማሳካትና የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት እንዲቻል አራት ንዑሳን ኮሚቴዎችን ያቀፈ አንድ ዓብይ ኮሚቴ ተቋቁሞ የተቀናጀ እንቅስቃሴ ሲደረግ መቆየቱን ዳይሬክተሩ አስታውሰዋል፡፡

በተያያዘም የኮሮና ወረርሽኝን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ከ250 በላይ ነጋዴዎች ተሳታፊ የሆኑበት የኢትዮ አዲስ የፋሲካ ንግድ ትርዒት እየተካሄደ መሆኑን የጆርካ ኢቨንት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታደሰ ታምራት ገልጸዋል፡፡

የኮሮና ወረርሽኝ እንዳይሠራጭ ጥንቃቄ በተሞላ መልኩ እየተካሄደ የሚገኘው ይህ ኤግዚቢሽን፣ ለመገበያየት ለሚመጡ ሰዎች የገንዘብ እጥረት በሚያጋጥማቸው ጊዜ በአፋጣኝ እንዲያገኙ ለማድረግ ባንኮች በንግድ ትርዒቱ ላይ እንዲሠሩ ማድረጋቸውንም ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በፊት አብዛኛውን ተጠቃሚዎች ገንዘብ ለማውጣት የሚጠቀሙበትን የኤትኤም ማሽን ይዘው ቢንቀሳቀሱም አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸውን የገለጹት ኃላፊው፣ በአሁኑ ወቅት ይህንን ችግር ሙሉ ለሙሉ መቅረፍ እንደቻሉ  አስረድተዋል፡፡

ለሰባተኛ ጊዜ የሚካሄደው ይህ የንግድ ትርዒት በአሁኑ ወቅት እየተባባሰ የመጣውን የዋጋ ንረት ያረጋጋል ተብሎ እንደሚታሰብና ሰዎች የፈለጉትን ምርት በቀላሉ እንዲያገኙ የሚረዳ ነው ብለዋል፡፡

የንግድ ትርዒቶች ለብዙ ሰዎች የሥራ ዕድል እየፈጠሩ መሆኑን ኢንተርፕራይዞችም ከሌሎች ተቋሞች ጋር የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት ጭምር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በሙስሊሞች ዘንድ የሚከበረውን ኢድ አል ፈጥርን በማስመልከት፣ ከሚያዝያ 27 ቀን ጀምሮም በግዮን ሆቴል ከ150 በላይ ኢንተርፕራይዞችን በማሳተፍ የንግድ ትርዒት ለማከናወን ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን አቶ ታደሰ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

በሌላ በኩል፣ ‹‹አገራዊ ጥሪ ለማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት›› በሚል መሪ ቃል ለሁለተኛ ዙር የተዘጋጀው አገር አቀፍ የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ኤግዚቢሽን ከ250 በላይ የሚሆኑ ኢንተርፕራይዞች እየተሳተፉ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

አምራች ኢንዱስትሪዎች ፈጠራ ላይ በማተኮርና ለጥራት ከፍ ያለ ትኩረት በመስጠት በአገር ውስጥም አልፈው በውጭ ገበያ ተወዳዳሪ እንደሆኑ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑም ተነግሯል፡፡

በአዲስ አበባም በተለያዩ ቦታዎች ላይ ለሚካሄዱት ኤግዚቢሽንና ባዛሮች ላይ ከቻይና፣ ከህንድ፣ ከሱዳንና ከሌሎችም የመጡ ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን ይዘው ተሳታፊ እየሆኑ ይገኛል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...